Daily Weather Report 24 Sep 05

Weather Summary for previous day

Sept. 4, 2024

በትናንትናው ዕለት በሰሜን፣ በምዕራብ፣ በደቡብ፣ በመካከለኛው እና በምስራቅ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የደመና ሽፋን እና ክምችት ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም የሰሜን ምዕራብ ትግራይ ዞን፤ የሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ፣ ደቡብ ወሎ፣ ሰሜን ሸዋ እና ዋግኸምራ ዞኖች፤ የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ቄለም፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ ቡኖ በደሌ፣ ሰሜን፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብና ምስራቅ ሸዋ፣ አርሲ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ድሬዳዋ፤ ሐረር፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል እና አሶሳ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ ዞን፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ እና ኮንታ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የፋፈን ዞን ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለዉ ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በአምደወርቅ፣ በአይራ፣ በጭራ፣ በጨለንቆ፣ በማሻ እና በፉኚዶ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, the north, west, south, central and eastern parts of the country had cloud coverage and accumulation. In association with this, the northwest Tigray zone; north, south and central Gondar, west and east Gojjam, Awi, south Wollo, north Shewa and Waghemra zones; Jimma, Ilubabor, Horo Guduru, Kelam, west and east Wellega, Buno Bedele, north, west, south west and east Shewa, Arsi, west and east Hararge zones; Addis Ababa; Dire Dawa; Harar; from the Benishangul Gumuz region Metekel and Asossa zones; from the central Ethiopia region Gurage zone; from the south west Ethiopia region Bench Sheko, Sheka and Konta zones; Sidama region zones and Somali region Fafen zone received light to moderate rainfall. In addition, more than 30 mm of heavy rainfall was recorded over Amdework, Aira, Chira, Chelenko, Masha and Fugnido.

Weather Forecast for next day

Sept. 6, 2024

በነገው ዕለት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከትግራይ ክልል የምዕራብ፣ ማዕከላዊ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ደቡብ ምስራቅ፣ ደቡብ እና ምስራቅ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ሰሜን ሸዋ እና ዋግኸምራ ዞኖች፤ ከአፋር ክልል የጋቢ ዞን፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል፣ አሶሳ፣ ካማሽ እና ማኦ ኮሞ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ቄለም ወለጋ፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ ሆሮጉድሩ ወለጋ፣ ሰሜን፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብና ምስራቅ ሸዋ፣ አርሲ እና ምዕራብ አርሲ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ድሬዳዋ፤ ሐረር፤ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ እና ከፋ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀላባ፣ ሀድያ፣ የየም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች እና የሲዳማ ክልል ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በሽሬ እንደስላሴ፣ በአድዋ፣ በጎንደር፣ በሊቦከምከም፣ በቋራ፣ በጃዊ፣ በቻግኒ፣ በይልማናደንሳ፣ በጉባ፣ በዳንጉር፣ በቡለን፣ በወንበራ፣ ሸርኮሌ፣ በሲቡሲሬ፣ በጉቶጊዳ፣ በኪረሙ፣ በአሙሩ፣ በጉዱሩ፣ በግንደበረት፣ በኤጀሬ፣ በደንዲ፣ በበደሌ፣ በማሻ እና በቀበና በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል ከሚጠናከሩት የአየር ሁኔታ ክስተቶች ላይ በመነሳት በጥቂት የቦረና፤ ጉጂ እና የደቡብ ሶማሌ ደቡባዊ ክፍል ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡

For the coming day, there will be cloud coverage over the Kiremt rainfall-benefiting areas of the country. In line with this, the western, central, northwestern, southeastern, southern and eastern zones of the Tigray region; from the Amhara region west, north, south and central Gondar, west and east Gojjam, north and south Wollo, north Shewa and Waghemra Zones; from the Afar region Gabi zone; from the Benishangul Gumuz region, Asossa, Kamash, Metekel and Mao Komo and zones; from the Oromia region Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, Kelam Wellega, west and east Wellega, Horo Guduru Wellega, north, west, southwest and east Shewa, Arsi and west Arsi zones; Addis Ababa; Dire Dawa; Harar; from the Gambella region Agnuwak and Majang zones; from the south west Ethiopia region Bench Sheko, Sheka and Kefa zones; from the central Ethiopia region Gurage, Silte, Halaba, Hadiya, Yem special zone, Kambata and Tembaro Zones and Sidama region Zones will receive light to moderate rainfall in many places. In addition, in Shire Endesilase, Adwa, Gondar, Libokemkem, Quara, Jawi, Chagni, Yilmanadensa, Guba, Dangur, Bulen, Wanbera, Sherkole, Sibusire, Gobuseyo, Gutogida, Kiramu, Amuru, Sulula Fincha’a, Guduru, Gindeberet, Ejere, Dandi, Bedele, Masha and Kebena will receive heavy rainfall of more than 30 mm in 24 hours. On the other hand, due to the intensifying weather events a few Borena, Guji and south Somali region southern part will receive light rainfall.