Daily Weather Report 24 Oct 16

Weather Summary for previous day

Oct. 15, 2024

በትናንትናው ዕለት አይከል፣ ሞጣ፣ ደብረማርቆስ፣ የትኖራ፣ አሶሳ፣ ቡለን፣ ነጆ፣ አይራ፣ አለምተፈሪ፣ ጊምቢ፣ ነቀምቴ፣ አንገርጉትን፣ ጊዳአያና፣ ሻምቡ፣ ጎሬ፣ ጭራ፣ ጋቲራ፣ በደሌ፣ ሶኮሩ፣ ሊሙገነት፣ ኢጃጂ፣ አዲስ አበባ፣ ጊኒር፣ ቡሌሆራ፣ ቦሬ፣ ያቤሎ፣ ቴፒ፣ አማን፣ ተርጫ፣ ሆሳዕና፣ ሐዋሳ፣ ወላይታ ሶዶ፣ አርባ ምንጭ፣ ሳዉላ፣ ጂንካ፣ ኮንሶ እና ቡርጂ የደመና ሽፋን የነበራቸው ሲሆን ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በቻግኒ እና በአርጆ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡

Yesterday, Ayikel, Mota, Debremarkos, Yetnora, Asossa, Bulen, Nedjo, Aira, Alemteferi, Gimbi, Nekemte, Angergutin, Gidayana, Shambu, Gore, Chira, Gatira, Bedele, Sokoru, Limugenet, Ijaji, Addis Ababa, Ginir, Bulehora, Bore, Yabelo, Tepi, Aman, Tercha, Hosaina, Hawassa, Walaita Sodo, Arba Minch, Sawula, Jinka, Konso and Burji had cloud coverage and also received light to moderate rainfall. More than 30 mm of heavy rainfall was recorded over Chagni and Arjo.

Weather Forecast for next day

Oct. 17, 2024

በነገው ዕለት ዝናብ ሰጭ የአየር ሁኔታ ክስተቶች በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት የደቡብና ደቡብ ምስራቅ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን የሚኖራቸው ሲሆንና፤ በምዕራብ እና በደቡብ ምዕራብ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ ደግሞ ጠንካራ የደመና ክምችት ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል ምዕራብ አርሲ፣ ባሌ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ እና ምስራቅ ቦረና ዞኖች እንዲሁም የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ቄለም፣ ምዕራብ፣ ምስራቅ እና የሆሮጉድሩ ወለጋ ዞኖች፣ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳዉሮ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል፣ አሶሳ፣ ካማሽ እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ቡርጂ፣ አማሮ፣ ደራሸ፣ ደቡብ ኦሞ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ፣ ኑዌር፣ ኢታንግ እና ማጃንግ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ሁሉም ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የጃራር፣ ኤሬር፣ ዶሎ እና ቆራሔ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በማኦኮሞ፣ በካማሽ፣ በጋምቤላ፣ በላሬ፣ በአቦቦ፣ በዲማ፣ በጆሬ፣ በጎግ፣ በቤጊ፣ በነጆ፣ በጊምቢ፣ በአይራ፣ በጊዳሚ፣ በአንፍሎ፣ በሰዮ፣ በደዴሳ፣ በበደሌ፣ በቡሬ፣ በመቱ፣ በያዩ፣ በጨዋቃ፣ በሰተማ፣ በጎማ፣ በማሻ፣ በገሻ፣ በሶዶዙሪያ፣ በክንዶኮይሻ፣ በአርቤጎና እና በቦሬ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል ከሚኖረው የደመና ሽፋን ላይ በመነሳት ማዕከላዊ ጎንደር፤ አዊ ዞን፣ ምዕራብ ጎጃም፤ ምዕራብና ደቡብ ምዕራብ ሸዋ፣ ምስራቅ ሐረርጌ ዞን፤ ፋፈን፤ ጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀላባ፣ ሀድያ፣ የየም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች በጥቂት ስፍራዎቻቸው ላይ ቀላል መጠን ያለው ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ ያገኛሉ፡፡

For the next day, rain-producing weather events will have cloud coverage over the south and south east areas of our country, which are in their Bega second rainy season. Also, there will also be strong cloud coverage over the western and southwestern parts of the country. Along with this, from the Oromia region west Arsi, Bale, East Borena, Guji and west Guji zones as well as Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, Kelam, west, east and Horo Guduru Wellega zones; from the south west Ethiopia region Bench Sheko, Sheka, Kefa, Konta, west Omo and Dawuro zones; from the Benishangul Gumuz region Metekel, Asossa, Kamashi and Mao Komo zones; from the south Ethiopia region Wolaita, Gamo, Gofa, Basketo, Burji, Amaro, Derashe, south Omo and Gedeo zones; from Gambella region Agnuwak, Nuwer, Itang and Majang zones; all zones of Sidama region and from the Somali region Jarar, Erer, Dollo and Korahe zones will receive light to moderate rainfall in many places. In addition, Mao Komoo, Kamashi, Gambella, Lare, Abobo, Dima, Jore, Gog, Begi, Nedjo, Gimbi, Aira, Gidami, Anfilo, Seyo, Dedesa, Bedele, Bure, Mettu, Yayu, Chewaka, Setema, Gomma, Masha, Gesha, Sodozuria, Kindokoisha, Arbegona and Bore will receive more than 30 mm of heavy rain in 24 hours. On the hand, from the cloud coverage central Gondar; Awi zone, west Gojjam; west and south west Shewa, east Hararge zone; Fafen; Gurage, Silte, Halaba, Hadiya, Yem special zone, Kambata and Tembaro zones will receive light unseasonal rain at few places.