Daily Weather Report 24 Nov 30

Weather Summary for previous day

Nov. 29, 2024

በትናንትናው ዕለት በሰሜን ጎንደር፣ ምስራቅ ጎጃም፣ ሆሮ ጉድሩና ምዕራብ ወለጋ፣ ኢሉባቦር፣ ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረና እና ምስራቅ ቦረና፣ ሸካ፣ ቤንች ሸኮ እና ደቡብ ኦሞ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም ደባርቅ፣ ደ/ማርቆስ፣ ሻምቡ፣ ጊምቢ፣ አርጆ፣ ጎሬ፣ ቦሬ፣ ቡሌሆራ፣ ነገሌ፣ ሞያሌ፣ ቴፒ እና ጅንካ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን (1-29 ሚ.ሜ) ያለው ዝናብ ያገኛሉ ሲሆን በአማን ከባድ ዝናብ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, North Gondar, East Gojam, Horo Gudruna, West Welega, Ilubabor, West Guji, Borena and East Borena, Sheka, Bench Sheko and South Omo had cloud cover in our country. In this regard, Debark, D/Markos, Shambu, Gimbi, Arjo, Gore, Bore, Bulehora, Negele, Moyale, Tepi and Jinka will receive light to moderate rainfall (1-29 mm) and heavy rainfall will be recorded in Aman.

Weather Forecast for next day

Dec. 1, 2024

በነገው ዕለት በደቡብ ምዕራብ፣ በደቡብ እና በ ምዕራብ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የኢሉባቦር እና ቄለም ወለጋ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ከፋ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጎፋ እና ደቡብ ኦሞ ዞኖች ፤ከጋምቤላ ክልል የማጃንግ እና አኙዋክ ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የዳዋ እና ሊበን ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን (1-29 ሚ.ሜ) ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል ከሚጠናከሩት የአየር ሁኔታ ክስተቶች ላይ በመነሳት በኩነባ እና በርሃሌ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ ያገኛሉ፡፡

Tomorrow there will be cloud cover over the southwest, south and west parts of the country. Along with this, Ilubabor and Kelem Welega zones from the Oromia region; Sheka, Bench Sheko, West Omo and Kefa zones from South West Ethiopia region; Gofa and South Omo zones of South Ethiopia region, Majang and Anuwak zones of Gambella region and Dawa and Liben zones of Somali region will receive light to moderate rainfall (1-29 mm). On the other hand, based on the intensifying weather events, Kuneba and Berhale will experience light to moderate unseasonal rain.