Daily Weather Report 24 Oct 17

Weather Summary for previous day

Oct. 16, 2024

በትናንትናው ዕለት በሰሜን ምዕራብ፣ በምዕራብ፣ በደቡብ ምዕራብ፣ በደቡብ እና በመካከለኛው የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም ደባርቅ፣ ጎንደር፣ ቻግኒ፣ ቡለን፣ አሶሳ፣ ጊምቢ፣ አንገርጉትን፣ ነቀምቴ፣ ጊዳአያና፣ ሻምቡ፣ በደሌ፣ ጭራ፣ ጋቲራ፣ ሊሙገነት፣ ሶኮሩ፣ ኢጃጂ፣ ፍቼ፣ ኮምቦልቻ፣ ነገሌ፣ ያቤሎ፣ ሞያሌ፣ ሐዋሳ፣ ዲላ እንድብር፣ ሆሳዕና፣ ወራቤ፣ አማን፣ ተርጫ፣ ወላይታ ሶዶ፣ ሳዉላ፣ አርባ ምንጭ እና ጂንካ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን (1-29 ሚ.ሜ) ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በፓዌ፣ በጅማ እና በቦሬ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, cloud coverage was observed in the north west, west, south west, south and central parts of the country. In line with this, Debark, Gondar, Chagni, Bullen, Asossa, Gimbi, Angergutin, Nekemte, Gidayana, Shambu, Bedele, Chira, Gatira, Limugenet, Sokoru, Ijaji, Fiche, Kombolcha, Negelle, Yabelo, Moyale, Hawasa, Dilla, Indibir, Hosaina, Werabe, Aman, Tercha, Walaita Sodo, Sawula, Arba Minch and Jinka received light to moderate rainfall (1-29 mm). Additionally, more than 30 mm of heavy rain was recorded over Pawe, Jimma and Bore.

Weather Forecast for next day

Oct. 18, 2024

በነገው ዕለት በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በደቡብና ደቡብ ምስራቅ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን የሚኖራቸው ሲሆን፤ በሌላ በኩል በምዕራብ፣ በደቡብ ምዕራብ እና በሰሜን ምዕራብ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የተስፋፋ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል ምዕራብ አርሲ፣ ባሌ፣ ምስራቅ ቦረና፣ ጉጂ እና ምዕራብ ጉጂ ዞኖች እንዲሁም የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ቄለም፣ ምዕራብ፣ ምስራቅ እና የሆሮጉድሩ ወለጋ ዞኖች፣ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳዉሮ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል፣ አሶሳ፣ ካማሽ እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ቡርጂ፣ አማሮ፣ ደራሸ፣ ኮንሶ፣ ደቡብ ኦሞ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ፣ ኑዌር፣ ኢታንግ እና ማጃንግ ዞኖች እና የሲዳማ ክልል ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በማኦኮሞ፣ በጋምቤላ፣ በቤጊ፣ በጊዳሚ፣ በአንፍሎ፣ በሰዮ፣ በጅማ ሆሮ፣ በጉቶጊዳ፣ በአልጌ፣ በያዩ፣ በአሌ፣ በሳለኖኖ፣ በማሻ፣ በየኪ፣ በሸኮ፣ በማጂ፣ በገሻ፣ በደቻ፣ በክንዶኮይሻ እና በዳሞትሶሬ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል ከሚኖረው የደመና ሽፋን ላይ በመነሳት ምዕራብና ማዕከላዊ ጎንደር፤ አዊ ዞን፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፤ ሰሜን፣ ምዕራብና ደቡብ ምዕራብ ሸዋ፣ ምስራቅ ሐረርጌ ዞን፤ ፋፈን፣ ኤሬር፣ ጃራር፤ ጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀላባ፣ ሀድያ፣ የየም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች በጥቂት ስፍራዎቻቸው ላይ ቀላል መጠን ያለው ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ ያገኛሉ፡፡

Tomorrow, there will be cloud coverage over the south and south east areas of our country, which are in their Bega second rainy season. On the other hand, there will be widespread cloud coverage over the western, southwestern and northwestern parts of the country. Regarding with this, from Oromia region west Arsi, Bale, East Borena, Guji and west Guji zones as well as Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, Kelam, west, east and Horo Guduru Wellega zones; from the south west Ethiopia region Bench Sheko, Sheka, Kefa, Konta, west Omo and Dawuro zones; from Benishangul Gumuz region Metekel, Asossa, Kamashi and Mao Komo zones; from the south Ethiopia region of Walaita, Gamo, Gofa, Basketo, Burji, Amaro, Derashe, Konso, south Omo and Gedeo zones; from Gambella region Agnuwak, Nuwer, Itang and Majang zones and Sidama region zones will receive light to moderate rainfall in most of their areas. Besides, Mao Komo, Gambella, Begi, Gidami, Anfilo, Seyo, Jimma Horo, Gutogida, Alge, Yayu, Ale, Salenono, Masha, Yeki, Sheko, Maji, Gesha, Decha, Kindokoisha and Damotsore will receive more than 30 mm heavy rainfall in 24 hours. On the other side, from the cloud coverage west and central Gondar; Awi zone, west and east Gojjam; north, west and south west Shewa, east Hararge zone; Fafen, Erer, Jarar; Gurage, Silte, Halaba, Hadiya, Yem special zone, Kambata and Tembaro zones will receive light unseasonal rain at few places.