Daily Weather Report 24 Oct 12
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በሰሜን ምዕራብ፣ በምዕራብ፣ በሰሜን ምስራቅ፣ በመካከለኛው፣ በደቡብ ምዕራብ፣ በደቡብ እና በምስራቅ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም ዱብቲ፣ ጎንደር፣ አይከል፣ ባህር ዳር፣ ቻግኒ፣ ዳንግላ፣ ደብረማርቆስ፣ ደብረወርቅ፣ ነፋስመዉጫ፣ ሲሪንቃ፣ መሀልመዳ፣ መካነሰላም፣ ወረኢሉ፣ አለም ከተማ፣ እነዋሪ፣ ደብረብርሀን፣ ሾላገበያ፣ ማንኩሽ፣ ቡለን፣ አይራ፣ አንገርጉትን፣ ነቀምቴ፣ በደሌ፣ ጎሬ፣ ጭራ፣ ሊሙገነት፣ ሶኮሩ፣ አምቦ፣ ወሊሶ፣ ቢሾፍቱ፣ አዳማ፣ ባቱ፣ አቦምሳ፣ ቡኢ፣ ኑራኤራ፣ አርሲሮቤ፣ ባሌሮቤ፣ ገለምሶ፣ ሚኤሶ፣ መተሀራ፣ አዋሽ አርባ፣ ቁሉቢ፣ ጨለንቆ፣ ባቢሌ፣ ኩርፋጨሌ፣ ሂርና፣ ሐሮማያ፣ ቦሬ፣ ቡሌሆራ፣ አዲስ አበባ፣ ሐረር፣ ድሬዳዋ፣ ማሻ፣ አማን፣ ሆሳዕና፣ ተርጫ፣ ወላይታ ሶዶ፣ አርባ ምንጭ፣ ቡርጂ እና ቢላቴ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን (1-29 ሚ.ሜ) ዝናብ ያገኙ ሲሆን፤ በወራቤ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, north west, west, north east, central, south west, south and east parts of the country had cloud cover. In association with this, Dubti, Gondar, Ayikel, Bahirdar, Chagni, Dangila, Debremarkos, Debrework, Nefasmewucha, Sirinka, Mehalmeda, Mekaneselam, Wareilu, Alemketama, Enewari, Debrebrehan, Sholagebeya, Mankush, Bulen, Aira, Angergutin, Nekemte, Bedele, Gore, Chira, Limugenet, Sokoru, Ambo, Waliso, Bishoftu, Adama, Batu, Abomsa, Bui, Nuraera, Arsirobe, Balerobe, Gelemso, Mieso, Metehara, Awash Arba, Kulubi, Chelenko, Babile, Kurfachele, Hirna, Haromaya, Bore, Bulehora, Addis Ababa, Harar, Dire Dawa, Masha, Aman, Hosaina, Tercha, Wolaita Sodo, Arba Minch, Burji and Bilate received light to moderate rain (1-29 mm); more than 30 mm of heavy rainfall was recorded over Werabe in 24 hours.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በደቡብና ደቡብ ምስራቅ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን የሚኖራቸው ሲሆን፤ በሌላ በኩል በሰሜን ምዕራብ፣ በምዕራብ በመካከለኛው እና በደቡብ ምዕራብ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የተሻለ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ምዕራብ፣ ምስራቅ እና የሆሮጉድሩ ወለጋ ዞኖች፣ ሰሜን፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብና ምስራቅ ሸዋ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ፣ ጉጂ፣ ምዕራብ እና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ሐረር፤ ከአማራ ክልል የአዊ ዞን፣ ምዕራብ እና ምስራቅ ጎጃም ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ እና ዳዉሮ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል እና ካማሽ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀላባ፣ ሀድያ፣ የየም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የጌዲኦ ዞን፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የፋፈን፣ ጃራር፣ እና ዶሎ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በዳንግላ፣ በባህርዳር፣ በይልማናደንሳ፣ በደዴሳ፣ በበደሌ፣ በያዩ፣ በሰተማ፣ በሊሙሴቃ፣ በሶኮሩ፣ በደንዲ፣ በኢጃጂ፣ በቶሌ፣ በስልጤ፣ በሳንኩራ እና በዶዶላ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል ከሚጠናከሩት የአየር ሁኔታ ክስተቶች ላይ በመነሳት ድሬዳዋ፤ ምዕራብ ትግራይ ዞን፤ ሰሜን፣ ምዕራብ፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች በጥቂት ስፍራዎቻቸው ላይ ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡
Tomorrow, there will be cloud coverage over the south and south east areas of our country which are in their Bega second rainy season; on the other hand, there will be better cloud coverage over the north west, west central and south west parts of the country. Along with this, from the Oromia region Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, west, east and Horo Guduru Wellega zones, north, west, South west and east Shewa, Arsi and west Arsi, Bale and east Bale, Guji, west and east Hararge zones; Addis Ababa; Harar; from Amara region Awi zone, west and east Gojjam zones; from the south west Ethiopia region Bench Sheko, Sheka, Kefa, Konta and Dawuro zones; from Benishangul Gumuz region Metekel and Kamashi zones; from the central Ethiopia region Gurage, Silte, Halaba, Hadiya, Yem special zone, Kambata and Tembaro zones; from Gambella region Agnuwak and Majang zones; from the south Ethiopia region Gedeo zone; zones of Sidama region and from Somali region Fafen, Jarar and Dollo zones will receive light to moderate rainfall in most of their areas. In addition, Dangila, Bahirdar, Yilmanadensa, Dedesa, Bedele, Yayu, Setema, Limuseka, Sokoru, Dendi, Ijaji, Tole, Silte, Sankura and Dodola will receive heavy rainfall of more than 30 mm in 24 hours. On the other hand, due the intensifying weather events, Dire Dawa; west Tigray zone; north, west, south and central Gondar, north and south Wollo and north Shewa zones will receive light rainfall at a few places.