Daily Weather Report 24 Sep 12
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በሰሜን፣ በምዕራብ፣ በመካከለኛው እና በደቡብ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች፤ የጅማ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ ሰሜን፣ ምዕራብና ደቡብ ምዕራብ ሸዋ፣ አርሲ፣ ባሌ፣ ምዕራብ ጉጂ እና ምዕራብ ሐረርጌ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የአሶሳ ዞን፤ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ ዞን፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሀድያ ዞን፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ፣ ኮንታ እና ምዕራብ ኦሞ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ ዞን እና የሲዳማ ክልል ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለዉ ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በቻግኒ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, there was cloud cover in the North, West, Central and South parts of the country. In connection with this, the zones of West, North, South and Central Gondar, West and East Gojam, Awi, North and South Wolo and North Showa; Jimma, Horo Guduru, West and East Wollega, North, West and South West Showa, Arsi, Bale, West Guji and West Hararge zones; Addis Ababa; Asosa zone from Benshangul Gumuz region; Anuwak zone from Gambella region; From the central region of Ethiopia, Hadiya zone; Sheka, Konta and West Omo Zones from Southwest Ethiopia Region; The Wolayta zone and Sidama region of southern Ethiopia received light to moderate rainfall. In addition, more than 30 mm of heavy rainfall was recorded in Chagni.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከትግራይ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ እና ማዕከላዊ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ ደቡብ ወሎ እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል፣ አሶሳ፣ ካማሽ እና ማኦ ኮሞ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ቄለም ወለጋ፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ ሆሮጉድሩ ወለጋ፣ ሰሜን፣ ምዕራብና ደቡብ ምዕራብ ሸዋ፣ ባሌ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ድሬዳዋ፤ ከጋምቤላ ክልል የማጃንግ ዞን፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ እና ዳዉሮ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀላባ፣ ሀድያ፣ የየም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ባስኬቶ፣ ጎፋ፣ ጋሞ እና ጌዲኦ ዞኖች እና የሲዳማ ክልል ሁሉም ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በአለፋ፣ በጃዊ፣ በዳንግላ፣ በሰከላ፣ በካማሽ፣ በሊሙ፣ በጅማ አርጆ፣ በሊሙሴቃ፣ በሶኮሩ፣ በቀርሳ፣ በደዴሳ፣ በዶዶላ፣ በማሻ፣ በየም ልዩ ዞን እና በለሞ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል አልፎ አልፎ ከሚጠናከሩት የአየር ሁኔታ ክስተቶች ላይ በመነሳት በአኙዋክ፣ ጋቢ፣ ጉጂ፣ ፋፈን፣ ምዕራብ እና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡
Tomorrow, there will be cloud cover over the Kiremt rainfall benefiting parts of the country.. In addition, the western, northwestern and central zones of the Tigray region; North, South and Central Gondar, Awi Zone, West and East Gojam, South Wolo and North Showa Zones from Amhara Region; ; Plantation, Asosa, Kamash and Mao Komo zones from Benshangul Gumuz region; From the Oromia region Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, Kelem Welega, West and East Welega, Horogudru Welega, North, West and Southwest Showa, Bale, Arsi and West Arsi zones; Addis Ababa; Dire Dawa; Majang Zone from Gambella Region; Sheka, Kefa, Konta and Dawuro zones from South West Ethiopia region; Gurage, Silte, Halaba, Hadia, Yem Special Zone, Kembata and Tmbaro zones of Central Ethiopia region; All the zones of South Ethiopia region of Wolayta, Basketo, Gofa, Gamo and Gedeo and Sidama region will receive light to moderate rainfall in many places. In addition, Alfa, Jawi, Dangla, Saka, Kamash, Limu, Jimma Arjo, Limouseka, Sokoru, Karsa, Dedesa, Dodola, Masha, Bayem Special Zone and Lemu will receive heavy rainfall of more than 30 mm in 24 hours. On the other hand, light rainfall will occur in Anuwak, Gabi, Guji, Fafen, West and East Hararge zones based on occasional intensifying weather events.