Daily Weather Report 24 Sep 09

Weather Summary for previous day

Sept. 8, 2024

በትናንትናው ዕለት በምዕራብ አጋማሸ፣ በመካከለኛው፣ በደቡብ፣ በሰሜን ምስራቅ እና በምስራቅ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም የሰሜን ምዕራብ ትግራይ ዞን፤ የሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ፣ ደቡብ ወሎ፣ ሰሜን ሸዋ እና ዋግኸምራ ዞኖች፤ የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ ቡኖ በደሌ፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብና ምስራቅ ሸዋ፣ አርሲ እና ምዕራብ ሐረርጌ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ድሬዳዋ፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የአሶሳ እና መተከል ዞኖች፤ ከአፋር ክልል የጋቢ እና ሀሪ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ ዞን፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሀድያ፣ ጉራጌ እና ስልጤ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ እና ኮንታ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ ዞን፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የፋፈን ዞን ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለዉ ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በዳንግላ፣ በቡሬ እና በአርሲነገሌ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, the western half, central, southern, northeastern and eastern parts of the country had cloud coverage. In association to this, north west Tigray zone; north, south and central Gondar, west and east Gojjam, Awi, south Wollo, north Shewa and Waghemra zones; Jimma, Ilubabor, Horo Guduru, west and east Wellega, Buno Bedele, west, south west and east Shewa, Arsi and west Hararge zones; Addis Ababa; Dire Dawa; from the Benishangul Gumuz region Asossa and Metekel zones; from the Afar region Gabi and Hari zones; from the Gambella region Agnuwak zone; from the central Ethiopian region Hadiya, Gurage and Silte zones; from the south west Ethiopia region Bench Sheko, Sheka and Konta zones; from the south Ethiopia region Wolaita zone; Sidama region zones and from Somali region Fafen zone received light to moderate rainfall. In addition, more than 30 mm of heavy rainfall was recorded over Dangila, Bure and Arsinegele.

Weather Forecast for next day

Sept. 10, 2024

በነገው ዕለት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከትግራይ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ማዕከላዊ፣ ደቡብ፣ ደቡብ ምስራቅ እና ምስራቅ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ ሰሜን ወሎ፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን እና ዋግኸምራ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል፣ አሶሳ፣ ካማሽ እና ማኦ ኮሞ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ቄለም ወለጋ፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ ሆሮጉድሩ ወለጋ፣ ሰሜን፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብና ምስራቅ ሸዋ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ባሌ፣ ምዕራብና እና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ሐረር፤ ድሬዳዋ፤ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ እና ከፋ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀላባ፣ ሀድያ፣ የየም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ዳውሮ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ሁሉም ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የፋፈን ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በሁመራ፣ በፀለምት፣ በአድዋ፣ በመተማ፣ በፎገራ፣ በባህርዳር፣ በዳንግላ፣ በቻግኒ፣ በቡለን፣ በወንበራ፣ በካማሽ፣ በሊሙ፣ በጅማ አርጆ፣ በሊሙሴቃ፣ በሶኮሩ፣ በደዴሳ፣ በኖኖ፣ በአመያ፣ በደንዲ፣ በኢሉ፣ በዶዶላ፣ በአርሲነገሌ፣ በቀበና፣ በስልጤ፣ በዳሎቻ እና በወራ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል ከሚጠናከሩት የአየር ሁኔታ ክስተቶች ላይ በመነሳት በጥቂት የጉጂ እና የደቡብ ሶማሌ ደቡባዊ ክፍል ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡

Tomorrow, there will be cloud coverage over the Kiremt rainfall benefitting parts of the country. Along with this, from the Tigray region western, northwestern, central, southern, southeastern and eastern zones; from the Amhara region west, north, south and central Gondar, Awi zone, west and east Gojjam, north and south Wallo, Oromo ethnic special zone, north Shewa and Waghemra Zones; from the Afar region Gabi and Hari zones; from the Benishangul Gumuz region Metekel, Asossa, Kamash and Mao Komo zones; from the Oromia region Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, Kelam Wellega, west and east Wellega, Horo Guduru Wellega, north, west, southwest and east Shewa, Arsi and west Arsi, Bale, west and east Hararge zones; Addis Ababa; Harar; Dire Dawa; from the Gambella region Agnuwak and Majang zones; from the south west Ethiopia region Sheka and Kefa zones; from the central Ethiopian region Gurage, Silte, Halaba, Hadiya, Yem special zone, Kambata and Tembaro Zones; from the south Ethiopia region Wolaita, Dawuro and Gedeo zones; all zones of the Sidama region and Somali region Fafen zone receive light to moderate rainfall in many places. In addition, in Humera, Tselemt, Adwa, Metema, Fogera, Bahirdar, Dangila, Chagni, Bulen, Wanbera, Kamash, Limmu, Jimma Arjo, Limuseka, Sokoru, Dedesa, Nono, Ameya, Dendi, Ilu, Dodola, Arsinegele, Kebena, Silte, Dalocha and Werra will receive heavy rainfall of more than 30 mm in 24 hours. On the other hand, due to the intensifying weather events, a few parts of Guji and southern parts of the Somali region will receive light rainfall.