Daily Weather Report 24 Oct 02
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት ትግራይ፤ አማራ፤ አፋር፤ ቤንሻንጉል ጉሙዝ፤ ጋምቤላ፤ ኦሮሚያ፤ ሲዳማ፤ ሰሜን ሶማሌ፤ ደቡብ ምዕራብ፣ ደቡብና ማዕከላዊ ኢትዮጵያ እንዲሁም ምስራቅ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም የሰሜን ምዕራብ፣ ማዕከላዊ እና ደቡብ ምስራቅ ትግራይ ዞኖች፤ የሰሜንና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች፤ የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብና ምስራቅ ሸዋ፣ ባሌ፣ አርሲ፣ ምዕራብ ጉጂ፣ ምዕራብ እና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ሐረር፤ ድሬዳዋ፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል እና አሶሳ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ እና ኑዌር ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ እና ዳዉሮ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሀድያ እና ስልጤ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የጎፋ፣ ጋሞ፣ ኮንሶ፣ ቡርጂ እና ደቡብ ኦሞ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የፋፈን ዞን ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለዉ ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በማንኩሽ፣ በቡለን፣ በጋምቤላ እና በፉኚዶ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, there was cloud cover over Tigray, Amhara, Afar, Benishangul-Gumuz, Gambella, Oromia, Sidama, Northern Somali, Southwest, South and Central Ethiopia and eastern parts of the country. In line with this, the northwest, central and southeast Tigray zones, north and central Gondar, Awi, west and east Gojjam, north and south Wollo and north Shewa zones; Jima, Ilubabor, Buno Bedele, Horo Guduru, west and east Wellega, west, southwest and east Shewa, Bale, Arsi, west Guji, west and east Hararge zones; Addis Ababa; Harar, Dire Dawa, from Benishangul-Gumuz region Metekel and Assosa zones; from Gambella region Anwuak and Nuer zones; from Southwest Ethiopia region Bench Sheko, Sheka and Dauro zones; from Central Ethiopia region Hadiya and Silte zones; from Southern Ethiopia region Gofa, Gamo, Konso, Burji and South Omo zones; Sidama region zones and from Somali region Fafen zone received light to moderate amounts of rainfall. In addition, more than 30 mm of heavy rainfall was recorded in Mankush, Bullen, Gambella and Fugnido.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት በምዕራብ፣ በደቡብ ምዕራብና በደቡብ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የተስፋፋ የደመና ሽፋን የሚኖራቸው ሲሆን፤ በተጨማሪም በሰሜን፤ ሰሜን ምስራቅና በምስራቅ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ቄለም፣ ምዕራብና ምስራቅ እና የሆሮጉድሩ ወለጋ ዞኖች፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብና ምስራቅ ሸዋ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ምስራቅ ቦረና፣ ባሌ፣ ምዕራብ እና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ሐረር፤ ድሬዳዋ፤ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ እና ዳዉሮ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል፣ ካማሽ፣ አሶሳ እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጎፋ፣ ጋሞ፣ ባስኬቶ፣ አማሮ፣ ደራሸ፣ ቡርጂ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ሁሉም ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በአሶሳ፣ በማኦኮሞ፣ በካማሽ፣ በቤጊ፣ በሊሙ፣ በሳሲጋ፣ በነጆ፣ በአልጌ፣ በጨዋቃ፣ በበደሌ፣ በአሌ፣ በቡሬ፣ በመቱ፣ በኦሞ፣ በማሻ እና በጎምቦራ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል አልፎ አልፎ ከሚጠናከሩት የአየር ሁኔታ ላይ በመነሳት ከአፋር ክልል የጋቢ እና ሀሪ ዞኖች፤ ከትግራይ ክልል የምዕራብ እና ሰሜን ምዕራብ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ምዕራብ እና ምስራቅ ጎጃም፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀላባ፣ ሀድያ፣ የየም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ እና ከሶማሌ ክልል የፋፈን ዞን በጥቂት ስፍራዎቻቸው ላይ ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡
Tomorrow there will be widespread cloud cover over the west, southwest and south areas of our country, and there will also be cloud cover over the north, northeast and east areas of our country. At the same time, the Oromia region includes Jimma, Iluubaabor, Buno Bedele, Kelem, west and east and Horogudru Wellega zones, west, southwest and east Shewa, Arsi and west Arsi, Guji and west Guji, east Borena, Bale, west and east Hararge zones; Addis Ababa, Harar, Dire Dawa, Gambella region, Angwuak and Majang zones; from Southwest Ethiopia region Bench Sheko, Sheka, Kefa, Konta and Dauro zones; from Benishangul-Gumuz region Mekkel, Kamash, Asosa and Maokomo zones; from Southern Ethiopia region Wolayta, Gofa, Gamo, Basketo, Amaro, Derashe, Burji and Gedeo zones; all zones of the Sidama region receive light to moderate amounts of rainfall in many places. In addition, in Assossa, Maokomo, Kamash, Begi, Limu, Sasiga, Nejo, Alge, Salta, Bedele, Ale, Bure, Metu, Omo, Masha and Gombora will receive heavy amounts of rainfall of more than 30 mm in 24 hours. On the other hand, based on the occasional intensifying weather, from Afar region Gabi and Hari zones, from Tigray region west and northwest zones; from Amhara region west, north, south and central Gondar, Awi zone, west and east Gojjam, North and South Wollo, Oromo Ethnic Special Zone and North Shewa zones; From the Central Ethiopia region Gurage, Silte, Halaba, Hadia, Yem Special Zone, Kembata and Tembaro zones, and from Somali region Fafen zone will receive light amounts of rain in a few places.