Daily Weather Report 24 Sep 26

Weather Summary for previous day

Sept. 25, 2024

በትናንትናው ዕለት በሰሜን፣ በምዕራብ፣ በደቡብ፣ በመካከለኛው እና በምስራቅ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም የሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም ዞኖች፤ የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ ባሌ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ምዕራብ ጉጂ እና ምዕራብ ሐረርጌ ዞኖች፤ ድሬዳዋ፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል እና አሶሳ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ ዞን፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የጋሞ እና ደቡብ ኦሞ ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የፋፈን ዞን ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለዉ ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በጊምቢ፣ በአርጆ፣ በበደሌ፣ በጨለንቆ እና በካራሚሌ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, the north, west, south, central and east parts of the country had cloud coverage. In line with this, north, south and central Gondar, Awi, west and east Gojjam; Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, Horo Guduru, west and east Wellega, Bale, Arsi and west Arsi, west Guji and west Hararge zones; Dire Dawa; from the Benishangul Gumuz region Metekel and Asossa zones; from the south west Ethiopia region Bench Sheko zone; from the south Ethiopia region Gamo and south Omo zones and Fafen zone of Somali region received light to moderate rainfall. In addition, more than 30 mm of heavy rain was recorded over Gimbi, Arjo, Bedele, Chelenko and Karamile.

Weather Forecast for next day

Sept. 27, 2024

በነገው ዕለት በምዕራብ አጋማሸ፣ በመካከለኛው እና ምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከትግራይ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ እና ማዕከላዊ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ምዕራብ እና ምስራቅ ጎጃም፣ ዋግኸምራ፣ ደቡብ ወሎ እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል፣ ካማሽ፣ አሶሳ እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ቄለም፣ ምዕራብና ምስራቅ እና የሆሮጉድሩ ወለጋ ዞኖች፣ ሰሜን፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብና ምስራቅ ሸዋ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ባሌ ምዕራብ እና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ሐረር፤ ድሬዳዋ፣ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ እና ዳዉሮ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀላባ፣ ሀድያ፣ የየም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጎፋ፣ ጋሞ፣ ባስኬቶ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ሁሉም ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የፋፈን ዞን በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በአርማጮ፣ በአቸፈር፣ በጃዊ፣ በዳንግላ፣ በአሶሳ፣ በማኦኮሞ፣ በቤጊ፣ በጉቶጊዳ፣ በጅማአርጆ፣ በኑኑኩምባ፣ በሲቡሲሬ፣ በጅማራሬ፣ በአቤዶንጎሮ፣ በባኮቲቤ፣ በሊሙሴቃ፣ በቀርሳ፣ በሶኮሩ፣ የየም ልዩ ዞን፣ በአሮሬሳ እና በዶዶላ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በደቡብና በደቡብ ምስራቅ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ ከሚኖረው የደመና ሽፋን በጥቂት ስፍራዎቻቸው ላይ ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡

For the coming day, there will be cloud coverage over the western half, central and eastern parts of the country. Along with this, from the Tigray region west, north west and central zones; from the Amhara region west, north, south and central Gondar, Awi zone, west and east Gojjam, Waghemra, south Wollo and north Shewa zones; from the Benishangul Gumuz region Metekel, Kamash, Asossa and Mao Komo zones; from the Oromia region Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, Kelam, Horo Guduru, west and east and Wellega zones, north, west, south west and east Shewa, Arsi and west Arsi, Guji and west Guji, Bale, west and east Hararge zones; Addis Ababa; Harar; Dire Dawa; from the Gambella region Agnuwak and Majang zones; from the south west Ethiopia region Bench Sheko, Sheka, Kefa, Konta and Dawuro zones; from the central Ethiopia region Gurage, Silte, Halaba, Hadiya, Yem special zone, Kambata and Tembaro zones; from south Ethiopia region Walaita, Gofa, Gamo, Basketo and Gedeo zones; all zones of Sidama region and from Somali region Fafen zone will receive light to moderate rainfall in many places. In addition, Armacho, Achefer, Jawi, Dangila, Asossa, Mao Komo, Begi, Gutogida, Jimma Arjo, Nunu Kumba, Sibusire, Jimma Rare, Abedongoro, Bakotibe, Limuseka, Kersa, Sokoru, Yem special zone, Aroresa and Dodola will receive heavy rainfall of more than 30 mm in 24 hours. On the other hand, from the cloud coverage in the south and south east areas of our country will receive light rainfall in a few places.