Daily Weather Report 24 Sep 28

Weather Summary for previous day

Sept. 27, 2024

በትናንትናው ዕለት በትግራይ፤ በአማራ፤ በኦሮሚያ፤ በሲዳማ፤ በደቡብ እና ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም ማዕከላዊና ደቡብ ምስራቅ ትግራይ ዞኖች፤ የሰሜን፣ ምዕራብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች፤ ከአፋር ክልል የአዉሲ ዞን፤ የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብና ምስራቅ ሸዋ፣ ባሌ፣ አርሲ፣ ምዕራብ ጉጂ፣ ምዕራብ እና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ሐረር፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሀድያ ዞን፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የቡርጂ ዞን እና የሲዳማ ክልል ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለዉ ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በአለምከተማ፣ በነቀምቴ እና በአርጆ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, over Tigray; Amhara; Oromia; Sidama; south and central Ethiopia had cloud coverage. In association with this, the central and south east Tigray zones; north, west and central Gondar, Awi, west and east Gojjam, north and south Wollo and north Shewa zones; Awusi zone from Afar region; Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, Horo Guduru, west and east Wellega, west, south west and east Shewa, Bale, Arsi, west Guji, west and east Hararge zones; Addis Ababa; Harar; from the central Ethiopia region Hadiya zone; from the south Ethiopia region Burji zone and Sidama region zones received light to moderate rainfall. In addition, more than 30 mm of heavy rainfall was recorded over Alemketama, Nekemte and Arjo.

Weather Forecast for next day

Sept. 29, 2024

በነገው ዕለት ለዝናብ መፈጠር ምቹ ሁኔታን የሚፈጥሩ የአየር ሁኔታ ክስተቶች በምዕራብ አጋማሸ፣ በመካከለኛው እና በምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ ቀጣይነት ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከትግራይ ክልል የምዕራብ እና ሰሜን ምዕራብ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜንና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ምዕራብ እና ምስራቅ ጎጃም ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል፣ ካማሽ፣ አሶሳ እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ቄለም፣ ምዕራብና ምስራቅ እና የሆሮጉድሩ ወለጋ ዞኖች፣ ሰሜን፣ ምዕራብና ደቡብ ምዕራብ ሸዋ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ፣ ምዕራብ እና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ ሐረር፤ ድሬዳዋ፣ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ፣ ኑዌር፣ ኢታንግ እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳዉሮ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀላባ፣ ሀድያ፣ የየም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጎፋ፣ ጋሞ፣ ባስኬቶ፣ አማሮ፣ ደራሸ፣ ኮንሶ፣ ቡርጂ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ሁሉም ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የፋፈን፣ ጃራር እና ኤሬር ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በማንዱራ፣ በቻግኒ፣ በአሶሳ፣ በማኦኮሞ፣ በቤጊ፣ በነጆ፣ በሰዮ፣ በዲጋ፣ በጅማአርጆ፣ በኑኑኩምባ፣ በሲቡሲሬ፣ በጮራ፣ በቡሬ፣ በመቱ፣ በአሌ፣ በበደሌ፣ በአልጌ፣ በማሻ፣ በተርጫ፣ በካዎኮይሻ፣ በዳሞትሶሬ፣ በክንዶኮይሻ፣ በቁጫ፣ በቦረዳ፣ በቡርሳ፣ በጉርሱም እና በሐሮረየስ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል ከሚጠናከሩት የአየር ሁኔታ ክስተቶች ላይ በመነሳት በደቡብና በደቡብ ምስራቅ የሀገራችን አከባቢዎች ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡

Tomorrow, the weather conditions favoring the formation of rain will continue over the western half, central and eastern parts of the country. Along with this, from the Tigray region west and north-west zones; from the Amhara region west, north and central Gondar, Awi zone, west and east Gojjam zones; from the Benishangul Gumuz region Metekel, Kamash, Asossa and Mao Komo zones; from the Oromia region Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, Kelam, Horo Guduru, west and east and Wellega zones, north, west and south west Shewa, Arsi and west Arsi, Guji and west Guji, Bale and east Bale, west and east Hararge zones; Harar; Dire Dawa; from the Gambella region Agnuwak, Nuwer, Itang and Majang zones; from the south west Ethiopia region Bench Sheko, Sheka, Kefa, Konta, west Omo and Dawuro zones; from the central Ethiopia region Gurage, Silte, Halaba, Hadiya, Yem special zone, Kambata and Tembaro zones; from the south Ethiopia region Walaita, Gofa, Gamo, Basketo, Amaro, Derashe, Konso, Burji and Gedeo zones; all zones of Sidama region and fro Somali region Fafen, Jarar and Erer zones will receive light to moderate rainfall in many places. In addition, Mandura, Chagni, Asossa, Mao Komo, Begi, Nedjo, Sayo, Digga, Jimma Arjo, Nunu Kumba, Sibusire, Chora, Bure, Mettu, Ale, Bedele, Alge, Masha, Tercha, Kawokoisha, Damotsore, Kindokoisha, Kucha, Boreda, Bursa, Gursum and Haroreyes will receive heavy rainfall of more than 30 mm in 24 hours. On the other hand, due to the strengthening weather events, the south and south east areas of our country will have rainfall