Daily Weather Report 24 Sep 17
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ ጠንካራ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም የሰሜን ምዕራብ፣ ማዕከላዊ፣ ደቡብ እና ደቡብ ምስራቅ ትግራይ ዞኖች፤ የምዕራብ፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ሰሜን ሸዋ እና ዋግኸምራ ዞኖች፤ የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብና ምስራቅ ሸዋ፣ ባሌ፣ አርሲ፣ ምዕራብ ጉጂ፣ ምዕራብ እና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ሐረር፤ ድሬዳዋ፤ ከአፋር ክልል የአዉሲ፣ ጋቢ እና ሀሪ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል እና አሶሳ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ ዞን፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የስልጤ እና ሀድያ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ እና ዳዉሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ እና ደቡብ ኦሞ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የፋፈን እና ቆራሔ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለዉ ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በጊምቢ፣ በአይራ፣ በነቀምቴ፣ በአርጆ፣ በአልጌ፣ በበደሌ፣ በጋምቤላ እና በማሻ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, the Kiremt rainfall benefiting parts of the country had cloud coverage. In this regard, the northwest, central, south and southeast Tigray zones; west, south and central Gondar, Awi, west and east Gojjam, north and south Wollo, north Shewa and Waghemra zones; Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, Horo Guduru, west and east Wellega, west, south west and east Shewa, Bale, Arsi, west Guji, west and east Hararge zones; Addis Ababa; Harar; Dire Dawa; from the Afar region Awusi, Gabi and Hari zones; from the Benishangul Gumuz region Metekel and Asossa zones; from Gambella region Agnuwak zone; from the central Ethiopian region Silte and Hadiya zones; from the south west Ethiopia region Bench Sheko, Sheka and Dawuro zones; from the south Ethiopia region Walaita and south Omo zones; zones of Sidama region and Somali region Fafen and Korahe zones received light to moderate rainfall. In addition, more than 30 mm of heavy rainfall was recorded over Gimbi, Aira, Nekemte, Arjo, Alge, Bedele, Gambella and Masha.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከትግራይ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ እና ማዕከላዊ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ ደቡብ ወሎ፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች፤ ከአፋር ክልል የጋቢ፣ አዉሲ እና ሀሪ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል፣ አሶሳ፣ ካማሽ እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ቄለም፣ ምዕራብና ምስራቅ እና የሆሮጉድሩ ወለጋ ዞኖች፣ ሰሜን፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብና ምስራቅ ሸዋ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ጉጂ፣ ባሌ፣ ምዕራብ እና ምስራቅ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ድሬዳዋ፤ ሐረር፤ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ፣ ኑዌር እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳዉሮ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀላባ፣ ሀድያ፣ የየም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጎፋ፣ ጋሞ፣ ባስኬቶ፣ ጌዲኦ፣ ደራሸ፣ አማሮ እና ቡርጂ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ሁሉም ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የሲቲ፣ ፋፈን እና ጃራር ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በሁመራ፣ በወልቃይት፣ በሽራሮ፣ በሽሬ እንደስላሴ፣ በፀገደ፣ በዳንግላ፣ በቻግኒ፣ በቡሌን፣ በካማሽ፣ በሊሙ፣ በጉቶጊዳ፣ በሲቡሲሬ፣ በሰተማ፣ በኢሉ፣ በባኮጢቤ፣ በአቤዶንጎሮ፣ በአመያ፣ በኮፈሌ፣ በማሻ፣ በገሻ፣ በሶዶዙሪያ፣ በሁምቦ፣ በቦረዳ፣ በምዕራብአባያ፣ በጨንቻ፣ በአርባምንጭ ዙሪያ፣ በአርቤጎና እና በዲላ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በደቡብና ደቡብ ምስራቅ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡
Tomorrow, there will be cloud coverage over the Kiremt rainfall benefitting parts of the country. Along with this, from the Tigray region the western, north west, central; from the Amhara region west, north, south and central Gondar, Awi, west and east Gojjam, south Wollo, Oromo ethnic special zone and north Shewa zones; from the Afar region Gabi, Awusi and Hari zones; from Benishangul Gumuz region Metekel, Asossa, Kamash and Mao Komo zones; from the Oromia region Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, Kelam, Horo Guduru, west and west Wellega zones, north, west, south west and east Shewa, Arsi and west Arsi, Guji, Bale, west and east zones; Addis Ababa; Dire Dawa; Harar; from the Gambella region Agnuwak, Nuwer and Majang zones; from the South west Ethiopia region Bench Sheko, Sheka, Kefa, Konta, west Omo and Dawuroo zones; from the central Ethiopia region Gurage, Silte, Halaba, Hadiya, Yem special zone, Kambata and Tembaro zones; from the south Ethiopia region Wolaita, Gofa, Gamo, Basketo, Gedeo, Derashe, Amaro and Burji zones; all the zones of Sidama region and from the Somali region Siti, Fafen and Jarar zones will receive light to moderate rainfall in many places. In addition, in Humera, Welkait, Shiraro, Shire, Endesilase, Tsegede, Dangila, Chagni, Bulen, Kamash, Limmu, Gutogida, Sibusire, Setema, Ilu, Bakotibe, Abedongoro, Ameya, Kofele, Masha, Gesha, Sodozuria, Humbo, Boreda, Mirab Abaya, Chencha, Arbamich Zuria, Arbegona and Dilla will receive heavy rainfall of more than 30 mm in 24 hours. On the other hand, there will be cloud coverage over the south and south east areas of our country.