Daily Weather Report 24 Nov 29
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በምዕራብ አማራ፣ ምዕራብና ደቡብ ኦሮሚያ፣ በጋምቤላ፣ በደቡብ ምዕራብ እና በደቡብ ኢትዮጵያ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ በላይበር፣ ጊዳ አያና፣ ሻምቡ፣ አርጆ፣ ጅማ፣ በደሌ፣ ቦሬ፣ ያቤሎ፣ ነገሌ፣ ጋምቤላ፣ አማን፣ ምዕራብ አባያ፣ አርባ ምንጭ፣ ሳውላ፣ ቡርጂ እና ዲላ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በደባርቅ፣ ጎሬ እና ኮንሶ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, there was cloud cover over the west Amhara, west and south Oromia, Gambella, Southwest and South Ethiopia. In this regard, Liber, Gida Ayana, Shambu, Arjo, Jimma, Bedele, Bore, Yabello, Negele, Gambella, Aman, Mirab Abaya, Arba Minch, Sawla, Burji and Dilla received light to moderate (1-29 mm) amounts of rainfall. In addition, heavy amounts of more than 30 mm were recorded in Debark, Gore and Konso.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት በምዕራብ፣ በደቡብ ምዕራብ፣ በደቡብ እና በሰሜን ምስራቅ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረናና ምስራቅ ቦረና ዞኖች እና የኢሉባቦር፣ ቄለም እና ምዕራብ ወለጋ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የማኦኮሞ ዞን፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ከፋ፣ ሸካ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳውሮ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የማጃንግ ዞን እና ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ኮንሶ፣ ደራሼ፣ አማሮ፣ ቡርጂ፣ ደቡብ ኦሞ እና ጌድኦ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን (1-29 ሚ.ሜ) ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል ከሚጠናከሩት የአየር ሁኔታ ክስተቶች ላይ በመነሳት በኢሮብ፣ አፅቢ፣ ጨርጨር፣ ራያዘቦ፣ ኩነባ፣ በረሀሌ፣ ኢረብቲ፣ መጋሌ፣ ኮሪ፣ እዋ፣ ቴሩ እና አውራ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ ያገኛሉ፡፡
Tomorrow there will be cloud cover over west, southwest, south and northeastern part of our country. In association with this, the Oromia region includes Gujina, west Guji, Borena and east Borena zones and Ilubabor, Kelem and west Wellega zones; Mao Komo zone from Benishangul-Gumuz region; Bench Sheko, Kefa, Sheka, Konta, west Omo and Dauro zones of Gambella region and Southern Ethiopia region of Gamo, Gofa, Basketo, Konso, Derashe, Amaro, Burji, south Omo and Gedeo zones. On the other hand, Besed on the weather events that intensify, you will get light to moderate amounts of unseasona rainfall in Erob, Atsebi, Chercher, Rayzebo, Kunneba, Berhale, Erabti, Megale, Kori, Ewa, Teru and Awra.