Daily Weather Report 24 Oct 18
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በምዕራብ፣ በደቡብ ምዕራብ፣ በደቡብ እና በመካከለኛው የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም ማንኩሽ፣ ቡለን፣ አሶሳ፣ ቻግኒ፣ ዳንግላ፣ ደባርቅ፣ ጊምቢ፣ ነቀምቴ፣ ጎሬ፣ ጭራ፣ ጋቲራ፣ ሊሙገነት፣ ሶኮሩ፣ አዲስ አበባ፣ ነገሌ፣ ያቤሎ፣ ሐዋሳ፣ ዲላ፣ ሆሳዕና፣ ቢላቴ፣ አማን፣ ሳዉላ፣ አርባ ምንጭ፣ ምዕራብአባያ፣ ኮንሶ፣ ቡርጂ እና ጂንካ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን (1-29 ሚ.ሜ) ዝናብ አግኝተዋል፡፡
Yesterday, cloud cover was observed in the western, southwestern, southern, and central parts of the country. In association with this, Mankushi, Bullen, Asossa, Chagni, Dangila, Debark, Gimbi, Nekemte, Gore, Chira, Gatira, Limugenet, Sokoru, Addis Ababa, Negelle, Yabelo, Hawasa, Dilla, Hosaina, Bilate, Aman, Sawula, Arba Minch, Mirab Abaya, Konso, Burji and Jinka received light to moderate rainfall (1-29 mm).
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በደቡብና ደቡብ ምስራቅ የሀገራችን አከባቢዎች እና በምዕራብ፣ በደቡብ ምዕራብ እና በሰሜን ምዕራብ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ ጠንካራ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል ምዕራብ አርሲ፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረና እና ምስራቅ ቦረና ዞኖች እንዲሁም የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ቄለም፣ ምዕራብ እና ምስራቅ ወለጋ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳዉሮ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል፣ አሶሳ፣ ካማሽ እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ቡርጂ፣ አማሮ፣ ደራሸ፣ ኮንሶ፣ ደቡብ ኦሞ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ፣ ኑዌር፣ ኢታንግ እና ማጃንግ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የዳዋ እና ሊበን ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በማኦኮሞ፣ በአሶሳ፣ በቤጊ፣ በጊዳሚ፣ በአንፍሎ፣ በጅማ ሆሮ፣ በሳለኖኖ፣ በማሻ እና በየኪ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በፀሀይ ኃይል ታግዝው ከሚፈጠሩት የአየር ሁኔታ ክስተቶች ላይ በመነሳት ምዕራብ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ምዕራብ ጎጃም፤ አርሲ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ ፋፈን፣ ኤሬር፤ ሀላባ፣ ሀድያ፣ የየም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች በጥቂት ስፍራዎቻቸው ላይ ቀላል መጠን ያለው ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ ያገኛሉ፡፡
Tomorrow, the south and south east areas of our country, which are in their Bega second rainy season and the west, southwest and northwest areas of the country will have strong cloud coverage. Along with this, from the Oromia region west Arsii, Bale and east Bale, Guji and west Guji, Borena and east Borena zones as well as Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, Kelam, west and east Wellega zones; from the south west Ethiopia region Bench Sheko, Sheka, Kefa, Konta, west Omo and Dawuro zones; from the Benishangul Gumuz region Metekel, Asossa, Kamashi and Mao Komo zones; from the south Ethiopia region Walaita, Gamo, Gofa, Basketo, Burji, Amaro, Derashe, Konso, south Omo and Gedeo zones; from Gambella region Agnuwak, Nuwer, Itang and Majang zones; zones of Sidama region and from Somali region Dawa and Liban zones will receive light to moderate rainfall in most of their areas. In addition, Mao Komo, Asossa, Begi, Gidami, Anfilo, Jimma Horo, Salenono, Masha and Yeki will receive heavy rainfall of more than 30 mm in 24 hours. On the other hand, due to the weather events triggered by solar energy, west Gondar, Awi zone, west Gojjam; Arsi, west and east Hararge zones; Fafen, Erer; Halaba, Hadiya, Yem special zone, Kambata and Tembaro zones will experience light unseasonal rain at few places.