Daily Weather Report 25 Apr 01
Weather Summary for previous day
በትናንትናዉ ዕለት በምዕራብ፣ በደቡብ ምዕራብ እና በምስራቅ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸዉ፡፡ ከዚሁ ጋር በተያይዘም በጋምቤላ፣ ላሬ፣ ፉኝዶ፣ ነቀምቴ፣ አርጆ፣ ጎሬ፣ በደሌ፣ ቦሬ፣ አቦምሳ፣ መተሐራ፣ ኩሉምሳ፣ ገለምሶ፣ ቡሌሆራ ሐዋሳ፣ ሰኮሩ፣ እምድብር፣ ወላይታ፣ ዲላ፣ ተርጫ፣ አርባምንጭ፣ ጂንካ፣ ብላቴ፣ ያቤሎ፣ ደንገጎ፣ ግራዋ፣ ኩርፋጨሌ፣ ቁልቢ እና ሐሮማያ ከቀላል መጠን ያለዉ ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በተጨማሪም በማሻ እና አደሌ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል ፡፡ በሌላ በኩል የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን በፓዌ፣ አዋሽ አርባ፣ ጋምቤላ እና ፉኝዶ ከ38-42.5 ዲግሪ ሴልሺየስ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, there was a cloud cover over the western, southwestern and eastern parts of our country. In connection with this, light to moderate rain was recorded in Gambella, Lare, Fugendo, Nekemte, Arjo, Gore, Bedele, Bore, Abomsa, Metahara, Kulumsa, Gelemso, Bulehora, Hawassa, Sekoru, Emdbir, Wolaita, Dilla, Tercha, Arbaminch, Jinka, Bilate, Yabelo, Dengego, Girawa, Kurfachele, Qulbi and Haromaya. Additionally, heavy rainfall of over 30 mm was recorded in Masha and Adele. On the other hand, the highest temperature of the day was recorded in Pawe, Awash, Gambella and Fugendo between 38-42.5 degrees Celsius.
Weather Forecast for next day
በነገዉ ዕለት ለበልግ ዝናብ መፈጠር አመቺ የሆኑ የአየር ሁኔታ ክስተቶች በሰሜን፣ በሰሜን ምዕራብ፣ በምዕራብ፣ በደቡብ ምዕራብ እና በምስራቅ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የተሻለ ጥንካሬ ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ማዕከላዊ፣ ሰሜንና ደቡብ ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም እና አዊ ዞኖች ፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ቡኖ በደሌ፣ ኢሉባቦር፣ ምስራቅ እና ምዕራብ ሐረርጌ፣ሆሩጉድሩ፣ ቄለም፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ፣ አርሲ እና ምዕራብ አርሲ ዞኖች፤ ድሬዳዋ፣ ሐረር፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል፣ አሶሳ እና ማኦ ኮሞ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክና ማጃንግ ዞኖች ፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳዉሮ ዞኖች ፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ኮንሶ እና ቡርጂ ዞኖች፣ የሲዳማ ክልል ዞኖች፣ ከሶማሌ ክልል የፋፈን፣ ኤረር፣ ጃራር፣ ኖጎብ፣ ቆራሄ፣ ሸበሌ፣ ዳዋ፣ ሊበን፣ አፍዴር እና ዶሎ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን (1-29 ሚ.ሜ) ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም ኢሉባቦር፣ ባሌ፣ ጉጂ፣ ፋፈን እና ሊበን በ24 ሰዓት ዉስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ ፡፡ በሌላ በኩል በመተማ፣ ቋራ፣ ሁመራ መተከል፣ ጋምቤላ፣ አቦቦ፣ ፉኝዶ፣ ላሬ እና ገዋኔ ላይ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ38-41 ዲግሪ ሴልሺየስ በላይ ሆኖ ይመዘገባል፡፡
Tomorrow Weather conditions favorable for the occurrence of belg rains will be stronger in the north, northwest, west, southwest, and east of our country. In connection with this, the west, central, north and south Gondar, west and east Gojam, and Awi zones of the Amhara region; From the Oromia Region: Jimma, Buno Bedele, Ilubabor, East and West Hararge, Horugudru, Kelem, West and East Wellega, Guji and West Guji, Bale and East Bale, Arsi and West Arsi zones; Dire Dawa, Harar; from the Benishangul Gumuz Region: Metekel, Asosa and Mao Komo zones; from the Gambella Region: Anuak and Majang zones; from the Southwestern Ethiopia Region: Bench Sheko, Sheka, Kefa, Konta, West Omo and Dawuro zones; The Wolaita, Gamo, Gofa, Basketo, Konso and Burji zones of the Southern Ethiopian Region, the Sidama Region zones, and the Fafen, Erer, Jarar, Nogob, Korahe, Shebele, Dawa, Liben, Afder and Dolo zones of the Somali Region will receive light to moderate rainfall (1-29 mm). Additionally, Ilubabor, Bale, Guji, Fafen and Liben will receive heavy rainfall exceeding 30 mm in 24 hours. On the other hand, Metema, Quara, Humera, Metekel, Gambella, Abobo, Fugendo, Lare and Gewane will record daily maximum temperatures above 38-41 degrees Celsius.