Daily Weather Report 24 Oct 09
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በማይጨው፣ ደባርቅ፣ መተማ፣ ባህርዳር፣ ደብረታቦር፣ ሲሪንቃ፣ ዳንግላ፣ ቻግኒ፣ ላይበር፣ ቡለን፣ አሶሳ፣ ጋምቤላ፣ አቦቦ፣ ነጆ፣ ነቀምቴ፣ ቡሬ፣ ጎሬ፣ ጭራ፣ ጋቲራ፣ ባሌሮቤ፣ ቡሌሆራ፣ ቦሬ፣ ነገሌ፣ ያቤሎ፣ ደሎመና፣ ጊኒር፣ ገለምሶ፣ ሚኤሶ፣ ድሬዳዋ፣ ሐረር፣ ኢሚ፣ ሆሳዕና፣ ወላይታ ሶዶ፣ ሳዉላ፣ ጂንካ፣ ኮንሶ፣ ቡርጂ፣ ቢላቴ፣ ሐዋሳ፣ ዲላ፣ ቴፒ፣ ተርጫ፣ ሐረር፣ ሐዋሳ፣ ብላቴ እና ቡርጂ የደመና ሽፋን የነበራቸው ሲሆን ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በሐሮማያ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, in Maychew, Debark, Metema, Bahir Dar, Debretabor, Sirinka, Dangla, Chagni, Leiber, Bullen, Assosa, Gambella, Abobo, Nejo, Nekemte, Bure, Gore, Chira, Gatira, Bale Robe, Bulehora, Bore, Negele, Yabelo, Delomena, Ginir, Gemelso, Miesso, Dire Dawa, Harar,Immi, Hosanna, Wolayta Sodo, Sawla, Jinka, Konso, Burji, Bilate, Hawassa, Dilla, Tepe, Tercha, Harar, Hawassa, Bilatte and Burji had cloud cover, and at the same time, they received light to moderate amounts of rainfall. In addition, more than 30 mm of heavy rainfall was recorded in Haramaya.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት የደቡብና ደቡብ ምስራቅ የሀገራችን አከባቢዎች እንደዚሁም በሰሜን ምዕራብ፣ በምዕራብ፣ በደቡብ ምዕራብ እና በምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ቄለም፣ ምዕራብ፣ ምስራቅ እና የሆሮጉድሩ ወለጋ ዞኖች፣ ሰሜን፣ ምዕራብና ደቡብ ምዕራብ ሸዋ፣ ምዕራብ አርሲ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ባሌ እና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ ሐረር፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ እና ዳዉሮ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል፣ ካማሽ፣ አሶሳ እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ፣ ኑዌር፣ ኢታንግ እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጎፋ፣ ጋሞ፣ ባስኬቶ፣ አማሮ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የፋፈን ዞን በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በአሶሳ፣ በማኦኮሞ፣ በሸርኮሌ፣ በቤጊ፣ በሊሙ፣ በሲቡሲሬ፣ በሆሮ፣ በጅማራሬ፣ በሶኮሩ፣ በአሌ፣ በመቱ፣ በባኮቲቤ፣ በኖኖ፣ በጂባት፣ በግንደበረት፣ በአመያ እና በማሻ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል ከሚጠናከሩት የአየር ሁኔታ ክስተቶች ላይ በመነሳት ሰሜን እና ሰሜን ምዕራብ ትግራይ ዞኖች፤ ሰሜን፣ ምዕራብ፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ ዞን፣ ዋግኸምራ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፤ ድሬዳዋ፤ አርሲ፣ ምስራቅ ባሌ፤ ጉራጌ፤ ሀላባ፣ ሀድያ፣ የየም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች በጥቂት ስፍራዎቻቸው ላይ ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡
Tomorrow, there will be cloud cover over the Bega-rain benefitting areas of south and south east parts of the country, as well as the northwest, west, southwest and east of the country. In association with this, from Oromia region Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, Kelem, west, east and Horogudru Wellega zones, north, west and southwest Shewa, west Arsi, Gujina, west Guji, Bale and east Hararge zones; Harar; from Southwest Ethiopia region Bench Sheko, Sheka, Kefa, Konta and Dauro zones of the; from Benishangul-Gumuz region Mekkel, Kamash, Assosa and Maokomo zones; from Gambella region Agnuak, Nuer, Itang and Majang zones; from Southern Ethiopia region Wolayta, Gofa, Gamo, Basketo, Amaro and Gedeo zones; zones of Sidama region and from Somali region Fafen zone will receive light to moderate rainfall in many places. In addition, in Assosa, Maokomo, Sherkole, Begi, Limu, Sibusire, Horo, Jimarare, Sokoru, Alle, Metu, Bakotibe, Nono, Jibat, Gindeberet, Amaya, and Masha will receive heavy amounts of rainfall of more than 30 mm in 24 hours. On the other hand, Based on the intensifying weather phenomena north and northwest Tigray zones, north, west, south and central Gondar, west and east Gojjam, Awi zone, Waghemra, north and south Wollo, Dire Dawa, Arsi, east Bale, Gurage, Halaba, Hadia, Yem Special zone, Kembata and Tembaro zones will receive light amounts of rain in a few places.