Daily Weather Report 24 Sep 30
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በሰሜንና ምዕራብ አማራ፤ በቤንሻንጉል ጉሙዝ፤ በጋምቤላ፤ በኦሮሚያ፤ በሲዳማ፤ በሰሜን ሶማሌ፤ በደቡብ እና ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም የሰሜንና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ፣ ምዕራብ ጎጃም እና ደቡብ ወሎ ዞኖች፤ የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ ምዕራብና ደቡብ ምዕራብ ሸዋ፣ ባሌ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረና፣ ምዕራብ እና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል እና አሶሳ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ ዞን፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሀድያ፣ ጉራጌ እና ስልጤ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የጎፋ፣ ጋሞ፣ ኮንሶ፣ ቡርጂ እና ደቡብ ኦሞ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የፋፈን ዞን ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለዉ ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም ሸርኮሌ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, north and west Amhara; Benshangul Gumuz; Gambella; Oromia; Sidama; northern Somali; south and central Ethiopia had cloud coverage. In association with this, north and central Gondar, Awi, west Gojjam and south Wollo zones; Jimma, Ilubabor, Horo Guduru, west and east Wellega, west and south west Shewa, Bale, Arsi and west Arsi, west Guji, Borena, west and east Hararge zones; from Benishangul Gumuz region Metekel and Asossa zones; from Gambella region Agnuwak zone; from the central Ethiopian region Hadiya, Gurage and Silte zones; from the south region Ethiopia Gofa, Gamo, Konso, Burji and South Omo zones; Sidama region zones and Fafen zone of Somali region received light to moderate rainfall. In addition, more than 30 mm of heavy rain was recorded over Sherkole.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት ለዝናብ መፈጠር ምቹ ሁኔታን የሚፈጥሩ የአየር ሁኔታ ክስተቶች በምዕራብ፣ በሰሜን ምስራቅ፣ በመካከለኛው፣ በምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የተሻለ ጥንካሬ የሚኖራቸው ሲሆን፤ በደቡብ እና ደቡብ ምስራቅ የሀገሪቱ ክፍሎችም የተሻለ የዝናብ ስርጭት ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከትግራይ ክልል የምዕራብ እና ሰሜን ምዕራብ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ምዕራብ እና ምስራቅ ጎጃም፣ ደቡብ ወሎ እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል፣ ካማሽ፣ አሶሳ እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ቄለም፣ ምዕራብና ምስራቅ እና የሆሮጉድሩ ወለጋ ዞኖች፣ ሰሜን፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብና ምስራቅ ሸዋ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ፣ ቦረና እና ምስራቅ ቦረና ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ሐረር፤ ድሬዳዋ፣ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ፣ ኑዌር፣ ኢታንግ እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳዉሮ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀላባ፣ ሀድያ፣ የየም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጎፋ፣ ጋሞ፣ ባስኬቶ፣ አማሮ፣ ደራሸ፣ ኮንሶ፣ ቡርጂ፣ ደቡብ ኦሞ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ሁሉም ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የሲቲ፣ ፋፈን፣ ጃራር፣ ኤሬር፣ ኖጎብ፣ ዳዋ፣ ሊበን፣ እና ቆራሔ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በቻግኒ፣ በዳንግላ፣ በባህርዳር፣ በደንበጫ፣ በማንዱራ፣ በወንበራ፣ በሳሲጋ፣ በጅማአርጆ፣ በሲቡሲሬ፣ በጅማራሬ፣ በጨዋቃ፣ በባኮቲቤ፣ በቀርሳ፣ በሶኮሩ፣ በአሴኮ፣ በኩርፋጨሌ፣ በፈዲስ፣ በማጂ፣ በሳላማጎ፣ በተርጫ፣ በሶሮ፣ በጎምቦራ፣ በካዎኮይሻ እና በክንዶኮይሻ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡:
Tomorrow, the weather events that create favorable conditions for the formation of rain will have better strength over the west, north east, central and east parts of the country; will also have better rainfall distribution over the south and south east areas of the country. Along with this, from the Tigray region west and north west zones; from the Amhara region west, north, south and central Gondar, Awi zone, west and east Gojjam, south Wollo and north Shewa zones; from the Benishangul Gumuz region Metekel, Kamashi, Asossa and Mao Komo zones; from the Oromia region Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, Kelam, west and east and Horo Guduru Wellega zones, north, west, south west and east Shewa, Arsi and west Arsi, Guji and west Guji, Bale and east Bale, west and east Hararge, Borena and east Borena zones; Addis Ababa; Harar; Dire Dawaa; from the Gambella region Agnuwak, Nuwer, Itang and Majang zones; from the south west Ethiopia region Bench Sheko, Sheka, Kefa, Konta, west Omo and Dawuro zones; from the central Ethiopia region Gurage, Silte, Halaba, Hadiya, Yem special zone, Kambata and Tembaro zones; from the south Ethiopia region Walaita, Gofa, Gamo, Basketo, Amaro, Derashe, Konso, Burji, south Omo and Gedeo zones; all the zones of Sidama region and from Somali region of Siti, Fafen, Jarar, Erer, Nogob, Dawa, Liben, and Korahe zones will receive light to moderate rainfall in many places. In addition, Chagni, Dangila, Bahirdar, Denbecha, Mandura, Wanbera, Sasiga, Jimma Arjo, Sibusire, Jimma Rare, Chewaka, Bakotibe, Kersa, Sokoru, Aseko, Kurfachele, Fedis, Maji, Salamago, Tercha, Soro, Gombora, Kawokoisha and Kindokoisha will receive more than 30 mm of heavy rainfall in 24 hours.