Daily Weather Report 24 Oct 15

Weather Summary for previous day

Oct. 14, 2024

በትናንትናው ዕለት በምዕራብ፣ በደቡብ ምዕራብ፣ በመካከለኛው እና በደቡብ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም አሶሳ፣ ጋምቤላ፣ ነጆ፣ ጊምቢ፣ አይራ፣ ጊዳአያና፣ ሻምቡ፣ አርጆ፣ በደሌ፣ ደንብዶሎ፣ ጎሬ፣ ጭራ፣ ጅማ፣ ሶኮሩ፣ ወሊሶ፣ ካቺሴ፣ ደብረማርቆስ፣ ጨፋ፣ መካነሰላም፣ እነዋሪ፣ ሾላገበያ፣ አዲስ አበባ፣ ኑራኤራ፣ ጃራ፣ ጊኒር፣ ደሎመና፣ ነገሌ፣ ቦሬ፣ ያቤሎ፣ ቡሌሆራ፣ እንድብር፣ ሆሳዕና፣ ወራቤ፣ ማሻ፣ ተርጫ፣ ወላይታ ሶዶ፣ ሳዉላ፣ አርባ ምንጭ፣ ምዕራብአባያ፣ ጂንካ፣ ኮንሶ እና ዲላ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን (1-29 ሚ.ሜ) ዝናብ አግኝተዋል፡፡

Yesterday, the west, south west, central and south parts of the country had cloud coverage. With this, Asossa, Gambella, Nedjo, Gimbi, Aira, Gidayana, Shambu, Arjo, Bedele, Denbidollo, Gore, Chira, Jimma, Sokoru, Waliso, Kachise, Debremarkos, Cheffa, Mekaneselam, Enewari, Sholagebeya, Addis Ababa, Nuraera, Jara, Ginir, Delomana, Negelle, Bore, Yabelo, Bulehora, Indibir, Hosaina, Werabe, Masha, Tercha, Walaita Sodo, Sawula, Arba Minch, Mirab Abaya, Jinka, Konso and Dilla received light to moderate (1-29 mm ) rain.

Weather Forecast for next day

Oct. 16, 2024

በነገው ዕለት በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት የደቡብና ደቡብ ምስራቅ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የተሻለ የደመና ሽፋን የሚኖራቸው ሲሆን፤ በተጨማሪም በምዕራብ እና በደቡብ ምዕራብ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የተስፋፋ የደመና ክምችት ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል አርሲ፣ ባሌ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረና እና ምስራቅ ቦረና ዞኖች እንዲሁም የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ቄለም፣ ምዕራብ፣ ምስራቅ እና የሆሮጉድሩ ወለጋ ዞኖች፣ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳዉሮ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል፣ አሶሳ፣ ካማሽ እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ቡርጂ፣ ኮንሶ፣ አማሮ፣ ደራሸ፣ ደቡብ ኦሞ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ፣ ኑዌር፣ ኢታንግ እና ማጃንግ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የጃራር ዞን በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል ከሚጠናከሩት የአየር ሁኔታ ክስተቶች ላይ በመነሳት ማዕከላዊ ጎንደር፤ አዊ ዞን፣ ምዕራብ ጎጃም፤ ምዕራብና ደቡብ ምዕራብ ሸዋ፣ ምስራቅ ሐረርጌ ዞን፤ ኤሬር፤ ጉራጌ፣ ሀላባ፣ ሀድያ፣ የየም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች በጥቂት ስፍራዎቻቸው ላይ ቀላል መጠን ያለው ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ ያገኛሉ፡፡

Tomorrow, over the south and south east areas of our country which are in their Bega second rainy season will have better cloud coverage. Additionally, the western and southwestern parts of the country will also have widespread cloud accumulation. Along with this, from Oromia region, Arsi, Bale, Guji and west Guji, Borena and east Borena zones, as well as Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, Kelam, west, east and Horo Guduru Wellega zones; from the south west Ethiopia region Bench Sheko, Sheka, Kefa, Konta, west Omo and Dawuro zones; from Benishangul Gumuz region Metekel, Asossa, Kamashi and Mao Komo zones; from the south Ethiopia region Walaita, Gamo, Gofa, Basketo, Burji, Konso, Amaro, Derashe, south Omo and Gedeo zones; from Gambella region Agnuwak, Nuwer, Itang and Majang zones; zones of Sidama region and from Somali region Jarar zone will receive light to moderate rainfall in most of their areas. On the other hand, due to the rising weather conditions, central Gondar, Awi zone, west Gojjam; west and south west Shewa, east Hararge zone; Erer; Gurage, Halaba, Hadiya, Yem special zone, Kambata and Tembaro zones will receive light unseasonal rainfall at few places.