Daily Weather Report 24 Sep 13
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም የሰሜንና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ፣ ምዕራብ እና ምስራቅ ጎጃም ዞኖች፤ የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ ቡኖ በደሌ፣ ምዕራብና ደቡብ ምዕራብ ሸዋ እና አርሲ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል እና አሶሳ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ ዞን፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሀድያ እና ስልጤ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ እና ዳዉሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ እና ጎፋ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የፋፈን ዞን ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለዉ ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በበደሌ እና በፉኚዶ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, the Kiremt rainfall benefiting parts of the country had cloud coverage. In association with this, the north and central Gondar, Awi, west and east Gojjam zones; Jimma, Ilubabor, Horo Guduru, west and east Wellega, Buno Bedele, west and south west Shewa and Arsi zones; Addis Ababa; from the Benishangul Gumuz region Metekel and Asossa zones; from the Gambella region Agnuwak zone; from the central Ethiopia region Hadiya and Silte zones; from the south west Ethiopia region Bench Sheko, Sheka and Dawuro zones; from the south Ethiopia region, Wolaita and Gofa zones; Sidama region zones and from the Somali region Fafen zone received light to moderate rainfall. In addition, more than 30 mm of heavy rainfall was recorded over Bedele and Fugnido.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት ለክረምት ዝናብ መፈጠር አመቺ የሆኑ የአየር ሀኔታ ክስተቶች በክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት አከባቢዎች ላይ ቀጣይነት ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከትግራይ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ እና ማዕከላዊ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ ደቡብ ወሎ እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል እና ካማሽ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ ሆሮጉድሩ ወለጋ፣ ሰሜን፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብና ምስራቅ ሸዋ፣ ባሌ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ጉጂ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ሐረር፤ ድሬዳዋ፤ ከጋምቤላ ክልል የማጃንግ ዞን፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ እና ዳዉሮ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀላባ፣ ሀድያ፣ የየም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ባስኬቶ፣ ጎፋ፣ ጋሞ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ሁሉም ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የፋፈን ዞን በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በሽሬእንደስላሴ፣ በፀለምት፣ በባህርዳር፣ በዳንግላ፣ በቻግኒ፣ በቡሌን፣ በሰተማ፣ በደዴሳ፣ በሶኮሩ፣ በቀርሳ፣ በዶዶላ፣ በማሻ፣ በለሞ፣ በሳንኩራ፣ በአርቤጎና እና በቡራ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በደቡብና ደቡብ ምስራቅ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡
For the coming day, the weather conditions favorable for the formation of Kiremt rainfall will continue over the Kiremt rainfall-benefiting areas of the country. Along with this, from the Tigray region western, northwestern and central zones; from the Amhara region north, south and central Gondar, Awi zone, west and east Gojjam, south Wollo and north Shewa zones; from the Benishangul Gumuz region Metekel and Kamash zones; from the Oromia region Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, west and east Wellega, Horro Guduruu Wellega, north, west, south west and east Shewa, Bale, Arsi and west Arsi, Guji, west and east Hararge zones; Addis Ababa; Harar; Dire Dawa; from Gambella region Majang zone; from the south west Ethiopia region Bench Sheko, Sheka, Kefa, Konta and Dawuro zones; from the central Ethiopia region Gurage, Silte, Halaba, Hadiya, Yem special zone, Kembata and Tembaro zones; from the south Ethiopia region Wolaita, Basketo, Gofa, Gamo and Gedeo zones; all zones of Sidama region and Somali region Fafen zone receive light to moderate rainfall in many places. In addition, in Shire Endesilase, Tselemt, Bahirdar, Dangila, Chagni, Bulen, Setema, Dedesa, Sokoru, Kersa, Dodola, Masha, Lemmo, Sankura, Arbegona and Bura will receive heavy rainfall of more than 30 mm in 24 hours. On the other hand, there will be cloud coverage over the south and south east parts of our country.