Daily Weather Report 24 Oct 14
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በሰሜን ምዕራብ፣ በምዕራብ፣ በሰሜን ምስራቅ፣ በመካከለኛው፣ በደቡብ ምዕራብ፣ በደቡብ እና በምስራቅ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም ደባርቅ፣ አይከል፣ ሻሁራ፣ አምደወርቅ፣ ደብረታቦር፣ አዴት፣ ቻግኒ፣ አየሁ፣ ደብረማርቆስ፣ የትኖራ፣ ኮምቦልቻ፣ ባቲ፣ መካነሰላም፣ አለምከተማ፣ እነዋሪ፣ ደብረብርሀን፣ ማንኩሽ፣ ቡለን፣ አሶሳ፣ ነጆ፣ አይራ፣ ጊምቢ፣ አርጆ፣ በደሌ፣ ጎሬ፣ ቡሬ፣ ጋቲራ፣ ጭራ፣ ሶኮሩ፣ አምቦ፣ ወሊሶ፣ ፍቼ፣ አዲስ አበባ፣ ቢሾፍቱ፣ አቦምሳ፣ ቡኢ፣ ባሌሮቤ፣ ገለምሶ፣ ሚኤሶ፣ አዋሽ አርባ፣ ካራሚሌ፣ ጨለንቆ፣ ሂርና፣ ሐሮማያ፣ ሐረር፣ ደሎመና፣ ቡሌሆራ፣ ነገሌ፣ ማሻ፣ ተርጫ፣ ሆሳዕና፣ ወራቤ፣ ሐዋሳ፣ ዲላ፣ ኮንሶ፣ አዋሮ እና ጎዴ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን (1-29 ሚ.ሜ) ዝናብ ያገኙ ሲሆን፤ በአርሲሮቤ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, cloud coverage was observed over the northwest, west, northeast, central, southwest, south, and eastern parts of the country. With this, debark, Ayikel, Shahura, Amdework, Debretabor, Adet, Chagni, Ayehu, Debremarkos, Yetnora, Kombolcha, Bati, Mekaneselam, Alemketama, Enewari, Debrebrehan, Mankush, Bullen, Asossa, Nedjo, Aira, Gimbi, Arjo, Bedele, Masha, Tercha, Hosaina, Werabe, Hawasa, Dilla, Konso, Awaro and Gode received light to moderate rainfall (1-29 mm); heavy rain of more than 30 mm was recorded over Arsirobe in 24 hours.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት የደቡብና ደቡብ ምስራቅ የሀገራችን አከባቢዎች እንዲሁም በሰሜን ምዕራብ፣ በምዕራብ እና በደቡብ ምዕራብ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ቄለም፣ ምዕራብ፣ ምስራቅ እና የሆሮጉድሩ ወለጋ ዞኖች፣ ምዕራብ አርሲ፣ ባሌ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረና እና ምስራቅ ቦረና ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳዉሮ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል፣ አሶሳ፣ ካማሽ እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ቡርጂ፣ አማሮ፣ ደራሸ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ እና ማጃንግ ዞኖች እና የሲዳማ ክልል ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል ከሚጠናከሩት የአየር ሁኔታ ክስተቶች ላይ በመነሳት ሰሜን፣ ምዕራብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ምዕራብ ጎጃም፤ ምዕራብና ደቡብ ምዕራብ ሸዋ፣ ምስራቅ ሐረርጌ ዞን፤ ኤሬር፣ ጃራር፤ ደቡብ ኦሞ፤ ጉራጌ፣ ሀላባ፣ ሀድያ፣ የየም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች በጥቂት ስፍራዎቻቸው ላይ ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡
Tomorrow, there will be cloud coverage over the south and southeast areas of our country which are in their Bega second rainy season as well as the northwest, west and southwest of the country. Along with this, from the Oromia region, Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, Kelam, west, east and Horo Guduru Wellega zones, west Arsi, Bale, Guji and west Guji, Borena and east Borena zones; from the southwest Ethiopia region Bench Sheko, Sheka, Kefa, Konta, west Omo and Dawuro zones; from Benishangul Gumuz region Metekel, Asossa, Kamashi and Mao Komo zones; from the south Ethiopia region Wolaita, Gamo, Gofa, Basketo, Burji, Amaro, Derashe and Gedeo zones; o from Gambella region Agnuwak and Majang zones and Sidama region zones will receive light to moderate rainfall in most of their areas. On the other hand, due to the intensifying weather events, north, west and central Gondar, Awi zone, west Gojjam, west and southwest Shewa, east Hararge zone; Erer, Jarar; south Omo, Gurage, Halaba, Hadiya, Yem special zone, Kambata and Tembaro zones will receive light rainfall at a few places.