Daily Weather Report 24 Nov 28

Weather Summary for previous day

Nov. 27, 2024

በትናንትናው ዕለት በምዕራብና ደቡብ ኦሮሚያ፣ በመካከለኛው አማራ፣ በደቡብ ምዕራብ እና በደቡብ ኢትዮጵያ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ በደባርቅ፣ ደብረማርቆስ፣ ደብረወርቅ፣ መካነሰላም፣ ጊዳ አያና፣ አይራ፣ ነቀምቴ፣ አርጆ፣ ጅማ፣ ቡሬ፣ አደሌ፣ ቡሌሆራ፣ ሞያሌ፣ ማሻ፣ ማጅ፣ ጅንካ፣ ምዕራብ አባያ፣ ሳውላ እና ዲላ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በኮንሶ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, there was cloud cover over the west and south Oromia, central Amhara, Southwest and Southern Ethiopia. In this regard, Debre Markos, Debre Work, Mekanesalaam, Gida Ayanna, Aira, Nekemte, Arjo, Jimma, Bure, Adele, Bulehora, Moyale, Masha, Maj, Jinka, Mirab Abaya, Sawla and Dilla received light to moderate (1-29 mm) amounts of rain. In addition, heavy rainfall of more than 30 mm was recorded in Konso.

Weather Forecast for next day

Nov. 29, 2024

በነገው ዕለት በደቡብ፣ ደቡብ ምስራቅ፣ በደቡብ ምዕራብ እና በሰሜን ምስራቅ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የምዕራብ አርሲ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ፣ ቦረናና ምስራቅ ቦረና ዞኖች እንዲሁም የጅማ እና ኢሉባቦር ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳውሮ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የማጃንግ ዞን፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ኮንሶ፣ ደራሼ፣ አማሮ፣ ቡርጂ፣ ደቡብ ኦሞ እና ጌድኦ ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የአፍዴር እና ሸበሌ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን (1-29 ሚ.ሜ) ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል ከሚጠናከሩት የአየር ሁኔታ ክስተቶች ላይ በመነሳት በጨርጨር፣ ራያዘቦ፣ ቆቦ፣ ሀርቡ፣ ወረባቡ፣ ባቲ፣ ቃሉ፣ በረሀሌ፣ ኢረብቲ፣ መጋሌ፣ ኮሪ፣ ዱብቲ፣ ጭፍራ፣ ቴሩ እና አውራ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ ያገኛሉ፡፡

Tomorrow there will be cloud cover over the south, southeast, southwest and northeast areas of our country. At the same time, the Oromia region includes west Arsi, Guji and west Guji, Bale and east Bale, Borena and east Borena zones, as well as Jimma and Ilubabor zones; from Southwest Ethiopia region Bench Sheko, Sheka, Kefa, Konta, west Omo and Dauro zones; from Gambella region Majang zone; Sidama regional zones; from Southern Ethiopia region: Wolayta, Gamo, Gofa, Basketo, Konso, Derashe, Amaro, Burji, south Omo and Gedeo zones and from Somali region Afder and Shebelle zones will receive light to moderate amounts (1-29 mm) of rainfall. On the other hand, based on the intensifying weather events in Derek, Rayzebo, Kobo, Harbu, Werebabu, Bati, Kalu, Berhale, Erabati, Megale, Kori, Dubti, Chifra, Teru and Awra will receive light to moderate amounts of unseasonae rain.