Daily Weather Report 24 Sep 06

Weather Summary for previous day

Sept. 5, 2024

በትናንትናው ዕለት በምዕራብ አጋማሸ፣ በመካከለኛው እና በሰሜን ምስራቅ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም የሰሜን ምዕራብ ትግራይ ዞን፤ የሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ፣ ደቡብ ወሎ፣ ሰሜን ሸዋ እና ዋግኸምራ ዞኖች፤ የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ ቡኖ በደሌ፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብና ምስራቅ ሸዋ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል እና አሶሳ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ ዞን፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ እና ኮንታ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የሲቲ ዞን ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለዉ ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በአይራ፣ በሊሙገነት እና በማሻ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, the western half, central and northeastern parts of the country had cloud coverage. In relation to this, the northwest Tigray zone; north, south and central Gondar, west and east Gojjam, Awi, south Wollo, north Shewa and Waghemra zones; Jimma, Ilubabor, Horo Guduru, west and east Wellega, Buno Bedele, west, south west and east Shewa zones; Addis Ababa; from the Benishangul Gumuz region Metekel Asossa zones; from the central Ethiopia region Gurage zone; from the south west Ethiopia region Sheka and Konta zones; of Sidama region zones and Somali region Siti zone received light to moderate rainfall. In addition, more than 30 mm of heavy rainfall was recorded over Aira, Limugenet and Masha.

Weather Forecast for next day

Sept. 6, 2024

በነገው ዕለት ወደ ሀገራችን የሚገባው እርጥበት አዘል የአየር ሁኔታ የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ በተመሳሳይ ሁኔታ ይቀጥላሉ፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከትግራይ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ማዕከላዊ፣ ደቡብ፣ ደቡብ ምስራቅ እና ምስራቅ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን፣ ሰሜን ሸዋ እና ዋግኸምራ ዞኖች፤ ከአፋር ክልል የጋቢ እና ሀሪ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል፣ አሶሳ፣ ካማሽ እና ማኦ ኮሞ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ቄለም ወለጋ፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ ሆሮጉድሩ ወለጋ፣ ሰሜን፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብና ምስራቅ ሸዋ፣ አርሲ እና ምዕራብ አርሲ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ድሬዳዋ፤ ሐረር፤ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ፣ ኑዌር እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ እና ዳዉሮ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀላባ፣ ሀድያ፣ የየም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የጌዲኦ ዞን እና የሲዳማ ክልል ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በዳንሻ፣ በሽሬ እንደስላሴ፣ በአድዋ፣ በደባርቅ፣ በጣቁሳ፣ በመተማ፣ በፎገራ፣ በፋርታ፣ በባህርዳር፣ በዳንግላ፣ በቻግኒ፣ በደንበጫ፣ በወምበርማ፣ በቡሬ፣ በጉባ፣ በፓዌ፣ በቡለን፣ በወንበራ፣ በካማሽ፣ ሸርኮሌ፣ በደዴሳ፣ በጅማአርጆ፣ በጎቡሰዮ፣ በሲቡሲሬ፣ በጉቶጊዳ፣ በሆሮ፣ በጊዳአያና፣ በአቤዶንጎሮ፣ በሱሉላ ፍንጫዓ፣ በግንደበረት፣ በጀልዱ፣ በኤጀሬ፣ በደንዲ፣ በሊሙሴቃ፣ በሰተማ እና በማሻ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል ወላይታ፣ ጎፋ፣ ቦረና፣ ጉጂ፣ ባሌ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ፣ ሲቲ፣ ፋፈን እና ሊበን ዞኖች በጥቂት ስፍራዎቻቸው ላይ ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡

Tomorrow, the humid weather that will enter our country will continue in the same condition over the Kiremt rainfall benefiting parts of the country. Along with this, from the Tigray region western, northwestern, central, southern, southeastern and eastern zones; from the Amhara region west, north, south and central Gondar, Awi zone, west and east Gojjam, north and south Wollo, Oromo ethnic special zone, north Shewa and Waghemra zones; from the Afar region Gabi and Hari zones; from the Benishangul Gumuz region Asosa, Kamash and Mao Komo zones; from the Oromia region Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, Kelam Wellega, west and east Wellega, Horo Guduru Wellega, north, west, southwest and east Shewa, Arsi and west Arsi zones; Addis Ababa; Dire Dawa; Harar; from the Gambella region Agnuwak, Nuwer and Majang zones; from the south west Ethiopia region Sheka, Kefa, Konta and Dawuro zones; from the central Ethiopia region Gurage, Silte, Halaba, Hadiya, Yem special zone, Kambata and Tembaro Zones; from the south Ethiopia region Gedeo zone and Sidama region zones will receive light to moderate rainfall in many places. In addition, in Dansha, Shire Endesilase, Adwa, Debark, Takusa, Metema, Fogera, Farta, Bahirdar, Dangila, Chagni, Denbecha, Wemberima, Bure, Guba, Pawe, Bulen, Wanbera, Kamash, Sherkole, Dedesa, Jimma Arjo, Gobuseyo, Sibusire, Gutogida, Horo, Gidayana, Abedongoro, Sulula Fincha’a, Gindeberet, Jeldu, Ejere, Dendi, Limuseka, Setema and Masha will receive heavy rainfall of more than 30 mm in 24 hours. On the other hand, Wolaita, Gofa, Borena, Guji, Bale, west and east Hararge, Siti, Fafen and Liben zones will have light rainfall in some places.