Daily Weather Report 24 Sep 21

Weather Summary for previous day

Sept. 20, 2024

በትናትናው ዕለት በመቀሌ፤ አይከል፤ ሻሁራ፣ ዳንግላ፣ ባህር ዳር፣ በደ/ወርቅ፣ ላሊበላ፣ ስሪንቃ፣ ወረኢሉ፣ ጨፋ፣ ኤሊዳር፣ ዳሊፋጊ፤ አሶሳ፣ቡለን፤ ነቀምቴ፣ ሻምቡ፣ ኢጃጂ፣ አይራ፣ ጅማ፣ ጎሬ፣ መተሐራ፣ አቦምሳ፣ ቁሉምሳ፣ ኑራኢራ፣ አደሌ፣ አርሲ፣ ቡሌሆራ፣ ነገሌ፣ ሞያሌ፣ ጅግጅጋ፣ ብላቴ፣ ቦሬ፣ ሳውላ፣ አርባ ምንጭ፣ ጂንካ፣ ኮንሶ እና ቡርጂ የደመና ሽፋን የነበራቸው ሲሆንና ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በሌላ በኩል ከነበረው ጠንካራ የደመና ክምችት የተነሳ በአየሁ እና ተርጫ በ24 ሠዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday in Mekele. Ayekel. Shahura, Dangla, Bahr Dar, De/Werk, Lalibela, Srinka, Wareilu, Xifa, Elidar, Dalifagi; Asosa, Bullen; Nkemte, Shambu, Ijaji, Aira, Jimma, Gore, Methara, Abomsa, Qlumsa, Nuraira, Adele, Arsi, Bulehora, Negele, Moyale, Jigjiga, Blate, Bore, Saula, Arba Moshan, Jinka, Konso and Burji had cloud cover. Along with this, they received light to moderate rainfall. On the other hand, more than 30mm of heavy rainfall was recorded in Ayehu and Terta in 24 hours due to strong cloud cover.

Weather Forecast for next day

Sept. 22, 2024

በነገው ዕለት ለዝናብ መፈጠር አመቺ የሆኑ የአየር ሁኔታ ክስተቶች በሰሜን ምዕራብ፣ በምዕራብ እና በምስራቅ እንዲሁም በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት የደቡብና ደቡብ ምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከትግራይ ክልል የምዕራብ እና ሰሜን ምዕራብ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ ዞን እና ምዕራብ ጎጃም ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል፣ አሶሳ፣ ካማሽ እና ማኦ ኮሞ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ቄለም ወለጋ፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ ሆሮጉድሩ ወለጋ፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ ዞኖች፤ምዕራብ እና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች ፤ ድሬዳዋ፤ ሐረር፤ ከጋምቤላ ክልል የማጃንግ እና አኙዋክ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ እና ዳዉሮ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ስልጤ፣ ሀላባ፣ ሀድያ፣ የየም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ባስኬቶ፣ ጎፋ፣ ጋሞ እና ጌዲኦ ዞኖች ፤የሲዳማ ክልል ሁሉም ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል ፋፈን፣ ኤረር፣ ጃራር፣ ኖጎብ፣ ቆራሄ፣ ሸበሌ፣ አፍዴር፣ ሊበን እና ዳዋ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም አንፊሎ፣ ሰዮ፣ አመያ፣ ቦንጋ፣ ቡሬ፣ መቱ፣ አጋርፋ፣ አዳባ፣ ጎባ፣ ፈዲስ እና ግራዋ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡

Tomorrow Weather conditions favorable for the formation of rain will have cloud cover in the north-west, west and east and the south and, which are Bega the second rainy season of the. south-east regions of the country. In addition, the western and northwestern zones of the Tigray region; West and Central Gondar, Awi Zone and West Gojam Zones from Amhara Region; Plantation, Asosa, Kamash and Mao Komo zones from Benshangul Gumuz region; From the Oromia region, Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, Kelem Welega, West and East Welega, Horogudru Welega, Bale and East Bale, Arsi and and West Arsi zones; West and East Harerge zones; Dire Dawa; Harar; Majang and Anuwak zones from the Gambella region; Sheka, Kefa, Konta and Dawuro zones from South West Ethiopia region; From the Central Ethiopia Region, Silte, Halaba, Hadia, Yem Special Zone, Kambata and Tembaro Zones; From South Ethiopia region, Wolayta, Basketo, Gofa, Gamo and Gedo zones; all zones of Sidama region and Fafen, Erer, Jarar, Nogob, Korahe, Shebele, Afder, Liben and Dawa zones from Somali region will receive light to moderate rainfall in many places. In addition, Anfilo, Sayo, Amaya, Bonga, Bure, Mettu, Agarfa, Adaba, Goba, Fadis and Grawa will receive more than 30mm of heavy rainfall in 24 hours.