Daily Weather Report 24 Oct 22
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በሰሜን ምዕራብ፣ በምዕራብ፣ በሰሜን ምስራቅ፣ በመካከለኛው፣ በደቡብ ምዕራብ፣ በደቡብ ምስራቅ እና በምስራቅ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም ሽሬእንደስላሴ፣ አዲግራት፣ አፅቢ፣ ማይጨው፣ ኤሊዳር፣ አሶሳ፣ ጋምቤላ፣ ኤሊያ፣ ቻግኒ፣ ዳንግላ፣ ጎንደር፣ አይከል፣ ባህርዳር፣ ደብረታቦር፣ ነፋስመዉጫ፣ ላሊበላ፣ ሲሪንቃ፣ ኮምቦልቻ፣ ጨፋ፣ ባቲ፣ ሞጣ፣ የትኖራ፣ ደብረብርሀን፣ ሾላገበያ፣ አንገርጉትን፣ ነቀምቴ፣ ጭራ፣ ጋቲራ፣ ሊሙገነት፣ ሶኮሩ፣ ቡኢ፣ አዳማ፣ መተሀራ፣ ሐሮማያ፣ ኩሉምሳ፣ አደሌ፣ ባሌሮቤ፣ ቦሬ፣ ነገሌ፣ ያቤሎ፣ ሞያሌ፣ ዲላ፣ ሐዋሳ፣ እንድብር፣ ቢላቴ፣ ወላይታ ሶዶ፣ አርባ ምንጭ፣ ሳዉላ፣ ጂንካ፣ ቡርጂ፣ ኮንሶ፣ አማን፣ ተርጫ፣ ሐረር፣ አዋሮ እና ጎዴ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን (1-29 ሚ.ሜ) ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በፓዌ እና በማሻ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, there was cloud coverage over the north west, west, north east, central, south west, south east and east parts of the country. In line with this, Shire Endesilase, Adigrat, Atsebi, Myichew, Elidar, Asossa, Gambella, Elia, Chagni, Dangila, Gondar, Ayikel, Bahirdar, Debretabor, Nefasmewucha, Lalibela, Sirinka, Kombolcha, Cheffa, Bati, Motta, Yetnora, Debrebrehan, Sholagebeya, Angergutin, Nekemte, Chira, Gatira, Limugenet, Sokoru, Bui, Adama, Metehara, Haromaya, Kulumsa, Adele, Balerobe, Bore, Negelle, Yabelo, Moyale, Dilla, Hawassa, Indibir, Bilate, Walaita Sodo, Arba Minch, Sawula. , Jinka, Burji, Konso, Aman, Tercha, Harar, Awaro and Gode received light to moderate rainfall (1-29 mm). Additionally, heavy rainfall of over 30 mm was recorded over Pawe and Masha.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት ዝናብ ሰጭ የአየር ሁኔታ ክስተቶች በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት የደቡብና ደቡብ ምስራቅ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን የሚኖራቸው ሲሆን፤ በምዕራብ እና በደቡብ ምዕራብ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ ጠንካራ የደመና ክምችት ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል ምዕራብ አርሲ፣ ባሌ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረና እና ምስራቅ ቦረና ዞኖች እንዲሁም የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ቄለም፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ምዕራብ እና ምስራቅ ወለጋ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ እና ዳዉሮ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል፣ አሶሳ፣ ካማሽ እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ደራሸ፣ ደቡብ ኦሞ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ እና ማጃንግ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የዳዋ፣ ሊበን፣ ዶሎ፣ ቆራሔ እና ሸበሌ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል ከሚጠናከሩት የአየር ሁኔታ ክስተቶች ላይ በመነሳት ምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ማዕከላዊና ምስራቅ ትግራይ ዞኖች፤ ቂልበቲ ዞን፤ ሰሜን፣ ምዕራብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ምዕራብ ጎጃም፤ ምዕራብና ደቡብ ምዕራብ ሸዋ፣ አርሲ፣ ምስራቅ ሐረርጌ ዞን፤ ሐረር፤ ኤሬር፣ ፋፈን፣ ጃራር፤ ጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀላባ፣ ሀድያ፣ የየም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ ያገኛሉ፡፡
Tomorrow, rain-producing weather events will have cloud coverage in the south and southeast areas of our country, which are the second rainy season of the Bega. There will be strong cloud accumulation in the west and southwest. Along with this, from Oromia region west Arsi, Bale, Guji and west Guji, Borena and east Borena zones as well as Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, Kelam, Horo Guduru, west and east Wellega zones; from the south west Ethiopia region Bench Sheko, Sheka, Kefa, Konta and Dawuro zones; from Benishangul Gumuz region Metekel, Asossa, Kamashi and Mao Komo zones; from the south Ethiopia region Walaita, Gamo, Gofa, Basketo, Derashe, south Omo and Gedeo zones; from Gambella region Agnuwak and Majang zones; zones of Sidama region and from the Somali region of Dawa, Liben, Dollo, Korahe and Shebelle zones will receive light to moderate rainfall in many places. On the other hand, due to the intensifying weather events, west, north west, central and east Tigray zones; Kilbeti zone; north, west and central Gondar, Awi zone, west Gojjam; west and south west Shewa, Arsi, east Hararge zone; Harar; Erer, Fafen, Jarar; Gurage, Silte, Halaba, Hadiya, Yem special zone, Kambata and Tembaro zones will receive light to moderate unseasonal rain.