Daily Weather Report 24 Sep 22
Weather Summary for previous day
በትናትናው ዕለት አይከል፤ ቻግኒ፣ ዳንግላ፣ ባህር ዳር፣ በደ/ወርቅ፣ ኮምቦልቻ፣ ስሪንቃ፣ ጨፋ፣ መሃል ሜዳ፣ ዳሊፋጊ፤ አሶሳ፣ ነቀምቴ፣ ሻምቡ፣ ካቺስ፣ አርጆ፣ አይራ፣ ጎሬ፣ ቡሬ፣ ሊሙ ገነት፣ አቦምሳ፣ ቁሉምሳ፣ አደሌ፣ አርሲ፣ ቡሌሆራ፣ ነገሌ፣ ሞያሌ፣ ጅግጅጋ፣ አዲስ አበባ፣ ሐረር፣ ሐዋሳ፣ ብላቴ፣ ቦሬ፣ ሳውላ፣ ተርጫ፣ ሆሳዕና፣ አማን፣ ወላይታ ሶዶ እና ዲላ የደመና ሽፋን የነበራቸው ሲሆን ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡
Yesterday Metekel, Chagni, Dangla, Bahr Dar, De/ Werk, Kombolcha, Srinka, Chifa, Mehale Meda, Dalifagi; Asosa, Nekemte, Shambu, Kachis, Arjo, Aira, Gore, Bure, Limu Gent, Abomsa, Kulumsa, Adele, Arsi, Bulehora, Negele, Moyale, Jigjiga, Addis Ababa, Harer, Hawassa, Bilate, Bore, Sawula, Tercha, Hosaina, Aman, Wolayta Sodo and Dila had cloud cover and received light to moderate rainfall.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት ዝናብ ሰጭ የአየር ሁኔታ ክስተቶች በሰሜን ምዕራብ፣ በምዕራብ እና በምስራቅ እንዲሁም በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት የደቡብና ደቡብ ምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከትግራይ ክልል የምዕራብ እና ሰሜን ምዕራብ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ ዞን እና ምዕራብ ጎጃም ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል፣ አሶሳ፣ ካማሽ እና ማኦ ኮሞ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ቄለም ወለጋ፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ ሆሮጉድሩ ወለጋ፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ ዞኖች፤ምዕራብ እና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች ፤ ድሬዳዋ፤ ሐረር፤ ከጋምቤላ ክልል የማጃንግ እና አኙዋክ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ እና ዳዉሮ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ስልጤ፣ ሀላባ፣ ሀድያ፣ የየም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ባስኬቶ፣ ጎፋ፣ ጋሞ እና ጌዲኦ ዞኖች ፤የሲዳማ ክልል ሁሉም ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል ፋፈን ዞን በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ የሚያገኙ ሲሆን ፤ በተጨማሪም ቤጊ፣ ማኦ ኮሞ፣ አሶሳ፣ ኩምሩክ፣ ቡሬ፣ መቱ፣ ያዩ፣ ግራዋ፣ ፈዲስ፣ ባቢሌ እና ሸበሌ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡
Tomorrow Weather conditions favorable for the formation of rain will have cloud cover in the north-west, west and east and the south and, which are Bega the second rainy season of the south-east regions of the country. In addition, the western and northwestern zones of the Tigray region; West and Central Gondar, Awi Zone and West Gojam Zones from Amhara Region; Metekel, Asosa, Kamash and Mao Komo zones from Benshangul Gumuz region; From the Oromia region, Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, Kelem Welega, West and East Welega, Horogudru Welega, Bale and East Bale, Arsi and West Arsi zones; West and East Harerge zones; Dire Dawa; Harar; Majang and Anuwak zones from Gambella region; Sheka, Kefa, Konta and Dawuro zones from South West Ethiopia region; From the Central Ethiopia Region, Silte, Halaba, Hadia, Yem Special Zone, Kambata and Tmbaro Zones; Wolayta, Basketo, Gofa, Gamo and Gedo zones from South Ethiopia region; All zones of Sidama region and Fafen zone from Somali region will receive light to medium amount of rain in many places. In addition, Begi, Mao Como, Asosa, Kumruk, Bure, Mettu, Yayu, Grawa, Fadis, Babile and Shebele will receive heavy rainfall of more than 30 mm in 24 hours.