Daily Weather Report 24 Sep 01

Weather Summary for previous day

Sept. 30, 2024

በትናንትናው ዕለት በሰሜን፣ በምዕራብ፣ በመካከለኛው፣ በደቡብ እና በምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም የሰሜን ምዕራብ ትግራይ ዞን፤ የሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ ደቡብ ወሎ እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች፤ የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ ምዕራብና ደቡብ ምዕራብ ሸዋ፣ ባሌ፣ አርሲ፣ ምዕራብ ጉጂ፣ ምዕራብ ሐረርጌ፣ ቦረና እና ምስራቅ ቦረና ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል ዞን፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሀድያ ዞን፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ ዞን፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የቡርጂ፣ ኮንሶ እና ደቡብ ኦሞ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የፋፈን ዞን ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለዉ ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በሀዋሳ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, there was cloud coverage over the north, west, central, south and east parts of the country. In association with this, the north west Tigray zone; north, south and central Gondar, Awi, west and east Gojjam, south Wollo and north Shewa zones; Jimma, Ilubabor, Horo Guduru, west and east Wellega, west and south west Shewa, Bale, Arsi, west Guji, west Hararge, Borena and east Borena zones; Addis Ababa; from the Benshangul Gumuz region Metekel zone; from the central region Ethiopia Hadiya zone; from the south west Ethiopia region Bench Sheko zone; from the south Ethiopia region Burji, Konso and south Omo zones; zones of Sidama region and Fafen zone of Somali region received light to moderate rainfall. In addition, more than 30 mm of heavy rainfall was recorded over Hawasa.

Weather Forecast for next day

Oct. 2, 2024

በነገው ዕለት ዝናብ በምዕራብ፣ በሰሜን ምስራቅ፣ በመካከለኛው፣ በምስራቅ፣ በደቡብ እና ደቡብ ምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ ጠንካራ የደመና ሽፋንና ክምችት ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከትግራይ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ማዕከላዊ እና ደቡብ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ምዕራብ እና ምስራቅ ጎጃም፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል፣ ካማሽ፣ አሶሳ እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከአፋር ክልል የጋቢ፣ አዉሲ እና ሀሪ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ቄለም፣ ምዕራብና ምስራቅ እና የሆሮጉድሩ ወለጋ ዞኖች፣ ሰሜን፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብና ምስራቅ ሸዋ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ፣ ቦረና እና ምስራቅ ቦረና ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ሐረር፤ ድሬዳዋ፣ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ፣ ኑዌር፣ ኢታንግ እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳዉሮ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀላባ፣ ሀድያ፣ የየም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጎፋ፣ ጋሞ፣ ባስኬቶ፣ አማሮ፣ ደራሸ፣ ኮንሶ፣ ቡርጂ፣ ደቡብ ኦሞ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ሁሉም ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የሲቲ፣ ፋፈን፣ ጃራር፣ ኤሬር እና ኖጎብ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በቋራ፣ በቻግኒ፣ በዳንግላ፣ በጃዊ፣ በአቸፈር፣ በፓዌ፣ በቡሌን፣ በካማሽ፣ በሊሙ፣ በሳሲጋ፣ በጉቶጊዳ፣ በሲቡሲሬ፣ በአቤዶንጎሮ፣ በቤጊ፣ በነጆ፣ በአይራ፣ በጊምቢ፣ በጨዋቃ፣ በበደሌ፣ በአሌ፣ በጎማ፣ በቀርሳ፣ በሊሙሴቃ፣ በማሻ፣ በሸኮ፣ በገሻ፣ በደቻ፣ በኮንታ እና በተርጫ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡

For the coming day, there will be strong cloud coverage and accumulation over the west, north east, central, east, south and south east parts of the country. Along with this, from the Tigray region west, north west, central and south zones; from the Amhara region west, north, south and central Gondar, Awi zone, west and east Gojjam, north and south Wollo and north Shewa zones; from the Benishangul Gumuz region Metekel, Kamashi, Asossa and Mao Komo zones; from the Oromia region Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, Kelam, west and east and Horo Guduru Wellega zones, north, west, south west and east Shewa, Arsi and west Arsi, Guji and west Guji, Bale and east Bale, west and east Hararge, Borena and east Borena zones; Addis Ababa; Harar; Dire Dawaa; from the Gambella region Agnuwak, Nuwer, Itang and Majang zones; from the south west Ethiopia region Bench Sheko, Sheka, Kefa, Konta, west Omo and Dawuro zones; from the central Ethiopia region Gurage, Silte, Halaba, Hadiya, Yem special zone, Kambata and Tembaro zones; from the south Ethiopia region Walaita, Gofa, Gamo, Basketo, Amaro, Derashe, Konso, Burji, south Omo and Gedeo zones; all the zones of Sidama region and from Somali region of Siti, Fafen, Jarar, Erer and Nogob zones will receive light to moderate rainfall in many places. In addition, Quara, Chagni, Dangila, Jawi, Achefer, Pawe, Bulen, Kamash, Limmu, Sasiga, Gutogida, Sibusire, Abedongoro, Begi, Nedjo, Aira, Gimbi, Chewaka, Bedele, Ale, Gomma, Kersa, Limuseka, Masha, Sheko, Gesha, Decha, Konta and Tercha will receive more than 30 mm of heavy rain in 24 hours.