Daily Weather Report 24 Oct 10

Weather Summary for previous day

Oct. 9, 2024

በትናንትናው ዕለት በቤንሻንጉል ጉሙዝ፤ በምዕራብ ኦሮሚያ፤ በደቡብ ምዕራብ እና ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጠንካራ የደመና ሽፋን የተስተዋለባቸው ሲሆን በሰሜንና ምስራቅ አማራ፤ በጋምቤላ፤ መካከለኛ፣ ደቡብ እና ምስራቅ ኦሮሚያ፤ በስዳማ፤ ሰሜንና ደቡብ ሶማሌ እና በማዕከላዊና ኢትዮጵያ አልፎ አልፎ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም ደባርቅ፣ አይከል፣ ባህር ዳር፣ አዴት፣ ቻግኒ፣ ላይበር፣ ደብረማርቆስ፣ ሲሪንቃ፣ ጨፋ፣ ማጀቴ፣ ፓዌ፣ ጋምቤላ፣ አቦቦ፣ ነጆ፣ ጊምቢ፣ አይራ፣ አለምተፈሪ፣ አንገርጉትን፣ ሻምቡ፣ በደሌ፣ ጎሬ፣ አርጆ፣ ሊሙገነት፣ ሶኮሩ፣ ነቀምቴ፣ ጭራ፣ እጃጂ፣ ኩሉምሳ፣ አቦምሳ፣ አደሌ፣ ገለምሶ፣ ጃራ፣ ደሎመና፣ ነገሌ፣ ቡሌሆራ፣ ያቤሎ፣ አዲስ አበባ፣ ሐረር፣ ማሻ፣ አማን፣ ተርጫ፣ ሳዉላ፣ ወላይታ ሶዶ፣ አርባ ምንጭ፣ ኮንሶ፣ ጂንካ፣ ሐዋሳ፣ ዲላ፣ ጂጂጋ እና ጎዴ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን (1-29 ሚ.ሜ) ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በማንኩሽ፣ በሸርኮሌ፣ በቡለን፣ በአሶሳ እና በአልጌ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, strong cloud coverage was observed over Benishangul Gumuz, west Oromia, and south west and south Ethiopia. Occasional cloud coverage was noted over north and east Amhara; Gambella; central and south Oromia; Sidama, north and south Somalia and central Ethiopia. In association with this, Debark, Ayikel, Bahirdar, Adet, Chagni, Laiber, Debremarkos, Sirinka, Cheffa, Majete, Pawe, Gambella, Abobo, Nedjo, Gimbi, Aira, Alemteferi, Angergutin, Shambu, Bedele, Gore, Arjo, Limugenet, Sokoru, Nekemte, Chira, Ijaji, Kulumsa, Abomsa, Adele, Gelemso, Jara, Delomana, Negelle, Bulehora, Yabelo, Addis Ababa, Harar, Masha, Aman, Tercha, Sawula, Walaita Sodo, Arba Minch, Konso, Jinka, Hawasa, Dilla, Jijiga and Gode received light to moderate rainfall (1-29 mm). In addition, more than 30 mm of heavy rain was recorded over Mankush, Sherkole, Bullen, Asosa and Alge.

Weather Forecast for next day

Oct. 11, 2024

በነገው ዕለት በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት የደቡብና ደቡብ ምስራቅ የሀገራችን አከባቢዎች የደመና ሽፋን የሚኖራቸው ሲሆን፤ በተጨማሪም በምዕራብ እና በደቡብ ምዕራብ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የተሻለ የደመና ሽፋንና ክምችት ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ቄለም፣ ምዕራብ፣ ምስራቅ እና የሆሮጉድሩ ወለጋ ዞኖች፣ ምዕራብና ደቡብ ምዕራብ ሸዋ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ እና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ ሐረር፤ ድሬዳዋ፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ እና ዳዉሮ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል፣ ካማሽ እና አሶሳ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የፋፈን ዞን በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በወንበራ፣ በቡለን፣ በካማሽ፣ በነጆ፣ በጊምቢ፣ በአይራ፣ በጉቶጊዳ፣ በሲቡሲሬ፣ በሳሲጋ፣ በጨዋቃ፣ በአቤዶንጎሮ፣ በጅማራሬ፣ በሆሮ፣ በሶኮሩ፣ በባኮቲቤ፣ በኖኖ፣ በአመያ፣ በቸሃ እና በማሻ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል ከሚጠናከሩት የአየር ሁኔታ ክስተቶች ላይ በመነሳት ሰሜን እና ሰሜን ምዕራብ ትግራይ ዞኖች፤ ሰሜን፣ ምዕራብ፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ ዞን፤ ሰሜንና ምስራቅ ሸዋ፣ ባሌ፣ ምዕራብ ሐረርጌ፤ ጉራጌ፤ ሀላባ፣ ሀድያ፣ የየም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች በጥቂት ስፍራዎቻቸው ላይ ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡

Tomorrow, over the south and south east areas of our country which are in their Bega second rainy season will have cloud coverage. Additionally, there will be better cloud coverage and accumulation over the west and south west parts of the country. Along with this, from the Oromia region, Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, Kelam, west, east and Horo Guduru Wellega zones, west and south west Shewa, Arsi and west Arsi, east Hararge, Guji, and west Guji zones; Harar; Dire Dawa; from the south west Ethiopia region Bench Sheko, Sheka, Kefa, Konta and Dawuro zones; from the Benishangul Gumuz region Metekel, Kamashi and Asossa zones; from Gambella region Agnuwak and Majang zones; from the south Ethiopia region Walaita, Gofa, Basketo and Gedeo zones; zones of Sidama region and Fafen zone of Somali region receive light to moderate rainfall in most of their areas. In addition, Wenbera, Bulen, Kamashi, Nedjo, Gimbi, Aira, Gutogida, Sibusire, Sasiga, Chewaka, Abedongoro, Jimma Rare, Horo, Sokoru, Bakotibe, Nono, Amaya, Cheha and Masha will receive more than 30 mm of heavy rain in 24 hours. On the other hand, due to the intensifying weather events, the north and north west Tigray zones; north, west, south and central Gondar, west and east Gojjam, Awi zone; north and east Shewa, Bale, west Hararge; Gurage, Halaba, Hadiya, Yem special zone, Kambata, and Tembaro zones will receive light rainfall at a few places.