Daily Weather Report 24 Oct 07
Weather Summary for previous day
በትናትናው ዕለት በሰሜን ምዕራብ፣ በደቡብ ምዕራብ፣ በመካከለኛው፣ በሰሜን ምስራቅ፣ በምስራቅ እና በደቡብ የሀገራችን አካባቢዎች የደመና ሽፋንና ክምችት ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ሽሬእንደስላሴ፣ ማይጨው፤ ሻሁራ፣ ባህርዳር፣ ደብረታቦር፣ ቻግኒ፣ ዳንግላ፣ ደብረማርቆስ፣ የትኖራ፣ ላሊበላ፣ ኮምቦልቻ፣ ጨፋ፣ መካነሰላም፣ ደብረብርሀን፣ ሾላገበያ፣ አዋሽአርባ፤ አሶሳ፣ ቡለን፣ ጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ ኤልያ፣ ነቀምቴ፣ አንገርጉትን፣ ካችስ፣ ጎሬ፣ ጅማ፣ ሊሙገነት፣ ቡሬ፣ ጊዳአያና፣ ጭራ፣ ቡኢ፣ አዳማ፣ ኑራኤራ፣ ባቱ፣ ገለምሶ፣ ባሌሮቤ፣ ዶሎመና፣ ቦሬ፣ ሐረማያ፣ አዲስ አበባ፣ ድሬዳዋ፣ አማን፣ ተርጫ፣ ሆሳና፣ ወራቤ፣ ወላይታሶዶ፣ ዲላ፣ አርባምንጭ እና ጂንካ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ አግንተዋል፡፡ በተጨማሪም በማሻ፣ በጊኒር እና በአቦቦ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, there was cloud cover and accumulation in the northwest, southwest, central, northeastern, eastern, and southernmost areas of our country. In association with this, Shireselassie, Maichew, Shahura, Bahir Dar, Debretabor, Chagni, Dangla, Debre Markos, Yetnora, Lalibela, Combolcha, Cheffa, Mekansalam, Debre Berhane, Sholagagebeya, Awasharba, Asossa, Bullen, Gambella, Fugndo, Eliya, Nekemte, Angergutn, Kachis, Gore, Jimma, Limugenet, Bure, Gidaayana, Chira, Bui, Adama, Nuraera, Batu, Gemelso, Bale Robe, Dolomana, Bore, Haramaya, Addis Ababa, Dire Dawa, Aman, Tercha, Hosanna, Werabe, Wolaytasodo, Dilla, Arbminch and Jinka recived Light to moderate amount of rainfall. In addition, heavy amounts of rainfall of more than 30 mm were recorded in Masha, Ginir and Abobo.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት የምዕራብና የደቡብ ምዕራብ የሀገራችን አከባቢዎች ጠንካራ የደመና ክምችት የሚኖራቸው ሲሆን፤ የሰሜን ምዕራብ፤ የምስራቅ እና በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት የደቡብና ደቡብ ምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ቄለም፣ ምዕራብ፣ ምስራቅ እና የሆሮጉድሩ ወለጋ ዞኖች፣ ምዕራብ ሸዋ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ባሌ፣ ምስራቅ ቦረና፣ ምዕራብ እና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ እና ዳዉሮ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል፣ ካማሽ፣ አሶሳ እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ፣ ኢታንግ፣ ኑዌር እና ማጃንግ ዞኖች፤ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጎፋ፣ ጋሞ፣ ባስኬቶ፣ አማሮ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ሁሉም ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የፋፈን እና ጃራር ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሜ) ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በማኦ ኮሞ፣ በቤጊ፣ በጊዳሚ፣ በአንፊሎ፣ በአይራ፣ በሳሌኖኖ እና በማሻ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል ከሚጠናከሩት የአየር ሁኔታ ክስተቶች ላይ በመነሳት ሰሜን፣ ማዕከላዊ፣ ደቡብ እና ምዕራብ ጎንደር፣ ምዕራብ ጎጃም፣ አዊ ዞን፤ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ምስራቅ ባሌ እና ቦረና፤ ጉራጌ፤ ሀላባ፣ ሀድያ፣ የየም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ የሊበን፣ ኤረር፣ ዳዋ፣ አፍዴር፣ ሸበሌ፣ ቆራሄ እና ዶሎ፤ ደቡብ ኦሞ፣ አሌ እና ደራሸ ዞኖች በጥቂት ስፍራዎቻቸው ላይ ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡
Tomorrow, the western and southwestern areas of our country will have strong cloud accumulation. additionally; there will be cloud coverage over the northwest, east and Bega-rain benefitting areas in south and south east parts of the country. In association with this, from Oromia region Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, Kelem, west, east and Horogudru Wolga zones, west Shewa, Gujina, west Guji, Bale, east Borena, west and east Hararge zones; from the Southwest Ethiopia region Bench Sheko, Sheka, Fafa, Konta and Dauro zones; from Benishangul-Gumuz region: Metekel, Kamash, Asossa and Maokomo zones; from Gambella region Agnuak, Itang, Nuwer and Majang zones; from the Southern Ethiopia region Wolayta, Gofa, Gamo, Basketo, Amaro and Gedeo zones; all zones of the Sidama region and from Somali region Fafen and Jarrar zones receive light to moderate (1-29 mm) rainfall in many places. On the other hand, based on the intensifying weather events, north, central, south and west Gondar, west Gojjam, Awi Zone, Arsi and west Arsi, east Bale and Borena, Gurage, Halaba, Hadia, Yem Special zone, Kembata and Tembaro zones; Liben, Erer, Dawa, Afder, Shebelle, Korahe and Dolo; South Omo, Ale and Derashe zones will have light rainfall at a few places.