Daily Weather Report 24 Oct 31
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በትግራይ፤ በአማራ፤ በቤንሻንጉል ጉሙዝ፤ በኦሮሚያ፤ በደቡብ ምዕራብ፣ ማዕከላዊና ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል እና በምስራቅ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የተጠናከረና የተስፋፋ የደመና ሽፋንና ክምችት ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም የሰሜን ምዕራብ፣ ማዕከላዊ፣ ደቡብ፣ ደቡብ ምስራቅ እና ምስራቅ ትግራይ ዞኖች፤ የሰሜን፣ ደቡብ እና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ ዋግኸምራ፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን፣ ሰሜን እና ደቡብ ወሎ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል እና አሶሳ ዞኖች፤ የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ቄለም፣ ሆሮጉድሩ፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ ሰሜን፣ ምዕራብና ደቡብ ምዕራብ ሸዋ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ምዕራብ ጉጂ፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ፣ ምስራቅ ቦረና፣ ምዕራብ እና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የምዕራብ ኦሞ እና ዳዉሮ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የስልጤ እና ሀድያ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ ቡርጂ እና ደቡብ ኦሞ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የጃራር እና ፊቅ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን (1-29 ሚ.ሜ) ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በአዲግራት፣ በሽሬእንደስላሴ፣ በባህርዳር፣ በቻግኒ፣ በቡኢ፣ በባቱ፣ በጅማ፣ በሆሳዕና፣ በአርባ ምንጭ እና በአዋሮ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, Tigray; Amhara, Benishangul Gumuz; Oromia, the southwestern, central and south Ethiopian regions and the eastern parts of the country had strong and widespread cloud coverage and accumulation. In line with this, the north west, central, south, south east and east Tigray zones; north, south and central Gondar, Awi zone, west and east Gojjam, Waghemra, Oromo special zone, north and south Wollo zones; Metekel and Asossa zones from Benishangul Gumuz region; Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, Kelam, Horo Guduru, west and east Wellega, north, west and south west Shewa, Arsi and west Arsi, west Guji, Bale and east Bale, east Borena, west and east Hararge zones; Addis Ababa; west Omo and Dawuro zones from south west Ethiopia region; from the central Ethiopian region Silte and Hadiya zones; from the south Ethiopia region Walaita, Gamo, Gofa Burji and south Omo zones; zones of Sidama region and from Somali region Jarar and Fiq zones received light to moderate rainfall (1-29 mm). In addition, more than 30 mm of heavy rainfall was recorded over Adigrat, Shire Endesilase, Bahirdar, Chagni, Bui, Batu, Jimma, Hosaina, Arba Minch and Awaro.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በደቡብና ደቡብ ምስራቅ የሀገራችን አከባቢዎች እና በምዕራብና በደቡብ ምዕራብ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ ጠንካራ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ በሌላ በኩል በፀሀይ ኃይል ታግዘው ከሚፈጠሩት የአየር ሁኔታ ክስተቶች ላይ በመነሳት በሰሜን ምዕራብ እና በምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይም የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የምዕራብ አርሲ፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ፣ ምስራቅ ቦረና፣ ጉጂ እና ምዕራብ ጉጂ ዞኖች እንዲሁም የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ቄለም፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ምዕራብ እና ምስራቅ ወለጋ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ እና ዳዉሮ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል፣ ካማሽ እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ኮንሶ፣ ቡርጂ፣ አማሮ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ እና ማጃንግ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የዳዋ፣ ሊበን፣ አፍደር፣ ሸበሌ፣ ቆራሔ፣ ኖጎብ፣ ዶሎ፣ ኤሬር እና ጃራር ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን (1-29 ሚ.