Daily Weather Report 24 Oct 11
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በአፋር፤ በምስራቅና መካከለኛ ኦሮሚያ፤ በምስራቅ አማራ፤ በደቡብ ምዕራብ እና ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጠንካራ የደመና ሽፋን የነበራቸው ሲሆን በሰሜንና ምዕራብ አማራ፤ በቤንሻንጉል ጉሙዝ፣ በጋምቤላ፤ በምዕራብ እና በደቡብ ኦሮሚያ፤ በሲዳማ፤ እና በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም ኤሊዳር፣ ሰመራ፣ ዳሊፋጊ፣ መተማ፣ ጎንደር፣ አይከል፣ ባህር ዳር፣ ቻግኒ፣ ደብረማርቆስ፣ ደብረወርቅ፣ ኮምቦልቻ፣ ጨፋ፣ መሀልመዳ፣ መካነሰላም፣ ደብረብርሀን፣ ማንኩሽ፣ ቡለን፣ ጋምቤላ፣ ፉኚዶ፣ ነጆ፣ ሻምቡ፣ ጊዳአያና፣ በደሌ፣ ጎሬ፣ ጅማ፣ ሊሙገነት፣ ሶኮሩ፣ ነቀምቴ፣ ወሊሶ፣ አቦምሳ፣ አርሲሮቤ፣ ባቱ፣ ገለምሶ፣ ቁሉቢ፣ ባቢሌ፣ ኩርፋጨሌ፣ ሂርና፣ ሐሮማያ፣ ቦሬ፣ ያቤሎ፣ አዲስ አበባ፣ ሐረር፣ እንድብር፣ ሆሳዕና፣ ማሻ፣ ወላይታ ሶዶ፣ ምዕራብአባያ፣ ኮንሶ፣ ጂንካ፣ ቢላቴ እና ዲላ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን (1-29 ሚ.ሜ) ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በጉሊሶ፣ በዱብቲ፣ በእነዋሪ፣ በአምቦ፣ በቡኢ፣ በግራዋ፣ በወራቤ እና በተርጫ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, strong cloud coverage was observed over the Afar, east and central Oromia, east Amhara, south west and central Ethiopia regions. Additionally, northern and western Amhara, Benishangul Gumuz, Gambella, western and southern Oromia, Sidama, and the southern region of Ethiopia had cloud coverage. In association with this, Elidar, Semera, Dalifagi, Metema, Gondar, Ayikel, Bahirdar, Chagni, Debremarkos, Debrework, Kombolcha, Cheffa, Mehalmeda, Mekaneselam, Debrebrehan, Mankush, Bulen, Gambella, Fugnido, Nedjo, Shambu, Gidayana, Bedele, Gore, Jimma, Limugenet, Sokoru, Nekemte, Woliso, Abomsa, Arsirobe, Batu, Gelemso, Kulubi, Babile, Kurfachele, Hirna, Haromaya, Bore, Yabelo, Addis Ababa, Harar, Indibir, Hosaina, Masha, Walaita Sodo, Mirab Abaya, Konso, Jinka, Bilate and Dilla received light to moderate rainfall (1-29 mm). In addition, more than 30 mm of heavy rain was recorded over Guliso, Dubti, Enewari, Ambo, Bui, Girawa, Werabe and Tercha.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በደቡብ እና ደቡብ ምስራቅ፤ እንዲሁም በሰሜን ምዕራብ፣ በምዕራብ እና በደቡብ ምዕራብ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ቄለም፣ ምዕራብ፣ ምስራቅ እና የሆሮጉድሩ ወለጋ ዞኖች፣ ምዕራብ አርሲ፣ ምዕራብ እና ደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የአዊ ዞን፣ ምዕራብ እና ምስራቅ ጎጃም ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ እና ሸካ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል፣ ካማሽ፣ አሶሳ እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የጌዲኦ ዞን እና የሲዳማ ክልል ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በዳንግላ፣ በቻግኒ፣ በአቸፈር፣ በባህርዳር፣ በጃዊ፣ በፓዌ፣ በማንዱራ፣ በጉቶጊዳ፣ በሲቡሲሬ፣ በአቤዶንጎሮ፣ በጅማራሬ፣ በባኮቲቤ እና በዳኖ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል ከሚጠናከሩት የአየር ሁኔታ ክስተቶች ላይ በመነሳት ከአፋር ክልል የሀሪ፣ አዉሲ እና ጋቢ ዞኖች፤ ሰሜን፣ ምዕራብ፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ደቡብ ወሎ፤ ሰሜንና ምስራቅ ሸዋ፣ አርሲ፣ ባሌ፣ ምስራቅ ሐረርጌ፤ አዲስ አበባ፤ ሐረር፤ ድሬዳዋ፤ ሲቲ፣ ፋፈን፤ ጉራጌ፣ ሀላባ፣ ሀድያ፣ የየም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች በጥቂት ስፍራዎቻቸው ላይ ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡
Tomorrow, there will be cloud coverage over the south and south east areas of our country which are in their Bega second rainy season, as well as the north west, west and south west parts of the country. Along with this, from the Oromia region Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, Kelam, west, east and Horo Guduru Wellega zones, west Arsi, west and south west Shewa zones; from Amhara region Awi zone, west and east Gojjam zones; from the south west Ethiopia region Bench Sheko and Sheka zones; from Benishangul Gumuz region Metekel, Kamashi, Asossa and Mao Komo zones; from the south Ethiopia region Gedeo zone and Sidama zones will receive light to moderate rainfall in many places. In addition, Dangila, Chagni, Achefer, Bahirdar, Jawi, Pawe, Mandura, Gutogida, Sibusire, Abedongoro, Jimma Rare, Bakotibe and Dano will experience heavy rainfall of more than 30 mm in 24 hours. On the other hand, due to the intensifying weather events, north, west, south and central Gondar, south Wollo; north and east Shewa, Arsi, Bale, west Hararge; Addis Ababa; Harar; Dire Dawa; Siti, Fafen; Gurage, Halaba, Hadiya, Yem special zone, Kambata and Tembaro zones will receive light rainfall at a few places.