Daily Weather Report 24 Oct 23

Weather Summary for previous day

Oct. 22, 2024

በትናንትናው ዕለት ሽሬእንደስላሴ፣ ደባርቅ፣ ጎንደር፣ አይከል፣ ፓዌ፣ ቻግኒ፣ የትኖራ፣ ጋምቤላ፣ ቡሬ፣ ደንብዶሎ፣ ነጆ፣ አይራ፣ ጊምቢ፣ ነቀምቴ፣ አርጆ፣ ሻምቡ፣ ጭራ፣ ጅማ፣ ጋቲራ፣ ሶኮሩ፣ ኑራኤራ፣ ጃራ፣ ደሎመና፣ ነገሌ፣ ቡሌሆራ፣ ቦሬ፣ አማን፣ ተርጫ፣ ሆሳዕና፣ ሐዋሳ፣ ዲላ፣ ወላይታ ሶዶ፣ አርባ ምንጭ፣ ምዕራብአባያ፣ ሳዉላ፣ ጂንካ፣ ኮንሶ፣ ቡርጂ እና አዋሮ የደመና ሽፋን የነበራቸው ሲሆን ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በቡሌን ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, Shire Endesilase, Debark, Gondar, Ayikel, Pawe, Chagni, Yetnora, Gambella, Bure, Denbidollo, Nedjo, Aira, Gimbi, Nekemte, Arjo, Shambu, Chira, Jimma, Gatira, Sokoru, Nuraera, Jara, Delomanna, Negelle, Bulehora, Bore, Aman, Tercha, Hosaina, Hawassa, Dilla, Walaita Sodo, Arba Minch, Mirab Abaya, Sawula, Jinka, Konso, Burji and Awaro had cloud coverage and also received light to moderate rainfall. In addition, heavy rainfall of more than 30 mm was recorded over Bullen.

Weather Forecast for next day

Oct. 24, 2024

በነገው ዕለት በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት የደቡብና ደቡብ ምስራቅ የሀገራችን አከባቢዎች እና በምዕራብ፣ በደቡብ ምዕራብ እና በሰሜን ምዕራብ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ ጠንካራ የደመና ሽፋንና ክምችት ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል ምዕራብ አርሲ፣ ባሌ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረና እና ምስራቅ ቦረና ዞኖች እንዲሁም የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ቄለም፣ ምዕራብ እና ምስራቅ ወለጋ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ እና ዳዉሮ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል፣ አሶሳ፣ ካማሽ እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ደራሸ፣ ኮንሶ፣ ቡርጂ፣ ደቡብ ኦሞ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ እና ማጃንግ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የዶሎ፣ ቆራሔ፣ ሸበሌ እና ጃራር ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል ከሚኖረው የደመና ሽፋን ላይ በመነሳት ምዕራብ ትግራይ ዞን፤ ሰሜን፣ ምዕራብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ምዕራብ ጎጃም፤ ምዕራብ ሸዋ፣ አርሲ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ ሐረር፤ ኤሬር፣ ፋፈን፤ ጉራጌ፣ ሀላባ፣ ሀድያ፣ የየም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ ያገኛሉ፡፡

Tomorrow, the south and southeast areas of our country, where the Bega is their second rainy season and the west, southwest and northwest parts of the country will have strong cloud coverage and accumulation. Along with this, from the Oromia region west Arsi, Bale, Guji and west Guji, Borena and east Borena zones as well as Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, Kelam, west and east Wellega zones; from the south west Ethiopia region Bench Sheko, Sheka, Kefa, Konta and Dawuro zones; from Benishangul Gumuz region Metekel, Asossa, Kamashi and Mao Komo zones; from the south Ethiopia region Walaita, Gamo, Gofa, Basketo, Derashe, Konso, Burji, south Omo and Gedeo zones; from Gambella region Agnuwak and Majang zones; zones of Sidama region and from the Somali region Dollo, Korahe, Shebelle and Jarar zones will receive light to moderate rainfall in many places. On the other hand, from the cloud coverage west, Tigray zone; north, west and central Gondar, Awi zone, west Gojjam; west Shewa, Arsi, west and east Hararge zones; Harar; Erer, Fafen; Gurage, Halaba, Hadiya, Yem special zone, Kambata and Tembaro zones will receive light to moderate unseasonal rain.