Daily Weather Report 24 Oct 03

Weather Summary for previous day

Oct. 2, 2024

በትናንትናው ዕለት በሰሜን ምዕራብ፣ በሰሜን ምስራቅ፣ በመካከለኛው፣ በደቡብ፣ በደቡብ ምዕራብ እና በምስራቅ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በጎንደር፣ ባህር ዳር፣ ዳንግላ፣ ላሊበላ፣ መካነሰላም፣ ጨፋ፣ ማጀቴ፣ እንዋሪ፣ ጭራ፣ ቁሉምሳ፣ ሐሮማያ እና ገርቦ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን (1-29 ሚ.ሜ) ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በሌላ በኩል በጭፍራ፣ በዳሊፋጊ እና በሳዉላ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, the north west, north east, central, south, south west and east parts of the country had cloud coverage. In association with this, Gondar, Bahirdar, Dangila, Lalibela, Mekaneselam, Chifra, Majete, Enewari, Chira, Kulumsa, Haromaya and Gerbo received light to moderate rainfall (1-29 mm). On the other hand, more than 30 mm of heavy rain was recorded over Chifra, Dalifagi, and Sawula.

Weather Forecast for next day

Oct. 4, 2024

በነገው ዕለት በምዕራብ፣ በደቡብ ምዕራብ እና በምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች እና በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት የደቡብና ደቡብ ምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ቄለም፣ ምዕራብና ምስራቅ እና የሆሮጉድሩ ወለጋ ዞኖች፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብና ምስራቅ ሸዋ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ጉጂ፣ ባሌ፣ ምዕራብ እና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ሐረር፤ ድሬዳዋ፤ ከጋምቤላ ክልል የማጃንግ ዞን፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ እና ዳዉሮ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል፣ ካማሽ፣ አሶሳ እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጎፋ ባስኬቶ እና ጌዲኦ ዞኖች እና የሲዳማ ክልል ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በአሶሳ፣ በወንበራ፣ በነጆ፣ በአሌ፣ በቡሬ፣ በመቱ፣ በያዩ፣ በማሻ እና በወንዶገነት በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል ከሚጠናከሩት የአየር ሁኔታ ክስተቶች ላይ በመነሳት ከአፋር ክልል የአዉሲ እና ሀሪ ዞኖች፤ ከትግራይ ክልል የሰሜን ምዕራብ ዞን፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፤ ሀላባ፣ ሀድያ፣ የየም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የፋፈን ዞን በጥቂት ስፍራዎቻቸው ላይ ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡

For the next day, there will be cloud coverage over the west, south west and east parts of the country, as well as the Bega-rain-benefiting areas of the south and south east parts of the country. Along with this, from the Oromia region Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, Kelam, west and east and Horo Guduru Wellega zones, west, south west and east Shewa, Arsi and west Arsi, Guji, Bale, west and east Hararge zones; Addis Ababa; Harar; Dire Dawa; from Gambella region Majang zone; from the south west Ethiopia region Bench Sheko, Sheka, Kefa, Konta and Dawuro zones; from Benishangul Gumuz region Metekel, Kamash, Asossa, and Mao Komo zones; from the South Ethiopia region Walaita, Gofa, Basketo and Gedeo zones and the Sidama region zones will receive light to moderate rainfall in many places. In addition, Asossa, Wenbera, Nedjo, Ale, Bure, Mettu, Yayu, Masha and Wendogenet will receive heavy rainfall of more than 30 mm in 24 hours. On the other hand, due to the intensifying weather events; from the Afar region Awusi and Hari zones; from Tigray region north west zone; from the Amhara region west, north, south and central Gondar; from the central Ethiopia region Gurage, Halaba, Hadiya, Yem special zone, Kembata and Tembaro zones and Somali region Fafen zone will receive light rainfall in few places.