Daily Weather Report 24 Oct 08
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በሰሜን፣ በምዕራብ፣ በሰሜን ምስራቅ፣ በመካከለኛው፣ በደቡብ፣ በደቡብ ምዕራብ እና በምስራቅ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም ሽሬእንደስላሴ፣ መቀሌ፣ ደባርቅ፣ ፂፂቃ፣ አይከል፣ ሻሁራ፣ ባህርዳር፣ አዴት፣ ዳንግላ፣ ቻግኒ፣ ላይበር፣ ሲሪንቃ፣ ማጀቴ፣ ደብረብርሀን፣ ማንኩሽ፣ ሸርኮሌ፣ ቡለን፣ አሶሳ፣ ጊምቢ፣ ነጆ፣ አይራ፣ አለምተፈሪ፣ አርጆ፣ ነቀምቴ፣ ጊዳአያና፣ በደሌ፣ ቡሬ፣ ጎሬ፣ ጅማ፣ ጭራ፣ ሊሙገነት፣ ሶኮሩ፣ እጃጂ፣ ቡኢ፣ ቢሾፍቱ፣ መተሀራ፣ ባቱ፣ ኑራኤራ፣ አዲስ አበባ፣ ላንጌ፣ መሰላ፣ ሐሮማያ፣ ጎብየሬ፣ ጂጂጋ፣ ጃራ፣ ቦሬ፣ ነገሌ፣ ቡለሆራ፣ ጋምቤላ፣ ላሬ፣ ፉኚዶ፣ ማሻ፣ ቴፒ፣ አማን፣ ማጂ፣ በተርጫ፣ ጂንካ፣ ኮንሶ፣ አርባ ምንጭ፣ ወላይታ፣ ቡርጂ፣ ሐዋሳ፣ ዲላ፣ ሆዕሳ እና ወራቤ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለዉ ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በአንገርጉትን፣ በሳዉላ እና በሐረር ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, the north, west, north east, central, south, south west and east parts of the country had cloud coverage. In association with this, Shire Endesilase, Mekelle, Debark, Tsitsika, Ayikel, Shahura, Bahirdar, Adet, Dangila, Chagni, Laiber, Sirinka, Majete, Debrebrehan, Mankush, Sherkole, Bullen, Asossa, Gimbi, Nedjo, Aira, Alemteferi, Arjo, Nekemte, Gambella, Lare, Fugnido, Masha, Tepi, Aman, Maji, Tercha, Jinka, Konso, Arba Minch, Walaita, Burji, Hawasa, Dilla, Hosaina and Werabe received light to moderate rainfall. In addition, more than 30 mm of heavy rain was recorded over Angergutin, Sawula, and Harar.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በደቡብና ደቡብ ምስራቅ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን የሚኖራቸው ሲሆን፤ በሌላ በኩል በሰሜን ምዕራብ፣ በምዕራብ እና በደቡብ ምዕራብ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የተሻለ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ቄለም፣ ምዕራብ፣ ምስራቅ እና የሆሮጉድሩ ወለጋ ዞኖች፣ ምዕራብና ደቡብ ምዕራብ ሸዋ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ባሌ፣ ምዕራብ እና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ ሐረር፤ ድሬዳዋ፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ እና ዳዉሮ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል፣ ካማሽ፣ አሶሳ እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ባስኬቶ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ሁሉም ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የፋፈን ዞን በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በአሶሳ፣ በካማሽ፣ በጅማአርጆ፣ በሲቡሲሬ፣ በጉቶጊዳ፣ በደዴሳ፣ በበደሌ፣ በጨዋቃ፣ በሊሙሴቃ እና በማሻ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል ከሚጠናከሩት የአየር ሁኔታ ክስተቶች ላይ በመነሳት ሰሜን እና ሰሜን ምዕራብ ትግራይ ዞኖች፤ ሰሜን፣ ምዕራብ፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ ዞን፤ የጎፋ ዞን፤ ጉራጌ፤ ሀላባ፣ ሀድያ፣ የየም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች በጥቂት ስፍራዎቻቸው ላይ ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡
Tomorrow, there will be cloud coverage over the south and south east areas of our country which are in their Bega second rainy season; on the other hand, the north west, west and south west parts of the country will have better cloud coverage. Along with this, from the Oromia region Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, Kelam, west, east and Horo Guduru Wellega zones, west and south west Shewa, Arsi and west Arsi, Guji and west Guji, Bale, west and east Hararge zones; Harar; Dire Dawa; from the south west Ethiopia region Bench Sheko, Sheka, Kefa, Konta and Dawuro zones; from the Benishangul Gumuz region Metekel, Kamash, Asossa and Mao Komo zones; from the Gambella region Agnuwak and Majang zones; from the south Ethiopia region Walaita, Basketo and Gedeo zones; all zones of Sidama region and Somali region Fafen zone will receive light to moderate rainfall in many places. In addition, Asosa, Kamash, Jimma Arjo, Sibusire, Gutogida, Dedesa, Bedele, Chewaka, Limuseka and Masha will have heavy rainfall of more than 30 mm in 24 hours. On the other hand, due to the intensifying weather events, the north and north west Tigray zones; north, west, south and central Gondar, west and east Gojjam, Awi zone; Gofa zone; Gurage, Halaba, Hadiya, Yem special zone, Kambata and Tembaro zones will receive light rainfall at a few places.