Daily Weather Report 24 Sep 18

Weather Summary for previous day

Sept. 17, 2024

በትናንትናው ዕለት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም የሰሜን ምዕራብ፣ ማዕከላዊ፣ ደቡብ እና ደቡብ ምስራቅ ትግራይ ዞኖች፤ የደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን፣ ሰሜን ሸዋ እና ዋግኸምራ ዞኖች፤ የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ቄለም፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብና ምስራቅ ሸዋ፣ አርሲ፣ ቦረና፣ ምዕራብ እና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ሐረር፤ ከአፋር ክልል የአዉሲ፣ ጋቢ እና ሀሪ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል እና አሶሳ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ ዞን፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ እና ሀድያ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ እና ዳዉሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የጎፋ ዞን እና ከሶማሌ ክልል የሲቲ እና ፋፈን ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለዉ ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በኮምቦልቻ፣ በባቲ እና በጅማ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, the Kiremt rainfall benefiting parts of the country had cloud coverage. In this regard, the northwest, central, south and southeast Tigray zones; south and central Gondar, Awi, west and east Gojjam, north and south Wollo, Oromo ethnic special zone, north Shewa and Waghemra zones; Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, Horo Guduru, Kelam, west and east Wellega, west, south west and east Shewa, Arsi, Borena, west and east Hararge zones; Addis Ababa; Harar; from the Afar region Awusi, Gabi and Hari zones; from the Benishangul Gumuz region Metekel and Asossa zones; from Gambella region Agnuwak zone; from the central Ethiopia region Gurage and Hadiya zones; from the south west Ethiopia region Bench Sheko, Sheka and Dawuro zones; from the south Ethiopia region Gofa zone and from the Somali region Siti and Fafen zones received light to moderate rainfall. In addition, more than 30 mm of heavy rainfall was recorded over Kombolcha, Bati and Jimma.

Weather Forecast for next day

Sept. 19, 2024

በነገው ዕለት ለክረምት ዝናብ መፈጠር አመቺ የሆኑ የአየር ሀኔታ ክስተቶች በክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት አከባቢዎች ላይ ቀጣይነት ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከትግራይ ክልል የምዕራብ እና ሰሜን ምዕራብ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ምዕራብ እና ምስራቅ ጎጃም ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል፣ ካማሽ ፣አሶሳ እና ማኦ ኮሞ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ቄለም፣ ምዕራብና ምስራቅ እና የሆሮጉድሩ ወለጋ ዞኖች፣ ሰሜን፣ ምዕራብና ደቡብ ምዕራብ ሸዋ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ምዕራብ እና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ሐረር፤ ከጋምቤላ ክልል የማጃንግ ዞን፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ እና ዳዉሮ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀላባ፣ ሀድያ፣ የየም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጎፋ፣ ጋሞ፣ ባስኬቶ፣ አማሮ፣ ቡርጂ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ሁሉም ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የፋፈን፣ ጃራር እና ኤሬር ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በአሌ፣ በማሻ፣ በክንዶኮይሻ፣ በዳሞትሶሬ፣ በኮኮሳ፣ በአርቤጎና፣ በቦናዙሪያ፣ በዲላ፣ በጭናክሰን፣ በባብሌ፣ በሐሮረየስ እና በአራርሶ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በደቡብና በደቡብ ምስራቅ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡

For the coming day, the weather conditions favorable for the formation of Kiremt rainfall will continue over the Kiremt rain-benefiting parts of the country. Along with this, from the Tigray region the western and northwestern zones; from the Amhara region west, north, south and central Gondar, Awi zone, west and east Gojjam zones; from the Benishangul Gumuz region Metekel, Kamash, Asossa and Mao Komo zones; from the Oromia region Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, Kelam, Horro Guduru, west and east Wellega zones, north, west and south west Shewa, Arsi and west Arsi, Bale and east Bale, Guji and west Guji, west and east Hararge zones; Addis Ababa; Harar; from Gambella region Majang zone; from the south west Ethiopia region Bench Sheko, Sheka, Kefa and Dawuro zones; from the central Ethiopian region of Gurage, Silte, Halaba, Hadiya, Yem special zone, Kambata and Tembaro zones; from the south Ethiopia region Wolaita, Gofa, Gamo, Basketo, Amaro, Burji and Gedeo zones; all zones of Sidama region and from the Somali region Fafen, Jarar and Erer zones will receive light to moderate rainfall in many places. In addition, in Ale, Masha, Kindokoisha, Damotsore, Kokosa, Arbegona, Bonazuria, Dilla, Chinaksen, Babile, Haroreyes and Ararso will receive heavy rainfall of more than 30 mm in 24 hours. On the other hand, there will be cloud coverage over the south and south east areas of our country.