Daily Weather Report 24 Sep 25

Weather Summary for previous day

Sept. 24, 2024

በትናንትናው ዕለት በሰሜን፣ ምዕራብ እና ምስራቅ አማራ፤ በምዕራብ፣ መካከለኛ እና ምስራቅ ኦሮሚያ፤ በጋምቤላ፤ በሲዳማ፤ በሰሜን ሶማሌ፤ በደቡብ ምዕራብ፣ ደቡብ እና ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም የሰሜንና ማዕከላዊ ጎንደር አዊ፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም እና ደቡብ ወሎ ዞኖች፤ የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሸዋ፣ ባሌ፣ አርሲ፣ ምዕራብ ጉጂ፣ ምዕራብ እና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ሐረር፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል እና አሶሳ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ እና ዳዉሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ እና ጋሞ ዞኖች፣ የሲዳማ ክልል ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የፋፈን ዞን ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለዉ ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በሊሙገነት ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, north, west and east Amhara; west, central and east Oromia; Gambella; Sidama; northern Somali; south west, south and central Ethiopia had cloud coverage. In line with this, the north and central Gondar Awi, west and east Gojjam and south Wollo zones; Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, Horo Guduru, west and east Wellega, west and east Shewa, Bale, Arsi, west Guji, west and east Hararge zones; Addis Ababa; Harar; from the Benishangul Gumuz region Metekel and Asossa zones; from the south west Ethiopia region Bench Sheko, Sheka and Dawuro zones; from the South Ethiopia region Walaita and Gamo zones; Sidama region zones and the Fafen zone of Somali region received light to moderate rainfall. In addition, more than 30 mm of heavy rain was recorded over Limugenet.

Weather Forecast for next day

Sept. 26, 2024

በነገው ዕለት እርጥበታማው የአየር ሁኔታ በምዕራብ፣ በደቡብ ምዕራብ እና በመካከለኛው የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ ቀጣይነት ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከትግራይ ክልል የምዕራብ እና ሰሜን ምዕራብ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ምዕራብ እና ምስራቅ ጎጃም፣ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል፣ ካማሽ፣ አሶሳ እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ቄለም፣ ምዕራብና ምስራቅ እና የሆሮጉድሩ ወለጋ ዞኖች፣ ሰሜን፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብና ምስራቅ ሸዋ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ባሌ እና ምዕራብ ሐረርጌ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ሐረር፤ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ እና ከፋ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀላባ፣ ሀድያ፣ የየም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የፋፈን ዞን በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በአሶሳ፣ በማኦኮሞ፣ በቤጊ፣ በጊዳሚ፣ በሊሙ፣ በሳሲጋ፣ በጅማአርጆ፣ በሲቡሲሬ፣ በደዴሳ እና በባኮቲቤ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል ከሚጠናከሩት የአየር ሁኔታ ክስተቶች ላይ በመነሳት በደቡብና በደቡብ ምስራቅ የሀገራችን አከባቢዎች ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡

Tomorrow, the wet weather will continue over the west, south west and central parts of the country. Along with this, from the Tigray region the west and north west zones; from the Amhara region the west, north, south and central Gondar, Awi zone, west and east Gojjam zones; from the Benishangul Gumuz region Metekel, Kamash, Asossa and Mao Komo zones; from the Oromia region Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, Kelam, west and east and Horo Guduru Wellega zones, north, west, south west and east Shewa, Arsi and west Arsi, Bale and west Hararge zones; Addis Ababa; Harar; from the Gambella region Agnuwak and Majang zones; from the south west Ethiopia region Sheka and Kefa zones; from the central Ethiopia region Gurage, Silte, Halaba, Hadiya, Yem special zone, Kambata and Tembaro zones; from the south Ethiopia region, Walaita and Gedeo zones; zones of Sidama region and Fafen zone of Somali region will receive light to moderate rainfall in many places. In addition, Asossa, Mao Komo, Begi, Gidami, Limmu, Sasiga, Jimma Arjo, Sibusire, Dedesa and Bakotibe will receive heavy rainfall of more than 30 mm in 24 hours. On the other hand, due to the strengthening of the weather events, the south and south east areas of our country will have light rainfall.