Daily Weather Report 24 Sep 24

Weather Summary for previous day

Sept. 23, 2024

በትናንትናው ዕለት አይከል፣ ባህርዳር፣ ፓዌ፣ ዳንግላ፣ ቻግኒ፣ ጨፋ፣ ወራኢሉ፣ ማንኩሽ፣ ኤሊዳር፣ ዱብቲ፣ አይራ፣ ነቀምቴ፣ ጎሬ፣ ጭራ፣ አርሲሮቤ፣ አደሌ፣ ቦሬ፣ ቡሌሆራ፣ ነገሌ፣ አለምተፈሪ፣ ወላይታ ሶዶ፣ ሳዉላ፣ አርባ ምንጭ፣ አማን፣ ቴፒ፣ ፉኚዶ፣ ሐረር፣ ሐዋሳ፣ ብላቴ እና ቡርጂ የደመና ሽፋን የነበራቸው ሲሆን ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡

Yesterday, Ayikel, Bahirdar, Pawe, Dangila, Chagni, Chifra, Wareilu, Mankush, Elidar, Dubti, Aira, Nekemte, Gore, Chira, Arsirobe, Adele, Bore, Bulehora, Negelle, Alemteferi, Walaita Sodo, Sawula, Arba Minch, Aman, Tepi, Fugnido, Harar, Hawasa, Bilate and Burji had cloud coverage and also received light to moderate rainfall.

Weather Forecast for next day

Sept. 25, 2024

በነገው ዕለት በሰሜን ምዕራብ፣ በምዕራብ እና በመካከለኛው እንዲሁም በደቡብ እና በደቡብ ምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከትግራይ ክልል የምዕራብ እና ሰሜን ምዕራብ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ምዕራብ እና ምስራቅ ጎጃም ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል፣ ካማሽ ፣አሶሳ እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ቄለም፣ ምዕራብና ምስራቅ እና የሆሮጉድሩ ወለጋ ዞኖች፣ ምዕራብና ደቡብ ምዕራብ ሸዋ፣ ምዕራብ አርሲ፣ ባሌ፣ ጉጂ እና ምዕራብ ሐረርጌ ዞኖች፤ ሐረር፤ ከጋምቤላ ክልል የማጃንግ ዞን፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ እና ከፋ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ሀላባ፣ ሀድያ፣ የየም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የባስኬቶ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ሁሉም ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የፋፈን ዞን በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በመተማ፣ በአርማቾ፣ በፓዌ፣ በወምበርማ፣ በአሶሳ፣ በጅማአርጆ፣ በኑኑኩምባ፣ በኖኖቤንጃ እና በአውባሬ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡

Tomorrow, there will be cloud coverage over the north West, west and central as well as south and south east parts of the country. Along with this, from the Tigray region the west and north west zones; from the Amara region west, north, south and central Gondar, Awi zone, west and east Gojjam zones; from Benishangul Gumuz region Metekel, Kamash, Asossa and Mao Komo zones; from Oromia region Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, Kelam, west and east and Horo Guduru Wellega zones, west and south west Shewa, west Arsi, Bale, Guji and west Hararge zones; Harar; from Gambella region Majang zone; from the south west Ethiopia region Sheka and Kefa zones; from the central Ethiopian region Gurage, Halaba, Hadiya, Yem special zone, Kambata and Tembaro zones; from the south Ethiopia region Basketo and Gedeo zones; all zones of Sidama region and Somali region Fafen zone will receive light to moderate rainfall in many places. In addition, Metema, Armacho, Pawe, Wemberima, Asossa, Jimma Arjo, Nunu Kumba, Nono Benja and Awubare will experience heavy rainfall of more than 30 mm in 24 hours.