Daily Weather Report 24 Sep 19
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም የሰሜን ምዕራብ እና ማዕከላዊ ትግራይ ዞኖች፤ የደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ፣ ምዕራብ ጎጃም፣ ደቡብ ወሎ እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች፤ የጅማ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሸዋ፣ አርሲ፣ ባሌ እና ምዕራብ ሐረርጌ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ሐረር፤ ከአፋር ክልል የአዉሲ ዞን፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል ዞን፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የስልጤ እና ሀድያ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ እና ዳዉሮ ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የፋፈን ዞን ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለዉ ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በአንገርጉትን ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, the Kiremt rainfall benefiting parts of the country had cloud coverage. In this regard, the north west and central Tigray zones; south and central Gondar, Awi, west Gojjam, south Wollo and north Shewa zones; Jimma, Horo Guduru, west and east Wellega, west and east Shewa, Arsi, Bale and west Harargee zones; Addis Ababa; Harar; from the Afar region Awusi zone; from Benishangul Gumuz region Metekel zone; from the central Ethiopia Silte and Hadiya zones; from the south west Ethiopia region Sheka and Dawuro zones and Fafen zone of Somali region received light to moderate rainfall. In addition, more than 30 mm of heavy rainfall was recorded over Angergutin.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከትግራይ ክልል የምዕራብ እና ሰሜን ምዕራብ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜንና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ምዕራብ እና ምስራቅ ጎጃም፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል፣ ካማሽ ፣አሶሳ እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ቄለም፣ ምዕራብና ምስራቅ እና የሆሮጉድሩ ወለጋ ዞኖች፣ ምዕራብና ደቡብ ምዕራብ ሸዋ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ምዕራብ እና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ ሐረር፤ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ፣ ኢታንግ እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ እና ዳዉሮ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀላባ፣ ሀድያ፣ የየም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጎፋ፣ ጋሞ፣ ባስኬቶ፣ አማሮ፣ ቡርጂ፣ ደራሸ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ሁሉም ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የሲቲ፣ ፋፈን፣ ጃራር፣ ዶሎ እና ኤሬር ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በአሶሳ፣ በጊዳሚ፣ በጅማ ሆሮ፣ በሰዮ፣ በቡሬ፣ በሳለኖኖ፣ በቦናዙሪያ፣ በሐረር፣ በጭናክሰን፣ በኩርፋጨሌ፣ በባብሌ፣ በጉርሱም፣ በሐሮረየስ እና በአራርሶ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል ከሚጠናከሩት የአየር ሁኔታ ክስተቶች ላይ በመነሳት በምዕራብና ደቡብ ኦሞ፣ ቦረና፣ ቆራሔ፣ ሸበሌ እና ሊበን ዞኖች በጥቂት ስፍራዎቻቸው ላይ ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡
Tomorrow, there will be cloud coverage over the parts of the country that benefit from Kiremt rainfall. In line with this , from the Tigray region the western and north west zones; from the Amhara region the west, north and central Gondar, Awi zone, west and east Gojjam, Oromo ethnic special zone and north Shewa zones; from the Benishangul Gumuz region Metekel, Kamash, Asossa and Mao Komo zones; from the Oromia region Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, Kelam, west and east and Horo Guduru Wellega zones, west and southwest Shewa, Arsi and west Arsi, Bale and east Bale, Guji and west Guji, west and east Harargee zones; Harar; from the Gambella region Agnuwak, Itang and Majang zones; from the south west Ethiopia region Bench Sheko, Sheka, Kefa, Konta and Dawuro zones; from the central Ethiopian region Gurage, Silte, Halaba, Hadiya, Yem special zone, Kambata and Tembaro zones; from south Ethiopia region, Wolaita, Gofa, Gamo, Basketo, Amaro, Burji, Derashe and Gedeo zones; all the zones of the Sidama region and from the Somali region Siti, Fafen, Jarar, Dollo and Erer zones will receive light to moderate rainfall in many places. In addition, in Asossa, Gidami, Jimma Horo, Sayo, Bure, Salenono, Bonazuria, Harar, Chinaksen, Kurfachele, Babile, Gursum, Haroreyes and Ararso will receive heavy rainfall of more than 30 mm in 24 hours. On the other hand, due to strengthening weather events, the west and south Omo, Borena, Korahe, Shebelle and Liben zones will have light rainfall in a few places.