Daily Weather Report 24 Oct 29
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት ደባርቅ፣ መተማ፣ ደብረታቦር፣ ቻግኒ፣ ባህርዳር፣ ሞጣ፣ አየሁ፣ ደብረወርቅ፣ የትኖራ፣ ኤሊዳር፣ ቡለን፣ አሶሳ፣ ጋምቤላ፣ ደንብዶሎ፣ ቡሬ፣ ጎሬ፣ ነጆ፣ አይራ፣ ጊምቢ፣ ነቀምቴ፣ ሻምቡ፣ አደሌ፣ ደሎመና፣ ገለምሶ፣ ቦሬ፣ ማሻ፣ ተርጫ፣ ሐዋሳ፣ ቢላቴ፣ ዲላ፣ ወላይታ ሶዶ፣ አርባ ምንጭ፣ ምዕራብ አባያ፣ ጂንካ፣ ኮንሶ እና ቡርጂ የደመና ሽፋን የነበራቸው ሲሆን ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በአርጆ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, Debark, Metema, Debretabor, Chagni, Bahirdar, Mota, Ayehu, Debrework, Yetnora, Elidar, Bullen, Asossa, Gambella, Denbidollo, Bure, Gore, Nedjo, Aira, Gimbi, Nekemte, Shambu, Adele, Delomanna, Gelemso, Bore, Masha, Tercha, Hawassa, Bilate, Dilla, Walaita Sodo, Arba Minch, Mirab Abaya, Jinka, Konso and Burji had cloud cover and also received light to moderate rainfall. More than 30 mm of heavy rainfall was recorded over Arjo.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በደቡብና ደቡብ ምስራቅ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን የሚኖራቸው ሲሆን፤ በምዕራብ፣ በደቡብ ምዕራብ፣ በሰሜን ምዕራብ እና በምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ ጠንካራ የደመና ክምችት ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የምዕራብ አርሲ፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረና እና ምስራቅ ቦረና ዞኖች እንዲሁም የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ቄለም፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ምዕራብ እና ምስራቅ ወለጋ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳዉሮ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል፣ አሶሳ፣ ካማሽ እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ኮንሶ፣ ቡርጂ፣ አማሮ፣ ደቡብ ኦሞ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ፣ ኑዌር እና ማጃንግ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የዳዋ፣ ሊበን፣ አፍደር፣ ሸበሌ፣ ቆራሔ፣ ኖጎብ፣ ኤሬር እና ጃራር ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን (1-29 ሚ.ሜ) ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በጃዊ፣ በቡለን፣ በዳንጉር፣ በወንበራ፣ በአሶሳ፣ በነጆ፣ በጊምቢ፣ በሊሙ፣ በጊዳአያና፣ በአቤዶንጎሮ፣ በአሙሩ፣ በሱሉላ ፍንጫዓ፣ በበደሌ፣ በሰተማ፣ በሶኮሩ፣ የየም ልዩ ዞን፣ በለሞ፣ በካቻብራ፣ በዶዶላ፣ በአዳባ፣ በጎባ፣ በባሌ፣ በግራዋ፣ በኩርፋጨሌ፣ በፌዲስ፣ በባቢሌ፣ በደጋሃቡር፣ በአዋሮ እና በዳሮር በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል ከሚጠናከሩት የአየር ሁኔታ ክስተቶች ላይ በመነሳት በሽሬእንደስላሴ፣ በወልቃይት፣ በዳንሻ፣ በመተማ፣ በደባርቅ፣ በአይከል፣ በደምቢያ፣ በአለፋ፣ በፎገራ፣ በባህርዳር በቻግኒ፣ በዳንግላ፣ በሰከላ፣ በደጋዳሞት፣ በወምበርማ፣ በባኮቲቤ፣ በኖኖ፣ በግንደበረት፣ በጀልዱ፣ በአምቦ፣ በኤጀሬ፣ በአዲስ አበባ፣ በአመያ፣ በወንጪ፣ በወሊሶ፣ በአዳሚቱሉ፣ በጎሎልቻ፣ በጠና፣ በዶዶታ፣ በጮሌ፣ በቦኬ፣ በቡርቃ፣ በጭሮ፣ በሐሮማያ፣ በሐረር፣ በደደር፣ በጉርሱም፣ በሐሮረየስ፣ በቸሃ፣ በቀበና፣ በስልጤ እና በወራ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ ያገኛሉ፡፡
Tomorrow, there will be cloud coverage in our country's south and southeast areas, which are the second rainy season of the Bega. Also, there will be strong cloud accumulation over the western, southwestern, northwestern and eastern parts of the country. Along with this, from the Oromia region west RC, Bale and east Bale, Guji and west Guji, Borena and east Borena zones as well as Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, Kelam, Horo Guduru, west and east Wellega zones; from south west Ethiopia region Bench Sheko, Sheka, Kefa, Konta, west Omo and Dawuro zones; from Benishangul Gumuz region Metekel, Asossa, Kamashi and Mao Komo zones; from the south Ethiopia region Walaita, Gamo, Gofa, Basketo, Konso, Burji, Amaro, south Omo and Gedeo zones; from Gambella region Agnuwak, Nuwer and Majang zones; Sidama region zones and from Somali region Dawa, Liban, Afder, Shebelle, Korahe, Nogob, Erer and Jarar zones will receive light to moderate rainfall (1-29 mm) in many places. In addition, Jawi, Bullen, Dangur, Wanbera, Asossa, Nedjo, Gimbi, Limmu, Gidayana, Abedongoro, Amuru, Sulula Fincha’a, Bedele, Setema, Sokoru, Yem Special Zone, Lemo, Kachabira, Dodola, Adaba, Goba, Bale, Girawa, Kurfachele, Fedis, Babile, Degahabur, Awaro and Daror will receive heavy rainfall of more than 30 mm in 24 hours. On the other hand, due to the intensifying weather events, Shire Endesilase, Welkait, Dansha, Metema, Debark, Ayikel, Dembiya, Alefa, Fogera, Bahirdar, Chagni, Dangila, Sekela, Degadamot, Wemberima, Bakotibe, Nono, Gindeberet, Jeldu, Ambo, Ejere, Addis Ababa, Ameya, Wenchi, Waliso, Adamitulu, Gololcha, Tena, Dodota, Chole, Boke, Burka, Chiro, Haromaya, Harar, Deder, Gursum, Haroreyes, Cheha, Kebena, Silte and Wara will experience light to moderate unseasonal rain. .