Daily Weather Report 24 Sep 20
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በሰሜን እና ምዕራብ አማራ፤ በምዕራብ፣ ማዕከላዊ፣ ደቡብ እና ምስራቅ ኦሮሚያ፤ በጋምቤላ፤ በስዳማ፤ በደቡብ ምዕራብ እና ደቡብ ኢትዮጵያ ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም የአዊ፣ ሰሜን እና ማዕከላዊ ጎንደር ዞኖች፤ የጅማ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ አርሲ፣ ባሌ፣ ምዕራብ ጉጂ፣ ምዕራብ እና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ ከአፋር ክልል የአዉሲ ዞን፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል እና አሶሳ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የዳዉሮ ዞን፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጎፋ፣ ጋሞ፣ ቡርጂ፣ ኮንሶ እና ደቡብ ኦሞ ዞኖች እና የሲዳማ ክልል ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለዉ ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በማጂ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, the north and west Amhara; west, central, south and east Oromia; Gambella; Sidama; south west and south Ethiopia had cloud coverage. In association with this, Awi, north and central Gondar zones; Jimma, Horo Guduru, west and east Wellega, Arsi, Bale, west Guji, west and east Hararge zones; Awusi zone from the Afar region; from the Benishangul Gumuz region Metekel and Asossa zones; from south west Ethiopia region Dawuro zone; from the south Ethiopia regions Wolayta, Gofa, Gamo, Burji, Konso and south Omo zones and the zones of Sidama region received light to moderate rainfall. In addition, more than 30 mm of heavy rainfall was recorded over Maji.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት ዝናብ ሰጭ የአየር ሁኔታ ክስተቶች የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ ቀጣይነት የሚኖራቸው ሲሆን ወደ ደቡብ እና ደቡብ ምስራቅ የሀገሪቱ ክፍሎችም እንደሚስፈፉ የትንበያ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜንና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ምዕራብ እና ምስራቅ ጎጃም ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል፣ ካማሽ ፣አሶሳ እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ቄለም፣ ምዕራብና ምስራቅ እና የሆሮጉድሩ ወለጋ ዞኖች፣ ምዕራብ አርሲ፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረና እና ምስራቅ ቦረና፣ ምዕራብ እና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ ሐረር፤ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ፣ ኢታንግ እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳዉሮ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሀላባ፣ ሀድያ፣ የየም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጎፋ፣ ጋሞ፣ ባስኬቶ፣ አማሮ፣ ቡርጂ፣ ኮንሶ፣ ደራሸ፣ ደቡብ ኦሞ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ሁሉም ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የፋፈን፣ ጃራር፣ ዶሎ፣ ኤሬር፣ ቆራሔ፣ ኖጎብ፣ ሸበሌ፣ ሊበን እና ዳዋ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በማሻ፣ በማኦኮሞ፣ በጊዳሚ፣ በሳለኖኖ፣ በቦናዙሪያ እና በዲላ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡
Tomorrow, the forecast information indicates that rain-producing weather events will continue over Kiremt rainfall the areas and will spread to the south and south east parts of the country. In line with this, from the Amhara region west, north and central Gondar, Awi zone, west and east Gojjam zones; from the Benishangul Gumuz region Metekel, Kamash, Asossa and Mao Komo zones; from Oromia region Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, Kelam, west and east and Horo Guduruu Wellega zones, west Arsi, Bale and east Bale, Guji and west Guji, Borena and east Borena, west and east Hararge zones; Harar; from the Gambella region Agnuwak, Itang and Majang zones; from the south west Ethiopia region Bench Sheko, Sheka, Kefa, Konta, west Omo and Dawuro zones; from the central Ethiopia region, Halaba, Hadiya, Yem special zone, Kambata and Tembaro zones; from the south Ethiopia region Wolaita, Gofa, Gamo, Basketo, Amaro, Burji, Konso, Derashe, south Omo and Gedeo zones; all zones of Sidama region and from Somali region Fafen, Jarar, Dollo, Erer, Korahe, Nogob, Shebelle, Liben and Dawa zones will receive light to moderate rainfall in many places. In addition, in Masha, Mao Komo, Gidami, Salenono, Bonazuria and Dilla will experience heavy rainfall of more than 30 mm in 24 hours.