Daily Weather Report 24 Oct 21

Weather Summary for previous day

Oct. 20, 2024

በትናንትናው ዕለት ማንኩሽ፣ ባህርዳር፣ አየሁ፣ ነቀምቴ፣ ጎሬ፣ ቡሌሆራ፣ ቦሬ፣ ሞያሌ፣ ያቤሎ፣ ዲላ፣ ወላይታ ሶዶ፣ አርባ ምንጭ፣ ምዕራብአባያ፣ ሳዉላ፣ ጂንካ፣ ኮንሶ እና ቡርጂ የደመና ሽፋን የነበራቸው ሲሆን ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው (1-29 ሚ.ሜ) ዝናብ አግኝተዋል፡፡

Yesterday, Mankush, Bahir Dar, Ayehu, Nekemte, Gore, Bulehora, Bore, Moyale, Yabelo, Dilla, Walaita Sodo, Arba Minch, Mirab Abaya, Sawula, Jinka, Konso and Burji had cloud coverage along with light to moderate rainfall.

Weather Forecast for next day

Oct. 22, 2024

በነገው ዕለት በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በደቡብና ደቡብ ምስራቅ የሀገራችን አከባቢዎች እና በምዕራብ፣ በደቡብ ምዕራብ እና በሰሜን ምዕራብ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የተስፋፋ የደመና ሽፋንና ክምችት ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል ምዕራብ አርሲ፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረና እና ምስራቅ ቦረና ዞኖች እንዲሁም የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ቄለም፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ምዕራብ እና ምስራቅ ወለጋ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳዉሮ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል፣ አሶሳ፣ ካማሽ እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ቡርጂ፣ አማሮ፣ ደራሸ፣ ኮንሶ፣ ደቡብ ኦሞ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ እና ማጃንግ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ሁሉም ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የዳዋ፣ ሊበን፣ አፍደር፣ ዶሎ፣ ቆራሔ፣ ሸበሌ፣ ኖጎብ እና ጃራር ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በፀሀይ ኃይል ታግዝው ከሚፈጠሩት የአየር ሁኔታ ክስተቶች ላይ በመነሳት ሰሜን፣ ምዕራብ፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ምዕራብ ጎጃም፤ ምዕራብና ደቡብ ምዕራብ ሸዋ፣ አርሲ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ፤ ኤሬር፣ ፋፈን፤ ጉራጌ፣ ሀላባ፣ ሀድያ፣ የየም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ ያገኛሉ፡፡

Tomorrow, there will be widespread cloud coverage and accumulation in the south and southeast areas of our country, which are in their Bega second rainy season and the west, southwest and northwest areas of the country. Along with this, from Oromia region west Arsi, Bale and east Bale, Guji and west Guji, Borena and east Borena zones as well as Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, Kelam, Horo Guduru, west and east Wellega zones; from the south west Ethiopia region Bench Sheko, Sheka, Kefa, Konta, west Omo and Dawuro zones; from Benishangul Gumuz region Metekel, Asossa, Kamashi and Mao Komo zones; from the south Ethiopia region Walaita, Gamo, Gofa, Basketo, Burji, Amaro, Derashe, Konso, south Omo and Gedeo zones; from Gambella region Agnuwak and Majang zones; all zones of Sidama region and from Somali region Dawa, Liban, Afder, Dollo, Korahe, Shebelle, Nogob and Jarar zones will receive light to moderate rainfall in many places. On the other hand, due to the weather events created with the help of solar energy, north, west, south and central Gondar, Awi zone, west Gojjam; west and southwest Shewa, Arsi, west and east Hararge; Erer, Fafen; Gurage, Halaba, Hadiya, Yem Special zone, Kambata and Tembaro zones will experience light to moderate unseasonal rain.