Daily Weather Report 24 Oct 27

Weather Summary for previous day

Oct. 26, 2024

በትናንትናው ዕለት በደቡብ እና በደቡብ ምስራቅ እንዲሁም በሰሜን ምዕራብ፣ በምዕራብ በደቡብ ምዕራብ እና በመካከለኛው የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም ሐዋሳ፣ ብላቴ፣ ዲላ፣ ወላይታ ሶዶ፣ አርባ ምንጭ፣ ሳዉላ፣ ጂንካ፣ ተርጫ፣ ወራቤ፣ ሆሳዕና፣ ቦሬ፣ ያቤሎ፣ ቡሌሆራ፣ ባሌሮቤ፣ ዶሎዶ፣ ደባርቅ፣ መተማ፣ አይከል፣ ጎንደር፣ ደብረታቦር፣ ነፋስመዉጫ፣ ባህርዳር፣ አዴት፣ ሞጣ፣ ዳንግላ፣ ደብረማርቆስ፣ ደብረወርቅ፣ የትኖራ፣ ኮምቦልቻ፣ አሶሳ፣ ቡለን፣ ጋምቤላ፣ ነጆ፣ ሻምቡ፣ ነቀምቴ፣ ጎሬ፣ ቡሬ፣ ጅማ፣ ካቺሴ፣ ኢጃጂ፣ ቢሾፍቱ፣ አዳማ፣ ኑራኤራ፣ ቡኢ፣ ኩሉምሳ፣ አቦምሳ፣ አርሲሮቤ፣ ገለምሶ፣ ሂርና፣ ገርቦ እና አዋሽ አርባ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን (1-29 ሚ.ሜ) ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በማሻ እና በጎዴ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday there was cloud coverage over the south and southeast as well as in the country's northwest, west, southwest and central parts. In line with this, Hawasa, Bilate, Dilla, Walaita Sodo, Arba Minch, Sawula, Jinka, Tercha, Werabe, Hosaina, Bore, Yabelo, Bulehora, Balerobe, Dolodo, Debark, Metema, Ayikel, Gondar, Debretabor, Nefasmewuca, Bahirdar, Adet, Mota, Dangila, Debremarkos, Debrework, Yetnora, Kombolcha, Asossa, Bullen, Gambella, Nedjo, Shambu, Nekemte, Gore, Bure, Jimma, Kachise, Ijaji, Bishoftu, Adama, Nuraera, Bui, Kulumsa, Abomsa, Arsirobe, Gelemso, Hirna, Gerbo and Awash Arba received light to moderate rainfall (1-29 mm). More than 30 mm of heavy rain was recorded over Masha and Gode.

Weather Forecast for next day

Oct. 28, 2024

በነገው ዕለት በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በደቡብና ደቡብ ምስራቅ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን የሚኖራቸው ሲሆን፤ በምዕራብ እና በደቡብ ምዕራብ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ ደግሞ ጠንካራ የደመና ክምችት ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የምዕራብ አርሲ፣ ባሌ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረና እና ምስራቅ ቦረና ዞኖች እንዲሁም የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ቄለም፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ምዕራብ እና ምስራቅ ወለጋ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳዉሮ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል፣ አሶሳ፣ ካማሽ እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ኮንሶ፣ ቡርጂ፣ አማሮ፣ ደቡብ ኦሞ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ፣ ኑዌር፣ ኢታንግ እና ማጃንግ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የዳዋ፣ ሊበን፣ አፍደር፣ ሸበሌ፣ ቆራሔ፣ ኖጎብ እና ጃራር ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን (1-29 ሚ.ሜ) ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በቡለን፣ በማኦኮሞ፣ በላሬ፣ በጋምቤላ፣ በቤጊ፣ በጊዳሚ፣ በጅማ ሆሮ፣ በሰዮ፣ በሳለኖኖ፣ በበደሌ፣ በጅማ አርጆ፣ በሊሙሴቃ፣ በማሻ፣ በየኪ፣ በጌዝዕጎፋ፣ በተርጫ፣ በክንዶኮይሻ እና በዲላ ዙሪያ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል አልፎ አልፎ ከሚኖረው የደመና ሽፋን ላይ በመነሳት በመተማ፣ በደባርቅ፣ በደምቢያ፣ በአለፋ፣ በአይከል፣ በፎገራ፣ በባህርዳር ዙሪያ፣ በጃዊ፣ በቻግኒ፣ በዳንግላ፣ በደንበጫ፣ በሰከላ፣ በሞጣ፣ በባኮቲቤ፣ በአመያ፣ በቡርቃ፣ በባቢሌ፣ በቸሃ፣ በስልጤ፣ በዳሎቻ፣ በወራ፣ በለሞ፣ በካቻብራ፣ በባዳዋቾ እና የየም ልዩ ዞን ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ ያገኛሉ፡፡

Tomorrow, there will be cloud coverage in the south and southeast areas of our country, which are the second rainy season of the Bega; also there will be strong cloud accumulation over the western and southwestern parts of the country. Along with this, from the Oromia region west Arsi, Bale, Guji and west Guji, Borena and east Borena zones, as well as Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, Kelam, Horo Guduru, west and east Wellega zones; from the south west Ethiopia region Bench Sheko, Sheka, Kefa, Konta, west Omo and Dawuro zones; from Benishangul Gumuz region Metekel, Asossa, Kamashi and Mao Komo zones; from the south Ethiopia region Walaita, Gamo, Gofa, Basketo, Konso, Burji, Amaro, south Omo and Gedeo zones; from Gambella region Agnuwak, Nuwer, Itang and Majang zones; zones of Sidama region and from Somali region Dawa, Liban, Afder, Shebelle, Korahe, Nogob and Jarar zones will receive light to moderate rainfall (1-29 mm) in many places. In addition, Bullen, Mao Komo, Lare, Gambella, Begi, Gidami, Jimma Horo, Sayo, Salenono, Bedele, Jimma Arjo, Limuseka, Masha, Yeki, Gezeigofa, Tercha, Kindokoisha and Dilla will receive heavy rainfall of more than 30 mm in 24 hours. On the other hand, from the occasional cloud coverage, Metema, debark, Dembiya, Alefa, Ayikel, Fogera, Bahirdar Zuria, Jawi, Chagni, Dangila, Denbecha, Sekela, Mota, Bakotibe, Ameya, Burka, Babile, Cheha, Silte, Dalocha, Warra, Lemmo, Kachabira, Badawacho and Yem Special zone will receive light to moderate unseasonal rainfall.