Daily Weather Report 24 Sep 16
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም የማዕከላዊ እና ደቡብ ትግራይ ዞኖች፤ የሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ፣ ምዕራብ ጎጃም፣ ደቡብ ወሎ እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች፤ የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብና ምስራቅ ሸዋ፣ ባሌ፣ አርሲ፣ ምዕራብ ጉጂ፣ ምዕራብ እና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ሐረር፤ ከአፋር ክልል አዉሲ ዞን፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል እና አሶሳ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የስልጤ እና ሀድያ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ እና ዳዉሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የጋሞ እና ደቡብ ኦሞ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የፋፈን ዞን ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለዉ ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በላንጌ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, the Kiremt rainfall benefiting parts of the country had cloud coverage. In association with this, the central and southern Tigray zones; north, south and central Gondar, Awi, west Gojjam, south Wollo and north Shewa zones; Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, Horo Guduru, west and East Wellega, west, south west and east Shewa, Bale, Arsi, west Guji, west and east Hararge zones; Addis Ababa; Harar; from the Afar region Awusi zone; from the Benishangul Gumuz region Metekel and Asossa zones; from the central Ethiopian region Silte and Hadiya zones; from the south west Ethiopia region Bench Sheko, Sheka and Dawuro zones; from the south Ethiopia region Gamo and south Omo zones; Sidama region zones and Fafen zone of Somali region received light to moderate rainfall. In addition, more than 30 mm of heavy rain was recorded over Lange.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት ወደ ሀገራችን የሚገባው እርጥበት አዘል የአየር ሁኔታ የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት የሀገሪቱ ክፍሎች የተሻለ ጥንካሬ ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከትግራይ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ማዕከላዊ፣ ደቡብ፣ ደቡብ ምስራቅ እና ምስራቅ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን፣ ሰሜን ሸዋ እና ዋግኸምራ ዞኖች፤ ከአፋር ክልል የቂልበቲ፣ ጋቢ፣ አዉሲ እና ሀሪ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል፣ አሶሳ፣ ካማሽ እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ቄለም፣ ምዕራብና ምስራቅ እና የሆሮጉድሩ ወለጋ ዞኖች፣ ሰሜን፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብና ምስራቅ ሸዋ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ጉጂ፣ ባሌ፣ ምዕራብ እና ምስራቅ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ድሬዳዋ፤ ሐረር፤ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ እና ዳዉሮ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀላባ፣ ሀድያ፣ የየም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጎፋ፣ ጋሞ፣ ባስኬቶ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ሁሉም ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የሲቲና ፋፈን ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በዳንሻ፣ በሽሬ እንደስላሴ፣ በአድዋ፣ በደባርቅ፣ በፎገራ፣ በባህርዳር፣ በይልማናደንሳ፣ በጃዊ፣ በዳንግላ፣ በሰከላ፣ በደጋዳሞት፣ በሳሲጋ፣ በጉቶጊዳ፣ በደዴሳ፣ በጅማአርጆ፣ በበደሌ፣ በአሌ፣ በመቱ፣ በሰተማ፣ በሊሙሴቃ፣ በቀርሳ፣ በሶኮሩ፣ በኦሞ፣ በኖኖ፣ በአምቦ ደንዲ፣ በወንጪ፣ በኮኮሳ፣ በማሻ፣ በየኪ፣ በገሻ፣ በተርጫ፣ በስልጤ፣ በለሞ፣ በአንጋቻ፣ በሶሮ፣ በወራ፣ በክንዶኮይሻ፣ በዳሞትሶሬ፣ በአርቤጎና፣ በቦሬ እና በጋብላሉ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በደቡብና ደቡብ ምስራቅ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡
Tomorrow, the humid weather entering our country will have a better strength over the Kiremt rainfall benefiting parts of the country. Along with this, from the Tigray region the western, northwestern, central, southern, southeastern and eastern zones; from the Amhara region west, north, south and central Gondar, Awi zone, west and east Gojjam, north and south Wollo, Oromo ethnic special zone, north Shewa and Waghemra Zones; from the Afar region Kilbeti, Gabi, Awusi and Hari zones; from the Benishangul Gumuz region Metekel, Asossa, Kamashi and Mao Komo zones; from the Oromia region Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, Kelam, Horo Guduru, west and west Wellega zones, north, west, southwest and east Shewa, Arsi and west Arsi, Guji, Bale, west and east Hararge zones; Addis Ababa; Dire Dawa; Harar; from Gambella region Agnuwak and Majang zones; from the south west Ethiopia region Bench Sheko, Sheka, Kefa, Konta and Dawuro zones; from the central Ethiopia region Gurage, Silte, Halaba, Hadiya, Yem special zone, Kambata and Tembaro zones; from the south Ethiopia region, Wolaita, Gofa, Gamo, Basketo and Gedeo zones; all zones of Sidama region and Somali region Siti and Fafen will receive light to moderate rainfall in many places. In addition, in Dansha, Shire Endesilase, Adwa, Debark, Fogera, Bahirdar, Yilmanadensa, Jawi, Dangila, Sekela, Degadamot, Sasiga, Gutogida, Dedesa, Jimma Arjo, Bedele, Ale, Mettu, Setema, Limuseka, Kersa, Sokoru, Omo, Nono, Ambo, Dandi, Wenchi, Kokosa, Masha, Yeki, Gesha, Tercha, Silte, Lemmo, Angacha, Soro, Warra, Kindokoisha, Damotsore, Arbegona, Bore and Gablalu will receive heavy rainfall of more than 30 mm in 24 hours. On the other hand, there will be cloud coverage over the south and south east parts of our country.