Daily Weather Report 24 Oct 26

Weather Summary for previous day

Oct. 25, 2024

በትናንትናው ዕለት በአብዛኛው የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን የነበራቸው ሲሆን በተለይም በምዕራብ፣ በደቡብ ምዕራብ እና በምስራቅ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ ጠንካራ የደመና ክምችት ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም ደባርቅ፣ መተማ፣ አይከል፣ ደብረታቦር፣ ባህርዳር፣ ቻግኒ፣ ደብረማርቆስ፣ ማጀቴ፣ መሀልመዳ፣ ደብረብርሀን፣ ቡለን፣ አሶሳ፣ ጋምቤላ፣ አቦቦ፣ ነጆ፣ ነቀምቴ፣ አርጆ፣ ሻምቡ፣ ጎሬ፣ ጅማ፣ እጃጂ፣ አዳማ፣ ኑራኤራ፣ መተሀራ፣ አዋሽ አርባ፣ ቡኢ፣ ኩሉምሳ፣ ገለምሶ፣ ቁሉቢ፣ አደሌ፣ አርሲሮቤ፣ ደሎመና፣ ነገሌ፣ ቡሌሆራ፣ ቦሬ፣ ያቤሎ፣ ሐዋሳ፣ ዲላ፣ ወራቤ፣ ተርጫ፣ ማሻ፣ ወላይታ ሶዶ፣ አርባ ምንጭ፣ ሳዉላ፣ ጂንካ እና አዋሮ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን (1-29 ሚ.ሜ) ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በነፋስመዉጫ፣ በዳንግላ፣ በሸርኮሌ፣ በፉኚዶ እና በባቢሌ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, there was cloud coverage over most parts of the country, particularly in the west, southwest and east parts of the country had strong cloud accumulation. In line with this, Debark, Metema, Ayikel, Debretabor, Bahirdar, Chagni, Debremarkos, Majete, Mehalmeda, Debrebrehan, Bullen, Asossa, Gambella, Abobo, Nedjo, Nekemte, Arjo, Shambu, Gore, Jimma, Ijaji, Adama, Nuraera, Metehara, Awash Arba, Bui, Kulumsa, Gelemso, Kulubi, Adele, Arsirobe, Delomanna, Negelle, Bulehora, Bore, Yabelo, Hawassa, Dilla, Werabe, Tercha, Masha, Walaita Sodo, Arba Minch, Sawula, Jinka and Awaro received light to moderate (1-29 mm) rain. More than 30 mm of heavy rainfall was recorded over Nefasmewucha, Dangila, Sherkole, Fugnido and Babile.

Weather Forecast for next day

Oct. 27, 2024

በነገው ዕለት በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በደቡብና ደቡብ ምስራቅ የሀገራችን አከባቢዎች እና በምዕራብ፣ በደቡብ ምዕራብ እና በምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የተስፋፋ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የምዕራብ አርሲ፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረና እና ምስራቅ ቦረና ዞኖች እንዲሁም የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ቄለም፣ ምዕራብ እና ምስራቅ ወለጋ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳዉሮ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል፣ አሶሳ፣ ካማሽ እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ኮንሶ፣ ቡርጂ፣ አማሮ፣ ደቡብ ኦሞ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል በጥቂት አኙዋክ እና ማጃንግ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የዳዋ፣ ሊበን፣ አፍደር፣ ሸበሌ፣ ቆራሔ፣ ኖጎብ፣ ኤሬር እና ጃራር ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን (1-29 ሚ.ሜ) ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በአሶሳ፣ በማኦኮሞ፣ በቤጊ፣ በደዴሳ፣ በሰተማ፣ በጌራ፣ በባሌ፣ በመዳወላቡ፣ በቡርቃ፣ በማሻ፣ በገሻ፣ በጌዲኦ፣ በደጋሃቡር፣ በአዋሮ፣ በቀብሪዳሃር እና በደናን በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል ከሚጠናከሩት የአየር ሁኔታ ክስተቶች ላይ በመነሳት በአዲግራት፣ በሽሬእንደስላሴ፣ በፀገደ፣ በፀለምት፣ በደባርቅ፣ በመተማ፣ በአርማጮ፣ በደምቢያ፣ በአለፋ፣ በጎንደር፣ በአይከል፣ በፎገራ፣ በባህርዳር፣ በቻግኒ፣ በዳንግላ፣ በአቸፈር፣ በደንበጫ፣ በሰከላ፣ በደጋዳሞት፣ በጎሎልቻ፣ በሮቤ፣ በጮሌ፣ በጭሮ፣ በቦኬ፣ በግራዋ፣ በፌዲስ፣ በኩርፋጨሌ፣ በደደር፣ በባቢሌ፣ በጉርሱም፣ በለሞ፣ በካቻብራ፣ በባዳዋቾ እና የየም ልዩ ዞን ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ ያገኛሉ፡፡

Tomorrow, our country's south and southeast areas, which are the second rainy season of the Bega and in the west, southwest and east of the country will have widespread cloud coverage. Along with this, from the Oromia region west Arsi, Bale and east Bale, Guji and west Guji, Borena and east Borena zones as well as Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, Kelam, west and east Wellega zones; from the South west Ethiopia region Bench Sheko, Sheka, Kefa, Konta, west Omo and Dawuro zones; from Benishangul Gumuz region Metekel, Asosa, Kamashi and Mao Komo zones; from the south Ethiopia region Walaita, Gamo, Gofa, Basketo, Konso, Burji, Amaro, south Omo and Gedeo zones; from the Gambella region in a few zones of Agnuwak and Majang; zones of Sidama region and from Somali region Dawa, Liban, Afder, Shebelle, Korahe, Nogob, Erer and Jarar zones will receive light to moderate rainfall (1-29 mm) in many places. In addition, Asosa, Mao Komo, Begi, Dedesa, Setema, Gera, Bale, Madda Walabu, Burka, Masha, Gesha, Gedeo, Degahabur, Awaro, Kebridehar and Denan will receive heavy rainfall of more than 30 mm in 24 hours. On the other hand, due to the intensifying weather events, Adigrat, Shire Endesilase, Tsegede, Tselemt, Debark, Metema, Armacho, Dembiya, Alefa, Gondar, Ayikel, Fogera, Bahirdar, Chagni, Dangila, Achefer, Denbecha, Sekela, Degadamot, Gololcha, Robe, Chole, Chiro, Boke, Girawa, Fedis, Kurfachele, Deder, Babile, Gursum, Lemo, Kachabira, Badawacho and Yem special zone will receive light to moderate unseasonal rain.