Daily Weather Report 24 Oct 04

Weather Summary for previous day

Oct. 3, 2024

በትናትናው ዕለት በመተሐራ፣ ባቲ፣ ጅማ፣ አዲስ አበባ፣ ጨለንቆ፣ ሒርና፣ ቡለን፣ ቻግኒ፣ ጭራ፣ ዶሎ መና፣ ፉኝዶ፣ ጋቲራ፣ ገለምሶ፣ ሐረር፣ ጅግጅጋ፣ ቁሉምሳ፣ ሊሙገነት፣ ስሪንቃ እና ቴፒ የደመና ሽፋን የነበራቸው ሲሆን ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም ሾላ ገበያ፣ አዋሽ አርባ፣ አሶሳ እና በካራሚሌ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, Metehara, Bati, Jimma, Addis Ababa, Chelenko, Hirna, Bulen, Chagni, Chira, Dolomena, Fugnido, Gatira, Gelemso, Harar, Jijiga, Kulumsa, Limugenet, Sirinka and Tepi had cloud coverage, along with they received light to moderate rainfall. In addition, more than 30 mm of heavy rainfall was recorded over Sholagebeya, Awash Arba, Asossa and Karamile.

Weather Forecast for next day

Oct. 5, 2024

በነገው ዕለት ዝናብ ሰጭ የሆኑ የአየር ሁኔታ ክስተቶች በተለይም በምዕራብ፣ በደቡብ ምዕራብ እና በምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች የተሻለ የደመና ክምችት የሚኖራቸው ሲሆን፤ በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት የደቡብና ደቡብ ምስራቅ የሀገሪቲ አከባቢዎች ላይም የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ቄለም፣ ምዕራብና ምስራቅ እና የሆሮጉድሩ ወለጋ ዞኖች፣ ምዕራብና ደቡብ ምዕራብና ሸዋ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ጉጂ፣ ባሌ፣ ምዕራብ እና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ ሐረር፤ ድሬዳዋ፤ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ እና ዳዉሮ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል፣ ካማሽ፣ አሶሳ እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጎፋ፣ ጋሞ፣ ባስኬቶ፣ አማሮ፣ ቡርጂ እና ጌዲኦ ዞኖች እና የሲዳማ ክልል ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በአሶሳ፣ በጅማአርጆ፣ በበደሌ፣ በያዩ፣ በመቱ፣ በማሻ፣ በአሌ እና በደደር በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል ከሚጠናከሩት የአየር ሁኔታ ክስተቶች ላይ በመነሳት ከአፋር ክልል የአዉሲ እና ጋቢ ዞኖች፤ ከትግራይ ክልል የምዕራብ እና ሰሜን ምዕራብ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፤ ሀላባ፣ ሀድያ፣ የየም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የሲቲ እና ፋፈን ዞኖች በጥቂት ስፍራዎቻቸው ላይ ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡

Tomorrow, the weather events that will produce rain will have better cloud accumulation, particularly in the west, southwest and east of the country. Additionally, there will be cloud coverage over Bega-rain benefitting areas in south and south east parts of the country. Along with this, from the Oromia region, Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, Kelam, west and east and Horo Guduru Wellega zones, west and south west and Shewa, Arsi and west Arsi, Guji, Bale, west and east Hararge zones; Harar; Dire Dawa; from Gambella region Agnuwak and Majang zones; from the south west Ethiopia region Bench Sheko, Sheka, Kefa, Konta and Dawuro zones; from Benishangul Gumuz region Metekel, Kamash, Asosa and Mao Komo zones; from the south Ethiopia region Walaita, Gofa, Gamo, Basketo, Amaro, Burji and Gedeo zones and the Sidama region zones will receive light to moderate rainfall in many places. In addition, Asosa, Jimma Arjo, Bedele, Yayu, Mettu, Masha, Ale and Deder will receive more than 30 mm of heavy rain in 24 hours. On the other hand, due to the intensifying weather events, from the Afar region Awusi and Gabi zones; from the Tigray region west and north west zones; west, north, south and central Gondar, Awi zone, west and east Gojjam zones from the Amhara region; from the central Ethiopia region Gurage; Halaba, Hadiya, Yem special zone, Kembata and Tembaro zones and from the Somali region Siti and Fafen zones will receive light rainfall in few places.