Daily Weather Report 24 Oct 24
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በሰሜን፣ በምዕራብ፣ በደቡብ ምዕራብ፣ በደቡብ እና በደቡብ ምስራቅ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም ሽሬእንደስላሴ፣ አዲግራት፣ አፅቢ፣ መቀሌ፣ ደባርቅ፣ ጎንደር፣ አይከል፣ ዳንግላ፣ ቻግኒ፣ ሞጣ፣ አሶሳ፣ ጋምቤላ፣ ደንብዶሎ፣ በነጆ፣ በጊምቢ፣ በአይራ፣ ነቀምቴ፣ በደሌ፣ ቡሬ፣ ጎሬ፣ ጭራ፣ እጃጂ፣ አርሲሮቤ፣ ባሌሮቤ፣ ቦሬ፣ ነገሌ፣ ቡሌሆራ፣ ያቤሎ፣ ዲላ፣ ሐዋሳ፣ አርባ ምንጭ፣ ምዕራብአባያ፣ ሳዉላ፣ ጂንካ፣ ማጂ እና ቴፒ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን (1-29 ሚ.ሜ) ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በአንገርጉትን፣ በሊሙገነት እና በአዋሮ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, there was cloud coverage over the north, west, south west, south and south east parts of the country. In association with this, Shire Endesilase, Adigrat, Atsebi, Mekelle, Debark, Gondar, Ayikel, Dangila, Chagni, Motta, Asossa, Gambella, Denbidollo, Nedjo, Gimbi, Aira, Nekemte, Bedele, Bure, Gore, Chira, Ijaji, Arsirobe, Balerobe, Bore, Negelle, Bulehora, Yabelo, Dilla, Hawassa, Arba Minch, Mirab Abaya, Sawula, Jinka, Maji and Tepi received light to moderate rainfall (1-29 mm). Additionally, more than 30 mm of heavy rain was recorded over Angergutin, Limugenet and Awaro.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በደቡብና ደቡብ ምስራቅ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን የሚኖራቸው ሲሆን፤ በምዕራብ፣ በደቡብ ምዕራብ እና በምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ ደግሞ ጠንካራ የደመና ክምችት ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የምዕራብ አርሲ፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ፣ ጉጂ እና ምዕራብ ጉጂ ዞኖች እንዲሁም የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ቄለም፣ ምዕራብ እና ምስራቅ ወለጋ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳዉሮ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል፣ አሶሳ፣ ካማሽ እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ እና ማጃንግ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የዶሎ፣ ቆራሔ፣ ሸበሌ እና ጃራር ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በማኦኮሞ፣ አሶሳ፣ በቤጊ፣ በጊዳሚ፣ በጅማ ሆሮ፣ በቡሬ፣ በመቱ፣ በአሌ፣ በማሻ፣ በየኪ፣ በገሻ፣ በፌዲስ፣ በግራዋ፣ በቀብሪበያ እና በደጋሃቡር በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል ከሚጠናከሩት የአየር ሁኔታ ክስተቶች ላይ በመነሳት በፀገደ፣ በወልቃይት፣ በዳንሻ፣ በሽሬእንደስላሴ፣ በማይጨው፣ በጨርጨር፣ በአብዓላ፣ በጭፍራ፣ በዳሊፋጊ፣ በአዋሽ በፋንታሌ፣ በገዋኔ፣ በአርጎባ፣ በደባርቅ፣ በጎንደር፣ በአይከል፣ በባህርዳር፣ በቻግኒ፣ በዳንግላ፣ በቆቦ፣ በባቲ፣ በደዋጨፋ፣ በምንጃርሸንኮራ፣ በአንኮበር፣ በብርሐት፣ በባኮቲቤ፣ በኖኖ፣ በአመያ፣ በአዳሚቱሉ፣ በፋንታሌ፣ በሜርቲ፣ በአሴኮ፣ በጎሎልቻ፣ በጮሌ፣ በጭሮ፣ በቦኬ፣ በቡርቃ፣ በሐሮማያ፣ በሜታ፣ በጉርሱም፣ በባቢሌ፣ በሳንኩራ፣ በወራ፣ በለሞ፣ በካቻብራ እና የየም ልዩ ዞን ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ ያገኛሉ፡፡
Tomorrow, there will be cloud coverage in the south and southeast areas of our country, which is the second rainy season of the Bega. There will also be a strong accumulation of cloud over the western, southwestern and eastern parts of the country. In line with this, from the Oromia region west Arsi, Bale and east Bale, Guji and west Guji zones as well as Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, Horo Guduru, Kelam, west and east Wellega zones; from the south west Ethiopia region Bench Sheko, Sheka, Kefa, Konta, west Omo and Dawuro zones; from the Benishangul Gumuz region Metekel, Asossa, Kamashi and Mao Komo zones; from the south Ethiopia region Walaita, Gamo, Gofa, Basketo and Gedeo zones; from Gambella region Agnuwak and Majang zones; zones of Sidama region and from Somali region Dollo, Korahe, Shebelle and Jarar zones will receive light to moderate rainfall in many places. In addition, Mao Komo, Asossa, Begi, Gidami, Jimma Horo, Bure, Mettu, Ale, Masha, Yeki, Gesha, Fedis, Girawa, Keberibeya and Degahabur will receive heavy rainfall of more than 30 mm in 24 hours. On the other hand, due to the intensifying weather events, Tsegede, Welkait, Dansha, Shire Endesilase, Myichew, Chercher, Abiala, Chifra, Dalifagi, Awashfantale, Gewane, Argoba, Debark, Gondar, Ayikel, Bahirdar, Chagni, Dangila, Kobo, Bati, Dewachefa, Minjarshenkora, Ankober, Berehat, Bakotibe, Nono, Amaya, Adamitulu, Fentale, Merti, Aseko, Gololcha, Chole, Chiro, Boke, Burka, Haromaya, Metta, Gursum, Babile, Sankura, Wara, Lemmo, Kachabira and Yem special zone will receive light to moderate unseasonal rain.