Daily Weather Report 24 Sep 03

Weather Summary for previous day

Sept. 2, 2024

በትናንትናው ዕለት በሰሜን፣ በምዕራብ፣ በሰሜን ምስራቅ፣ በመካከለኛው፣ በደቡብ እና በምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን እና ክምችት ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር የሰሜን ምዕራብ፣ ማዕከላዊ፣ ደቡብ ምስራቅና ምስራቅ ትግራይ ዞኖች፤ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ሰሜን ሸዋ እና ዋግኸምራ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ ቡኖ በደሌ፣ ሰሜን፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብና ምስራቅ ሸዋ፣ ባሌ፣ አርሲ፣ ምዕራብ ሐረርጌ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል እና አሶሳ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የከፋ እና ኮንታ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሀድያ እና ስልጤ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የጎፋ፣ ወላይታ እና ደቡብ ኦሞ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የቆራሔ ዞን ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለዉ ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በዳንግላ፣ በቻግኒ እና በተርጫ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, the north, west, northeast, central, south and east parts of the country had cloud coverage and accumulation. In association with this, the north west, central, south east and east Tigray zones; north, south and central Gondar, west and east Gojjam, Awi, north and south Wollo, north Shewa and Waghemra zones; from the Oromia region Jimma, Ilubabor, Horo Guduru, west and east Wellega, Buno Bedele, north, west, south west and east Shewa, Bale, Arsi, west Hararge zones; Addis Ababa; from Benshangul Gumuz region Metekel and Asossa zones; from the south west Ethiopia region Kefa and Konta zones; from the central Ethiopia region Hadiya and Silte zones; from the South Ethiopia region Gofa, Wolaita and south Omo zones; Sidama region zones and Somali region Korahe zone received light to moderate rainfall. In addition, more than 30 mm of heavy rainfall was recorded over Dangila, Chagni and Tercha.

Weather Forecast for next day

Sept. 4, 2024

በነገው ዕለት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የተስፋፋ የደመና ሽፋንና ክምችት ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከትግራይ ክልል የምዕራብ፣ ማዕከላዊ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ደቡብ ምስራቅ፣ ደቡብ እና ምስራቅ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ ዞን፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን፣ ሰሜን ሸዋ እና ዋግኸምራ ዞኖች፤ ከአፋር ክልል የቂልበቲ፣ ጋቢ፣ አዉሲ እና ሀሪ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል፣ አሶሳ ካማሽ እና ማኦ ኮሞ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ቄላም ወለጋ፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ ሆሮጉድሩ ወለጋ፣ ሰሜን፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብና ምስራቅ፣ ሸዋ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ምስራቅ ቦረና፣ ባሌ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ምዕራብ እና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ድሬዳዋ፤ ሐረር፤ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ እና ዳዉሮ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀላባ፣ ሀድያ፣ የየም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ሁሉም ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የሲቲ እና ፋፈን ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በአድዋ፣ በደንቢያ፣ በጎንደር ዙሪያ፣ በሊቦከምከም፣ በአለፋ፣ በዳንግላ፣ በአሶሳ፣ በጋዎቀቤ፣ በዲጋ፣ በጉቶጊዳ፣ በጅማአርጆ፣ በሲቡሲሬ፣ በሰዮ፣ በሊሙ፣ በአቤዶንጎሮ፣ በሆሮ፣ በጅማራሬ፣ በባኮጢቤ፣ ግንደበረት፣ በዳኖ፣ በሶኮሩ፣ በጨዋቃ እና በቸሃ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በደቡብና ደቡብ ምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ ከሚጠናከሩት የአየር ሁኔታ ክስተቶች በመነሳት ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡

Tomorrow, there will be widespread cloud coverage and accumulation over the Kiremt rainfall benefiting parts of the country. In line with this, the western, central, northwestern, southeastern, southern and eastern zones of the Tigray region; from the Amhara region west, north, south and central Gondar, Awi zone, west and east Gojjam, north and south Wollo, north Shewa and Waghemra zones; from the Benshangul Gumuz region, Metekel, Asossa, Kamash and Mao Komo zones; from the Oromia region Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, Kelam Wellega, west and east Wellega, Horo Guduru Wellega, north, west, south west and east, Shewa, Guji and west Guji, east Borena, Bale, Arsi and west Arsi, west and east Hararge zones; Addis Ababa; Dire Dawa; Harar; Agnuwak and Majang zones from the Gambella region; from the south west Ethiopia region Bench Sheko, Sheka, Kefa, Konta and Dawuro zones; from the central Ethiopia region Gurage, Silte, Halaba, Hadiya, Yem special zone, Kambata and Tembaro zones; from the south Ethiopia region Wolaita, Gofa, Basketo and Gedeo zones; all zones of Sidama region and Somali region Siti and Fafen zones will receive light to moderate rainfall in many places. In addition, in Adwa, Denbia, Gondar Zuria, Libokemkem, Alefa, Dangila, Asossa, Gawokebe, Digga, Gutogida, Jimma Arjo, Sibusire, Sayo, Limmu, Abedongoro, Horo, Jimma Rare, Bakotibe, Gindeberet, Dano, Sokoru, Chewaka and Cheha will receive heavy rainfall of more than 30 mm in 24 hours. On the other hand, due to the intensifying weather events the south and southeast areas of the country will receive light to moderate rainfall.