Daily Weather Report 24 Oct 20
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በምዕራብ፣ በደቡብ ምዕራብ፣ በደቡብ እና በመካከለኛው የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም አይከል፣ ሳዉላ፣ ነቀምቴ፣ ያቤሎ፣ ዲላ፣ አርባ ምንጭ፣ ኮንሶ፣ ቡርጂ፣ ቡሌ ሆራ፣ ቦሬ እና ጂንካ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን (1-29 ሚ.ሜ) ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በሳውላ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, cloud cover was observed in the western, southwestern, southern, and central parts of the country. In association with this, Aykel, Nekemte, Sawula, Arba Minch, Jinka, Konso, Burji, Bule Hora, Yabelo, Dila and Bore received light to moderate rainfall (1-29 mm). In addition, above 30 mm of heavy rainfall was recorded over the areas of Sawula.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት የደቡብና ደቡብ ምስራቅ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የተሻለ የደመና ሽፋን የሚኖራቸው ሲሆን፤ በተጨማሪም በምዕራብ፣ በሰሜን ምዕራብ፣ በሰሜን ምስራቅ እና በደቡብ ምዕራብ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋንና ክምችት ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል ምዕራብ አርሲ፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረና እና ምስራቅ ቦረና ዞኖች እንደዚሁም ቄለምና ምዕራብ ወለጋ፣ ጅማ፣ ቡኖበደሌ እና ኢሉባቦር ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳዉሮ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል፣ አሶሳ፣ ካማሽ እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ቡርጂ፣ አማሮ፣ ደራሸ፣ ኮንሶ፣ ደቡብ ኦሞ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ፣ ኢታንግ እና ማጃንግ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የዳዋ፣ ዶሎ፣ ኤሬር፤ አፍዴር፣ ኖጎብ፣ ሸበሌ፣ ጃራር እና ሊበን ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በሸካ፣ ደቡብ ቤንች፣ ጌቺ፣ ዲማ፣ ቢታ፣ ጉጪ፣ ውጫሌ፣ መዳ ዋላቡ፣ ደኖድ፣ በአንፊሎ፣ በቦከህ፣ በማኦኮሞ፣ በቤጊ፣ በጊዳሚ እና ገሻሁ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል አልፎ አልፎ ከሚፈጠናከረው የአየር ሁኔታ ክስተቶች ላይ በመነሳት በምዕራብ፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ ደቡብና ሰሜን ወሎ እና አዊ ዞን፣ አርሲ፣ ምስራቅ ወለጋ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ ሀላባ፣ ሀድያ፣ የም ልዩ ዞን፣ ከምባታ፣ ጠምባሮ እና ፋፈን ዞኖች በጥቂት ስፍራዎቻቸው ላይ ቀላል መጠን ያለው ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ ያገኛሉ፡፡
On the following day, there will be heavy cloud cover in the west, southwest, and northwest regions of our country, as well as in the south and south-east regions, which are currently experiencing their second rainy season. In addition to this, from the Oromia region west Arsii, Bale and east Bale, Guji and west Guji, Borena and east Borena zones as well as Kellam and west Wellega, Ilubabor, Jimma, and Buno Bedele zones; from the south west Ethiopia region Bench Sheko, Sheka, Kefa, Konta, west Omo and Dawuro zones; from the Benishangul Gumuz region Metekel, Asossa, Kamashi and Mao Komo zones; from the south Ethiopia region Walaita, Gamo, Gofa, Basketo, Burji, Amaro, Derashe, Konso, south Omo and Gedeo zones; from Gambella region Agnuwak, Itang and Majang zones; zones of Sidama region and from Somali region Dawa,Dolo, Fafen, Erer; Afdar,Nogob,Jarar and Liban zones will receive light to moderate rainfall in most of their areas. In addition Shaka, Debub Benchi, Gechi, Wucale, Dima, Bita, Guci, Mada Walabu, Danod, Begi, Gidami, Anfilo, Bokh, Mao kono, and Geshahu will receive heavy rainfall of more than 30 mm in 24 hours. However, due to the weather events triggered by solar energy, west and south Gondar, Awi zone, west and east Gojjam; north and south west Wallo, Horo Guduru, west and east Hararge zones; Halaba, Hadiya, Yem special zone, Kambata and Tembaro zones will experience light unseasonal rain at few places.