Daily Weather Report 25 Apr 02

Weather Summary for previous day

April 1, 2025

በትናንትናዉ ዕለት በምዕራብ አማራ፣ በምዕራብ፣ ደቡብና ምስራቅ ኦሮሚያ እና በደቡብ ምዕራብ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸዉ፡፡ ከዚሁ ጋር በተያይዘም በጎንደር፣ ፉኝዶ፣ ጊምቢ፣ አርጆ፣ ጎሬ፣ ቦሬ፣ ኩሉምሳ፣ አቦምሳ፣ ገለምሶ፣ ቡሌሆራ፣ አማን፣ ሳዉላ፣ ወላይታ፣ ኮንሶ፣ ዲላ፣ ብላቴ፣ ደንገጎ፣ ኩርፋጨሌ እና ቁልቢ ከቀላል መጠን ያለዉ ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን በሰመራ፣ አዋሽ አርባ፣ ገዋኔ፣ ጋምቤላ እና ፉኝዶ ከ38-43.8 ዲግሪ ሴልሺየስ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, there was cloud cover over western Amhara, western, southern and eastern Oromia and southwestern parts of our country. In connection with this, light to moderate rain was recorded in Gondar, Fugendo, Gimbi, Arjo, Gore, Bore, Kulumsa, Abomsa, Gelemso, Bulehora, Aman, Saula, Wolaita, Konso, Dilla, Bilate, Dengego, Kurfachele and Qulbi. On the other hand, the highest temperature of the day was recorded in Semera, Awash Arba, Gewane, Gambella and Fugendo between 38-43.8 degrees Celsius.

Weather Forecast for next day

April 3, 2025

በነገዉ ዕለት በልግ ዋነኛና ሁለተኛ የዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ማዕከላዊ፣ ሰሜንና ደቡብ ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም እና አዊ፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ቡኖ በደሌ፣ ኢሉባቦር፣ ምስራቅ እና ምዕራብ ሐረርጌ፣ ሆሮጉድሩ፣ ቄለም፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ፤ ድሬዳዋ፣ ሐረር፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል፣ አሶሳ እና ማኦ ኮሞ፤ ከጋምቤላ ክልል የኢታንግ፣ አኙዋክና ማጃንግ ፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳዉሮ ዞኖች ፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ኮንሶ እና ቡርጂ፣ የሲዳማ ክልል፣ ከሶማሌ ክልል የፋፈን፣ ኤረር፣ ጃራር፣ ኖጎብ፣ ቆራሄ፣ ሸበሌ፣ ዳዋ፣ ሊበን፣ አፍዴር እና ዶሎ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን (1-29 ሚ.ሜ) ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በሁመራ፣ ዳንሻ፣ መተማ፣ ቋራ፣ ፓዌ፣ መተከል፣ ጋምቤላ፣ አቦቦ፣ ፉኝዶ፣ ላሬ፣ አዋሽ አርባ፣ ዳልፋጊ እና ገዋኔ ላይ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ38-41 ዲግሪ ሴልሺየስ በላይ ሆኖ ይመዘገባል፡፡

Tomorrow, there will be cloud cover over the areas of our country that receive the main and second rains during the Belg. In connection with this, the west, central, north and south Gondar, west and east Gojam, and Awi zones of the Amhara region; From the Oromia Region: Jimma, Buno Bedele, Ilubabor, East and West Hararge, Horugudru, Kelem, West and East Wellega, Guji and West Guji, Bale and East Bale zone; Dire Dawa, Harar; from the Benishangul Gumuz Region: Metekel, Asosa and Mao Komo zones; from the Gambella Region: Itang, Anuak and Majang zones; from the Southwestern Ethiopia Region: Bench Sheko, Sheka, Kefa, Konta, West Omo and Dawuro zones; The Wolaita, Gamo, Gofa, Basketo, Konso and Burji zones of the Southern Ethiopian Region, the Sidama Region zones, and the Fafen, Erer, Jarar, Nogob, Korahe, Shebele, Dawa, Liben, Afder and Dolo zones of the Somali Region will receive light to moderate rainfall (1-29 mm). On the other hand, Humera, Dansha, Metema, Quara, Pawe, Metekel, Gambella, Abobo, Fugendo, Lare, Dalifagi and Gewane will record daily maximum temperatures above 38-41 degrees Celsius.