Daily Weather Report 24 Sep 14
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም የማዕከላዊ ትግራይ ዞን፤ የሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ፣ ምዕራብ እና ምስራቅ ጎጃም እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች፤ የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ ምዕራብና ደቡብ ምዕራብ ሸዋ፣ ባሌ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ እና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ድሬዳዋ፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል፣ ማኦ ኮሞ እና አሶሳ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀላባ፣ ሀድያ፣ የየም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ እና ዳዉሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጎፋ፣ ጋሞ፣ ባስኬቶ፣ አማሮ እና ጌዲኦ ዞኖች እና የሲዳማ ክልል ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለዉ ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በአርጆ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, the Kiremt rainfall benefiting parts of the country had cloud coverage. In association with this, the central Tigray zone; north, south and central Gondar, Awi, west and east Gojjam and north Shewa zones; Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, Horo Guduru, west and east Wellega, west and south west Shewa, Bale, Arsi and west Arsi and east Hararge zones; Addis Ababa; Dire Dawa; from the Benishangul Gumuz region Metekel, Mao Komo and Asossa zones; from the central Ethiopia region Gurage, Silte, Hadiya, Halaba, Yem special zone, Kembata and Tembaro zones; from the south west Ethiopia region Bench Sheko, Sheka, Kefa, Konta and Dawuro zones; from the south Ethiopia region Wolaita, Gofa, Gamo, Basketo, Amaro and Gedeo zones and Sidama region zones received light to moderate rainfall. In addition, more than 30 mm of heavy rainfall was recorded over Arjo.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት ለክረምት ዝናብ መፈጠር አመቺ የሆኑ የአየር ሀኔታ ክስተቶች በክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት አከባቢዎች ላይ ቀጣይነት ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከትግራይ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ማዕከላዊ፣ ምስራቅ፣ ደቡብ እና ደቡብ ምስራቅ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ ደቡብ ወሎ እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል፣ ካማሽ ፣አሶሳ እና ማኦ ኮሞ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ ሆሮጉድሩ ወለጋ፣ ሰሜን፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብና ምስራቅ ሸዋ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ባሌ እና ምዕራብ ጉጂ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ከጋምቤላ ክልል የማጃንግ ዞን፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ እና ዳዉሮ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀላባ፣ ሀድያ፣ የየም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ እና ጌዲኦ ዞኖች እና የሲዳማ ክልል ሁሉም ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በባህርዳር እና በአዴት በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በደቡብና በደቡብ ምስራቅ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡
For the coming day, the weather conditions favorable for the formation of Kiremt rainfall will continue over the Kiremt rainfall-benefiting areas of the country. Along with this, from the Tigray region western, northwestern, central, eastern, southern and south eastern zones; from the Amhara region west, north, south and central Gondar, Awi zone, west and east Gojjam, south Wollo and north Shewa zones; from the Benishangul Gumuz region Metekel, Kamash, Asosa and Mao Komo zones; from the Oromia region Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, west and east Wellega, Horro Guduruu Wellega, north, west, south west and east Shewa, Arsi and west Arsi, Bale and west Guji zones; Addis Ababa; from Gambella region Majang zone; from the south west Ethiopia region Bench Sheko, Sheka, Kefa and Dawuro zones; from the central Ethiopia region Gurage, Silte, Halaba, Hadiya, Yem special zone, Kembata and Tembaro zones; from the south Ethiopia region Wolaita and Gedeo zones; all zones of Sidama region receive light to moderate rainfall in many places. In addition, in Bahirdar and Adet will receive heavy rainfall of more than 30 mm in 24 hours. On the other hand, there will be cloud coverage over the south and south east parts of our country.