Daily Weather Report 24 Sep 02

Weather Summary for previous day

Sept. 1, 2024

በትናንትናው ዕለት በሰሜን ምዕራብ፣ በምዕራብ፣ በሰሜን ምስራቅ፣ በመካከለኛው፣ በደቡብ እና በምስራቅ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን እና ክምችት ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም የማዕከላዊ፣ ደቡብና ደቡብ ምስራቅ ትግራይ ዞኖች፤ ሰሜንና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ሆሮ ጉዱሩ ፣ ቄለም፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ ቡኖ በደሌ፣ ሰሜን፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብና ምስራቅ ሸዋ፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ፣ ቦረና፣ አርሲ፣ ምዕራብ እና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ሐረር፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል፣ ካማሽ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ እና ማጃንግ ዞኖች ፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ኮንታ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሀድያ፣ ስልጤ እና ጉራጌ ዞኖች እና ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የጋሞ፣ ጎፋ እና ወላይታ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለዉ ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በአፅቢ፣ አምደ ወርቅ፣ ደብረታቦር፣ ደብረወርቅ፣ ኮምቦልቻ፣ የትኖራ፣ አርጆ፣ ፉኝዶ፣ ጅማ እና ወላይታ ሶዶ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, there was cloud cover and accumulation in the North West, West, North East, Central, South, and East areas of our country. In connection with this, the central, southern and southeastern Tigray zones; North and Central Gondar, West and East Gojam, Awi, North and South Wolo, Oromo Special Zone and North Showa Zones; From the Oromia region, Jimma, Ilubabor, Horo Guduru, Kelem, West and East Welega, Buno Bedele, North, West, South West and East Showa, Bale and East Bale, Borena, RC, West and East Hararge zones; Addis Ababa; Harar; From Benshangul Gumuz Region Plantation, Kamash Zones; Anuwak and Majang zones from Gambella region; from the Sheka, Bench Sheko, West Omo and Konta zones of South West Ethiopia; Hadia, Silte and Gurage zones of central Ethiopia and Gamo, Gofa and Wolayta zones of southern Ethiopia received light to moderate rainfall. In addition, more than 30 mm of heavy rain was recorded in Atsibi, Amde Work, Debre tabor, Debrework, Kombolcha, Yetnora, Arjo, Fugnido, Jimma and Wolayta Sodo.

Weather Forecast for next day

Sept. 3, 2024

በነገው ዕለት ወደ ሀገራችን የሚገባው እርጥበት አዘል የአየር ሁኔታ በምዕራብ አጋማሸ፣ በመካከለኛው፣ በሰሜን ምስራቅ እና በምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ ተጠናክረው ይቀጥላሉ፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከትግራይ ክልል የምዕራብ፣ ማዕከላዊ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ደቡብ ምስራቅ፣ ደቡብ እና ምስራቅ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ ዞን፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ሰሜን ሸዋ እና ዋግኸምራ ዞኖች፤ ከአፋር ክልል አውሲ፣ ሀሪ እና ጋቢ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የአሶሳ፣ ካማሽ፣ መተከል እና ማኦ ኮሞ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ምዕራብ እና ምስራቅ ወለጋ፣ ቄላም ወለጋ፣ ሆሮጉድሩ ወለጋ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ምስራቅ፣ ሰሜንና ምዕራብ ሸዋ፣ ባሌ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ሐረር፤ ድሬዳዋ፤ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ሸካ እና ከፋ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀላባ እና ሀድያ ዞኖች እና የሲዳማ ክልል ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በአዴት፣ ሰከላ፣ ደጋ ዳሞት፣ ደ/ታቦር፣ ፎገራ፣ ደራ፣ ሐሙሲት፣ መኮ፣ በደሌ፣ ቦረቻ፣ ደዴሳ፣ ጮራ፣ መቱ ሰቃ፣ ኢሉ ገላን፣ አዳ በርጋ፣ ኤጀሬ፣ ግንደበረት እና ወልቂጤ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ የሚያገኙ ሲሆን፤ የሶማሌ ክልል ሊበን እና ዳዋ ዞኖች ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡ በሌላ በኩል አልፎ አልፎ ከሚጠናከሩት የአየር ሁኔታ ክስተቶች ላይ በመነሳት በደቡብና ደቡብ ምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡

Tomorrow the humid weather that will enter our country tomorrow will continue to strengthen in the western half, central, northeastern and eastern parts of the country. In addition, the western, central, northwestern, southeastern, southern and eastern zones of the Tigray region; West, North, South and Central Gondar, West and East Gojam, Awi Zone, North and South Wolo, North Showa and Waghemra Zones of Amhara Region; Awusi, Hari and Gabi zones of the Afar region; Asosa, Kamash, Metkel and Mao Komo zones from Benshangul Gumuz region; From the Oromia region, Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, West and East Welega, Kelam Welega, Horogudru Welega, Southwest, East, North and West Showa, Bale, Arsi and West Arsi zones; Addis Ababa; Harar; Dire Dawa; Anuwak and Majang zones from Gambella region; Sheka and Kefa zones of South West Ethiopia region; Gurage, Silte, Halaba and Hadia zones of Central Ethiopia region and Sidama region zones will receive light to moderate rainfall in many places. Also in Adet, Sekala, Dega Damot, De/Tabor, Fogera, Dera, Hamusit, Meko, Dele, Borecha, Dedesa, Chora, Metu Zaka, Ilu Galan, Ada Berga, Ejere, Gandaberet and Wolkite more than 30 mm in 24 hours. When they receive heavy rainfall; Liban and Dawa zones of Somali region will have light rainfall. On the other hand, depending on the occasional strong weather events, there will be light amount of rain in the south and southeast areas of the country.