ሜ) ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በሁመራ፣ በወልቃይት፣ በፀገደ፣ በመተማ፣ በጃዊ፣ በዳንግላ፣ በባኮቲቤ፣ በኖኖ፣ በቡሬ፣ በደዴሳ፣ በሰተማ፣ በጎማ፣ በጌራ፣ በቀርሳ፣ በሊሙቆሳ፣ በአርሲነገሌ፣ በኮፋሌ፣ በኮኮሳ፣ በዶዶላ፣ በባሌ፣ በጎባ፣ በባቢሌ፣ በቸሃ፣ በቀበና፣ በዳሎቻ፣ በሳንኩራ፣ በለሞ፣ በጊቤ፣ በሶሮ፣ በጠምባሮ፣ በባዳዋቾ፣ በካቻብራ፣ በዳሞትሶሬ፣ በክንዶኮይሻ፣ በቦሎሶ ሶሬ፣ በተርጫ፣ በቁጫ፣ በሐዋሳ ዙሪያ፣ በብላቴ፣ በወንዶገነት፣ በገሻ፣ በቀብሪዳሃር እና በሽላቦ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል ከሚጠናከሩት የአየር ሁኔታ ክስተቶች ላይ በመነሳት በሽራሮ፣ በሽሬእንደስላሴ፣ በፀለምት፣ በአድርቃይ፣ በደባርቅ፣ በአርማጮ፣ በአቸፈር፣ በደምቢያ፣ በአለፋ፣ በጣቁሳ፣ በፎገራ፣ በባህርዳር፣ በይልማናደንሳ፣ በሜጫ፣ በደንበጫ፣ በደጋዳሞት፣ በወምበርማ፣ በደብረኤሊያስ፣ በጉዛማን፣ በደጀን፣ በወረጃርሶ፣ በገርባጉራቻ፣ በግንደበረት፣ በጀልዱ፣ በአምቦ፣ በደንዲ፣ በሜታሮቢ፣ በአመያ፣ በወንጪ፣ በወሊሶ፣ በቶሌ፣ በቡታጂራ፣ በሰበታሓዋስ፣ በአዲስ አበባ፣ በቢሾፍቱ፣ በአዳማ፣ በአዳሚቱሉ፣ በሙኔሳ፣ በሮቤ፣ በመርቲ፣ በአሰኮ፣ በአንቻር፣ በጎሎልቻ፣ በጠና፣ በዶዶታ፣ በሴሩ፣ በጮሌ፣ በቦኬ፣ በቡርቃ፣ በጭሮ፣ በግራዋ፣ በፌዲስ፣ በኩርፋጨሌ፣ በሐሮማያ፣ በሐረር እና በሐሮረየስ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ ያገኛሉ፡፡ ስለሆነም ማህበረሰቡ የደረሱ ሰብሎችን እንዲሰበስብ ሲል የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ይጠቁማል፡፡
Tomorrow, there will be strong cloud coverage in our country's south and southeast areas, which are the second rainy season of the Bega and the west and southwest parts of the country. In contrast, due to the weather events triggered by solar energy, there will be cloud coverage over the northwestern and eastern of parts the country. Along with this, from the Oromia region west Arsi, Bale, east Bale, east Borena, Guji, and west Guji zones as well as Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, Kelam, Horo Guduru, west and east Wellega zones; from the south west Ethiopia region Bench Sheko, Sheka, Kefa, Konta and Dawuro zones; Metekel, Kamashi and Mao Komo zones from Benishangul Gumuz region; from the south Ethiopia region Walaita, Gamo, Gofa, Basketo, Konso, Burji, Amaro and Gedeo zones; Agnuwak and Majang zones from Gambella region; Sidama region zones and from Somali region Dawa, Liban, Afder, Shebelle, Korahe, Nogob, Dollo, Erer and Jarar zones will receive light to moderate rainfall (1-29 mm) in many places. Additionally, Humera, Welkait, Tsegede, Metema, Jawi, Dangila, Bakotibe, Nono, Bure, Dedesa, Setema, Gomma, Gera, Kersa, Limmukosa, Arsinegelle, Kofale, Kokosa, Dodola, Bale, Goba, Babile, Cheha, Kebena, Dalocha, Sankura, Lemmo, Gibe, Soro, Tembaro, Badawacho, Kachabira, Damotsore, Kindokoisha, Boloso Sore, Tercha, Kucha, Hawasa Zuria, Bilate, Wendogenet, Gesha, Kebridahar and Shilabo will receive heavy rainfall of over 30 mm in 24 hours. On the other hand, due to the intensifying weather events, Shiraro, Shire Endesilase, Tselemt, Adirkay, Debark, Armacho, Achefer, Dembiya, Alefa, Takusa, Fogera, Bahirdar, Yilmanadensa, Mecha, Denbecha, Degadamot, Wemberima, Debre Elias, Guzman, Dejen, Werra Jarso, Gerba Guracha, Gindeberet, Jeldu, Ambo, Dendi, Meta Robi, Ameya, Wenchi, Waliso, Tole, Buta Jira, Sebeta Hawas, Addis Ababa Bishoftu, Adama, Adami Tulu, Munesa, Robe, Merti, Aseko, Anchar, Gololcha, Tena, Dodota, Seru, Chole, Boke, Burka, Chiro, Girawa, Fedis, Kurfachele, Haromaya, Harar and Haroreyes will receive light to moderate unseasonal rainfall. Therefore, the Ethiopian Meteorological Institute suggests that the community collect the ripe crops.