Daily Weather Report 24 Sep 07
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የደመና ሽፋን እና ክምችት ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም የሰሜን ምዕራብ እና ደቡብ ምስራቅ ትግራይ ዞኖች፤ የሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ሰሜን ሸዋ እና ዋግኸምራ ዞኖች፤ የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ ቡኖ በደሌ፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብና ምስራቅ ሸዋ፣ አርሲ፣ ባሌ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ሐረር፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የአሶሳ ዞን፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሀድያ ዞን እና ከአፋር ክልል የአዉሲ ዞን ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለዉ ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በሞጣ እና በአዲስ አበባ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, Kiremt rainfall benefiting areas of the country had cloud coverage and accumulation. In this regard, the northwest and southeast Tigray zones; north, south and central Gondar, west and east Gojjam, Awi, north and south Wollo, north Shewa and Waghemra zones; Jimma, Ilubabor, Horo Guduru, west and east Wellega, Buno Bedele, west, south west and east Shewa, Arsi, Bale, west and east Hararge zones; Addis Ababa; Harar; from the Benishangul Gumuz region Asossa zone; from the central Ethiopia region Hadiya zone and from the Afar region Awusi zone received light to moderate rains. In addition, more than 30 mm of heavy rain was recorded over Motta and Addis Ababa.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት በምዕራብ አጋማሸ፣ በሰሜን ምስራቅ፣ በመካከለኛው፣ በደቡብ እና በምስራቅ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የደመና ሽፋንና ክምችት ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከትግራይ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ማዕከላዊ፣ ደቡብ፣ ደቡብ ምስራቅ እና ምስራቅ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ሰሜን ሸዋ እና ዋግኸምራ ዞኖች፤ ከአፋር ክልል የጋቢ እና ሀሪ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል፣ አሶሳ፣ ካማሽ እና ማኦ ኮሞ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ቄለም ወለጋ፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ ሆሮጉድሩ ወለጋ፣ ሰሜን፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብና ምስራቅ ሸዋ፣ አርሲ እና ምዕራብ አርሲ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ እና ዳዉሮ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀላባ፣ ሀድያ፣ የየም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ እና ጌዲኦ ዞኖች እና የሲዳማ ክልል ሁሉም ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በዳንሻ፣ በአለፋ፣ በፎገራ፣ በባህርዳር፣ በዳንግላ፣ በቻግኒ፣ በወምበርማ፣ በደንበጫ፣ በቡሬ፣ በደጋዳሞት፣ በደብረኤሊያስ፣ በቡለን፣ በኪረሙ፣ በጊዳአያና፣ በአሙሩ፣ በሱሉላ ፍንጫዓ፣ በግንደበረት፣ በቦንጋ እና በቆቆሳ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል ባስኬቶ፣ ጎፋ፣ ጋሞ፣ ጉጂ፣ ባሌ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ፣ ድሬዳዋ፣ ሐረር፣ ሲቲ እና ፋፈን ዞኖች ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡
Tomorrow, there will be cloud coverage and accumulation over the western half, northeastern, central, southern and eastern parts of the country. Along with this, from the Tigray region western, northwestern, central, southern, southeastern and eastern zones; from the Amhara region west, north, south and central Gondar, Awi zone, west and east Gojjam, north and south Wollo, north Shewa and Waghemra zones; from the Afar region Gabi and Hari zones; from the Benishangul Gumuz region Asosa, Kamash and Mao Komo zones; from the Oromia region Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, Kelam Wellega, west and east Wellega, Horo Guduru Wellega, north, west, southwest and east Shewa, Arsi and west Arsi zones; Addis Ababa; from the Gambella region Agnuwak and Majang zones; from the south west Ethiopia region Sheka, Kefa, Konta and Dawuro zones; from the central Ethiopia region Gurage, Silte, Halaba, Hadiya, Yem special zone, Kambata and Tembaro Zones; from south Ethiopia region Wolaita and Gedeo Zones and all Sidama region zones will receive light to moderate rainfall in many places. In addition, in Dansha, Alefa, Fogera, Bahirdar, Dangila, Chagni, Wemberima, Denbecha, Bure, Degadamot, Debre Elias, Bulen, Kiramu, Gidayana, Amuru, Sulula Fincha’a, Gindeberet, Bonga and Kokosa will receive heavy rainfall of more than 30 mm in 24 hours. On the other hand, Basketo, Gofa, Gamo, Guji, Bale, west and east Hararge, Dire Dawa, Harar, Siti and Fafen zones will have light rainfall.